Sunday, July 28, 2013

ሀና ውልይም

ሀና ውልይም

ሀና ውልያም ከኢትዮጵያ በ Larry P. Williams 


and Carri D. Williams 

እና 7 ልጆቻቸውን ለመቀላቀል በአሜሪካ 

ሲያትል በሚባል ከተማ በ2008 ዓ/ም ገባች :: ሀና 

ከኢትዮጵያ ሰትመጣ የተሻለ 

ኑሮና ትምህርት እንደሚኖራት ቢመሰልም ያጋጠማት 

ግን ማንም የሰው ልጅ  ይደረግበታል ተብሎ 

የማይታሰብም ነበር ::እነዚህ ግለሰቦች ሀናን በማሰራብ 

፣ በመደብደብና እንዲሁም የከብት በረት ውሰጥ በማሰተኛት ሲቀጥዋት ከቆዩ በኋላ 

በመጨረሻም ከፍተኛ ብርድና ዝናብ በነበረነት ቀን እራቃነ ሰጋዋን ውጪ እንድታድር 

አድርገዋት ነበር :: ያቺም ቀን በርሃብና በዱላ የተጎዳው የሀና ሰውነት ብርድ ዝናብ 

ሲወርድበት አደረ በማግሰቱም ሀና ጭቃ ላይ በፊቷ ተደፍታ ተገኝታለች:: 

መርማሪዋቹ እንዳሉት ሰውነቷ በኤሌትሪክ 

ገመድ የተገረፈበት ምልክት ይታይበታል 

ጭንቅላቷላይም ትልቅ እብጠት ነበረው 

በዛላይ ሰውነቷ በጣም የከሳ እንደነበር 

ገልፀዋል:: ሀና ሽንት ቤት የምትጠቀመው 

ከሁሉም ተለይታና ከቤት ወጣ የለ ነበር 

ይህንንም ለምን እንደሆነ ሲገልፁት የጉባት 

በሽታ (hepatitis) ሰለነበራት እኛ ላይ 

እንደይጋባ ብለን ነው ሲሉ ገልፀዋል :: የሀና እድሜ እንኳን በትክክል የሚያውቅ 

የለም ከ 13 እሰከ 16 ትሆናለች ተብሎ በግምት ሲነገርም ተሰምቷል የዚህም 

ምክንያት Adaption Agency የውሽት ወረቀት በማዘጋጀቱ ነው ብለዋል ::ይህም 

እውነተኛ ነገር ነው እነዚህ ልጆች ከሀገር ሲወጡ ወላጆቻቸው ሞተዋል፣ አሳዳጊ 

ካላገኙ ሴተኛ አዳሪ ይሆናሉ፣ እድሜ ይቀነሳል ለወላጅ ደግሞ ዶክተርና ሳይንቲሰት 

ይሆናሉ እንጂ ይገደላሉ ይራባሉ ኩላሊታቸው ይሽጣል ብለው ሲናገሩ አይሰማም 

::ይህ በሀና የተፈፀመው አሰቃቂ ድርጊት በብዙ ልጆች ላይ ሊፈፀም እንደሚችል 

አልጠራጠርም :: ይህ በተሰማ በወሩ የዚህ አይነት ድርጊት በሌላም ሁልት 

ኢትዮጵያዊያኖች ላይ ተከሰቶ ነበር ነገር ግን ሁለቱም ልጆች የአካል ጉዳት 

ቢደርሰባቸውም በህይወት ተርፈዋል::እኛ ኢትዮጵያኖች ፍቅር የምናውቅ፣ ሩሩህ፣ 

አዛኝ፣ ያለንን ተካፍለን የምናድር ፣ የሌላወን ልጅ ከራሳችን ለይተን የማናይ፣ የርስ 

በራሳችን ጠባቂ፣ ነበርን ::ምነው ዛሬ ልጆቻችን ሲሸጡ አብረን አሻሻጭ ሆንን :: 

አንድ በዚህ መልክ የወጣች ወጣት "  ተሸጥኩኝ" ነው ያምትለው ይህ በጣም 

ያሳዝናል :: ታዲያ በዚህ መልክ እያወጡ  ያሉት ልጆች ወደፊት ምን ይሉን ይሆን ?  

እኛሰ ተጠያቂ አንሆንም ? ብዙ ልብ ያሚሰብሩ አሳዛኝ ታሪኮችን እንሰማለን ያው 

ከንፈር መጠን እናልፈዋለን በመጨረሻም.... ሲያትል ያላቹ ወገኖቼ .... እነዚህ የሀና 

ገዳዮች ሰሞኑን ለክስ ቀርበዋልና እባካቹ ፍርድ ቤት በመሄድ ሀናም  ወገን እንዳላት 

አሳዩልን :: እግዚያብሔር የሰጣትን ሕይወት የነጠቋት እነዚህን ነፍስ ገዳዮችን 

የሚገባቸውን ፍርድ እንዲያገኙ በማንኛውም መንገድ እንረዳዳ ::



እግዚያብሄር የሀናን ነፍስ በገነት ያኑርለን !!


ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

No comments: