Wednesday, July 31, 2013

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ 

ጥያቄ ተነሳ




*የማህበሩ ፕሬዝዳንት ከኃላፊነቱ ዝቅ እንዲል ተደረገ

በዘሪሁን ሙሉጌታ

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር የጠራው ጠቅላላ ጉባኤና የአመራር ምርጫው የማህበሩ ሕግና ደንብ ባላከበረ መንገድ 


አብዛኛዎቹን ነባር የማህበሩን ም/ቤት ባገለለ መንገድ የተከናወነ በመሆኑ ህገወጥ ምርጫ ነው ሲሉ ከም/ቤቱ አላግባብ 

ታግደናል ያሉ የም/ቤቱ አባላት ገለፁ።

ጉባኤውና የማህበሩ አመራር ምርጫ ህጋዊ ባለመሆኑ ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የበጎ አድራጎትና ማህበራት ኤጀንሲ ተቃውሞአቸውን እንደሚያቀርቡ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልፀዋል።

አላግባብ ከማህበሩ እንድንገለል ተደርጓል ከሚሉት ወጣቶች ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፀው ቅዳሜና 

እሁድ በአዲስ አበበ ከተማ መስተዳድር የተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ህገ-ወጥ በመሆኑ ከ60 ያላነሱ፣ አላአግባብ የተባረሩ 

የማህበሩ ነባር አባላት የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ ለኤጀንሲው አቤቱታቸውን ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆናቸው 

አስታውቀዋል።ማህበሩ ከ70 ነባር አባላት መካከል ሊቀየሩ ወይም ሊሰናበቱ የሚችሉት በጉባኤው ቢሆንም ቅዳሜና እሁድ 

ጠቅላላ ጉባኤው የተካሄደው የምክር ቤት አባል ባልነበሩ ሰዎች እንደሆነ ወጣት ብርሃኑ ገልጿል። ከጉባኤው በፊት 21 

ወጣት፣ በመቀጠል ደግሞ በየክፍለ ከተማው ግምገማ እንዲካሄድ ተደርጎ ከነባሩ ም/ቤት አብዛኛዎቹ ታግደው አስር የሚሆኑት 

ብቻ እንዲቀጥሉ መደረጉን ከወጣት ብርሃኑ ገለፃ መረዳት ተችሏል።

ለአባላቱ መባረር ምክንያቱ ጉባኤው ከመካሄዱ በፊት ከሳምንት በፊት ክፍለ ከተማ ላይ ማን አመራር ይሁን? የሚለው ከላይ 

ከድርጅቱ የኢህአዴግ ሊግ፣ የማህበሩና የፎረም (ፍራክሽን) ተወስኖ የመጣ ነው ሲል ወጣት ብርሃኑ ተናግሯል።

ማህበሩ እሁድ ዕለት ባካሄደው የአመራር ምርጫ ማህበሩን ሲመራ የነበረው ወጣት ዮሐንስ ጣሰው ከኃላፊነቱ ዝቅ ተደርጎ 

በምትኩ ወጣት መድሃኔ መለስ እንዲተካ የተደረገ ሲሆን፤ በጉባኤ ወቅት የማህበሩ አርማ እንዲለወጥ ተደርጓል።

በጉዳዩ ላይ የማህበሩን አመራር አባላት ለመጠየቅ ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም ማህበሩ ጉባኤውን በተመለከተ በነገው ዕለት 

ጋዜጣዊ መግለጫ ስለሚሰጥ ከወዲሁ ምላሽ ለመስጠት እንደማይቻል የማህበሩ ሊቀመንበር ወጣት መድሃኔ መለስ ገልጿል

No comments: