Monday, July 29, 2013

መንግስት የህዝበ ሙስሊሙ ንብረት የሆነውን እና በአንዋር መስጂድ ዙሪያ ከሚገኙት የንግድ ቤቶች መካከል አንዱን መውረሱ ታወቀ ፡፡

መንግስት የህዝበ ሙስሊሙ ንብረት የሆነውን እና በአንዋር መስጂድ ዙሪያ 

ከሚገኙት የንግድ ቤቶች መካከል አንዱን መውረሱ ታወቀ ፡፡

የአዲስ አበባ ህገ ወጡ መጅሊስ ፕሬዚደንት የሆነው ዶክተር አህመድም በጉዳዩ እጁ እንዳለበት ተጠቁሟል ፡፡ 

ንብረትነቱ የህዝበ ሙስሊሙ የሆነው እና በአንዋር መስጂድ ዙሪያ ካሉ ሱቆች መካከል አንዱ የነበረው ይህ የንግድ ቤት እንደ ሌሎቹ የንግድ ቤቶች ሁሉ ለረጅም አመታት በአንዋር መስጂድ ካርታ ስር የነበረና የኢትዮፕያ ንግድ ባንክ አንዋር ቅርንጫፍ ተከራይቶት ይጠቀምበት እንደነበረ ታውቋል ፡፡ ባንኩ በቀድሞዎቹ መጅሊሶች እንዝህላልነት ምክንያት ባንኩ በርካታ ውዝፍ እዳዎች የነበሩበት ቢሆንም ንብረትነቱ የመስጂዱ በመሆኑ አነሰም በዛም ባንኩ የወር ኪራይ ይከፍል እንደነበር የአዲስ አበባ ህገ ወጡ መጅሊስ አባላት አጋልጠዋል ፡፡ ሆኖም ግን በቅርቡ የስራ ዘመኑን የጨረሰው የኩማ ደመቅሳ አስተዳደር የአንዋር መስጂድ ካርታ መኖሩ እየታወቀ ካርታ የለውም አሁን በዶክተር አህመድ ዘመን ነው ካርታ ያገኘው ለማስባል ካርታ እንደ አዲስ ሲሰራለት ሆን ብለው ባንክ ቤቱን ከካርታው ውጭ በማድረግ እንዳስረኩ የታወቀ ሲሆን ፣ ይህ ለምን ይሆናል ባንኩን ጨምሮ በአንዋር መስጂድ ዙሪያ የሚገኙ የንግድ ቤቶች ሁሉ የመስጂዱ መሆናቸው እየታወቀ መንግስት ባንኩን ከካርታ ውጭ ማድረጉ አግባብ ባለመሆኑ እርምት እንዲደረግበት መጠየቅ አለብን በሚል
አንዳንድ የመጅሊሱ ስራ አስፈፃሚዎች ሃሳብ ቢያቀርቡም ዶክተር አህመድ ግን “ አይሆንም ይህን ጥያቄ መጠየቅ የለብንም፣ መንግስት አስቦበት ነው ካርታውን የሰራው ” በሚል እንዳከላከለ ለማወቅ ተችሏል ፡፡ የሌሎች ቤተ እምነት ሃላፊዎች የተወረሰባቸውን ንብረት ከመንግስት የማስመለስ ስራ ውስጥ ሲጠመዱ የኛዎቹ የመንግስት ሹመኞች ግን ከመንግስት ጋር በመመሳጠር ካርታ የነበረውን አንጋፋ መስጂድ ካርታ የለውም በሚል እና አዲስ ካርታ እንዲሰራለት በማስደረግ የህዝበ ሙስሊሙን ንብረት ያስዘርፋሉ ሲሉ የመጅሊስ የውስጥ ምንጮች ለፍትህ ሬዲዮ ገልፀዋል ፡፡ 

No comments: