Tuesday, July 30, 2013

እኛ አንፈራም !

      እኛ አንፈራም !
እኛ ኢቲዮያውያን የጥቅም ሰዎች አይደለንም ! ከጥቀም ይልቅ ነፃነታችን እናስቀድማለን ! በርግጥከጎተራ ሙሉ ስንዴ እንክርዳድ አይጠፋምእንክረዳዶቹ ግንባንዳባንዳልጆች ናቸው ፡፡ አገሩን የሚሸጥባንዳነው ! ሆድ-አደርባንዳነው ! 

በጥቅም ያለማደር ለሀገር መሞት ሲዎርድ ሲዋረድ የነበረ! ያለ ! ከአባቶቻችን የወረስነው ነው ! ጣልያን ለአጭር ጊዜ ኢትዮጲያን በወረረበት ወቅት ብዙ የሚባሉ ፎቆችን ገንብቱአል ፡፡ መንገዶችንም ሰርቱአል አስቸጋሪውን የሊማሊሞን መንገድ ጨምሮ ይህ ግን ለአባቶቻችን ደስታ አልሰጣቸውም ፡፡ ከጥቅም ይልቅ ነፃነት ይቀድማል ! በመሆኑም ደማቸውን አፍሰዋል ! አጥንታቸውን ከስክሰዋል ! ከመስዋትነት የተረፉት ለሃገራቸው ሰማአት ለሆኑት ሀውልት አቁመዋል! ታሪክም ከትበዋል ! የሰማቱን የአቡነ ጰጥሮስን ሀውልት ጨምሮ፡፡ ይህ ሃውልት ግን በልማት ሰበብ ተነቅሏል! 700 በላይ ኢትዮጵያውያንን ለጨረሰው ሞሶሎኒ ጣሊያን ውስጥ ሃዉልት ቁሞለታል ! የሞሶሎኒን ሃውልት መቆም የተቃወሙትን ኢትዮጵያውያንን መንግስት አስሮ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ከአባቶቻችን የወረስነውን ነፃነት መንግስታችን ነጥቆናል ! ህገወጥ ተግባሩን በሰላማዊ ትግል እናስወግዳለን ! እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ለሃገሩ እና ለነፃነቱ ሲል ለመሞት ዝግጁ ነው! የመግደል አላማ ግን የለውም ! መግደል የአረመኔዎች ነው! የጨቁአኞች ነው ! የጨቋኞች ሰይፍ ከሰላማዊ ትግላችን አይገታንም ! ጀግና ቢሰየፍምጀግና ይወለዳል ! ላማዊ ትግላችን ይቀጥላል ! … ይቀጥላል ! … እኛ አንፈራም ! ፍራሃት የገዳዮች መለያ ባህሪ ነው! ለህዝብ ፍቅር ሲባል መሞት ሰማአትነት ነው ! መንግሰተ ሰማያትንም መውረስ ነው ! ፈጣሪም የሰው ልጆችን ለማዳን ሲል የሞተውን ሞት መሞት ነው ! 

ይድረስ ለገዳዮቹ፡- ለነፃነታችን ስንል ወረቀትና እስክርቢቶ ታጥቀን ወጠ'ናል ! ለመሞት ተዘጋጅተናል ! ብቻ እናንተ ተኩሱ ! እውነት እላቹሃልሁ ግምባራችን እንጂ ጀርባችን አንሰጣችሁም ! አንፈራም ! … አንፈራም !... 



No comments: