ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአዳዲስ ሚኒስትሮችን ሹመት ለፓርላማ ያቀርባሉ
- አቶ ሬድዋን ሁሴን ለመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት
- አቶ ጌታቸው አምባዬ ለፍትሕ ሚኒስቴር
- አቶ በረከት ስምዖን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደኅንነት አማካሪነት ታጭተዋል
ወደ ሥልጣን ከመጡ ዘጠኝ ወራትን ያስቆጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በሚመሩት ካቢኔ ላይ የመጀመሪያውን መለስተኛ ሹም ሽር በማድረግ፣ ያጯቸው ሚኒስትሮች ሹመት እንዲፀድቅላቸው ሐሙስ ለፓርላማ ያቀርባሉ፡፡ በ2006 ዓ.ም. ረቂቅ በጀት ላይ ከፓርላማው ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡
- አቶ ጌታቸው አምባዬ ለፍትሕ ሚኒስቴር
- አቶ በረከት ስምዖን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደኅንነት አማካሪነት ታጭተዋል
ወደ ሥልጣን ከመጡ ዘጠኝ ወራትን ያስቆጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በሚመሩት ካቢኔ ላይ የመጀመሪያውን መለስተኛ ሹም ሽር በማድረግ፣ ያጯቸው ሚኒስትሮች ሹመት እንዲፀድቅላቸው ሐሙስ ለፓርላማ ያቀርባሉ፡፡ በ2006 ዓ.ም. ረቂቅ በጀት ላይ ከፓርላማው ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹም ሽር የሚያደርጉባቸው ተቋማት የፍትሕ ሚኒስቴር፣ የትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤትና የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መሆናቸውን፣ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሙዩኒኬሽን አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ብሔራዊ ፕላኒንግ ኮሚሽን የተባለ አዲስ መሥሪያ ቤት መዋቀሩንና ኮሚሽኑን የሚመራ ባለሥልጣን ሹመት፣ እንዲሁም የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ተቋም በሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ደረጃ በድጋሚ በመቋቋሙ ምክንያት፣ በሚኒስትር ማዕረግ የዋና ዳይሬክተር ሹመት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማው እንደሚቀርብ አቶ ጌታቸው አስረድተዋል፡፡
አዲስ ስለሚቀርቡ ተሿሚዎች ማንነት የተጠየቁት አቶ ጌታቸው፣ ማንነታቸውን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡
ሪፖርተር ከሌሎች ምንጮች ለማጣራት ባደረገው ጥረት፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤትን በሚኒስትር ማዕረግ እየመሩ የሚገኙት አቶ በረከት ስምዖንን፣ የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን የሚተኳቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
በተጨማሪም በቅርቡ ከኃላፊነት የተነሱትን የፍትሕ ሚኒስትር አቶ ብርሃን ኃይሉን፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው አምባዬ ይተኳቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የአዲስ አበባ ቀጣዩ ከንቲባ ይሆናሉ ተብለው በሚጠበቁት የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ድሪባ ኩማ ምትክ ደግሞ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ይሾማሉ ተብሏል፡፡
የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ስለዋሉ፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በመሆን የተሾሙት የቀድሞው የአዳማ ከንቲባ አቶ በከር ሻሌ ሹመት በፓርላማው መፅደቅ የሚገባው በመሆኑ፣ ለፓርላማው እንደሚቀርብና እሳቸውም ከሌሎች ተሿሚዎች ጋር ቃለ መሃላ እንደሚፈጽሙ አቶ ጌታቸው አስረድተዋል፡፡
አቶ በረከት ስምዖን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ የሆኑትን የቀድሞውን የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ፀጋዬ በርሄን ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
No comments:
Post a Comment