Wednesday, July 31, 2013

በቅርቡ ከአቶ ኩማ ደመቅሳ ላይ የአዲስ አበባ ከንቲባነትን የተረከቡት ከንቲባ ድሪባ ኩማ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ሐምሌ 28 ቀን 2005 . በመብራት ኃይል የሚያካሂደውን ሕዝባዊ ስብሰባ ፈቀዱ።
የአራት ፓርቲዎች ግንባር የሆነው መድረክ በማኒፌስቶውና በሌሎች የሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ለማድረግ በተደጋጋሚ ጊዜአት ጥያቄ ቀርቦ ውድቅ ሲደረግ መቆየቱን የተናገሩት የመድረክ ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን እንደሻው ናቸው። እንደ ሊቀመንበሩ ገለፃ መድረክ ሐምሌ 7 ቀን 2005 . መነሻውን 6 ኪሎ ያደረገ፣ መድረሻውን ደግሞ ድላችን ሐውልት ያደረገ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የእውቅና ጥያቄ ቢቀርብም በከተማዋ በርካታ የኮንስትራክሽን ስራዎች እየተካሄዱ በመሆኑ ሰልፍ ማካሄድ አትችሉም የሚል ሐምሌ 1 ቀን 2005 . ከከንቲባው /ቤት በተፃፈ ደብዳቤ መከልከሉን አስታውሰዋል።

ሠንደቅ ጋዜጣ -ሐምሌ24/2005

ከዚህ በፊት የሰማነው ምክንያት የከተማ ፖሊሶች ወይም የፀጥታ ሃይሎችሌላ ግዳጅ ላይ ስለሆኑወይምስልጠና ላይ ናቸውየሚል ነበር፡፡ አሁን ደግሞበከተማዋ በርካታ የኮንስትራክሽን ስራዎች እየተካሄዱ በመሆኑመባል ተጀመረ፡፡ አዲስ አበባ ተገንብታ እስክታልቅ እንግዲ ደህና ሠላማዊ ሰልፍ መከልከያ ሰበብ አገኙ፡፡
ምናልባትም አዲስ አበባ ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ ግንባታ ላይ የመሆኗ ቅኔው ይህ ይሆናል፡፡

No comments: