Wednesday, July 31, 2013

ማን ነው ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ?

ማን ነው ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ?

ዶክርሻለቃአትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ በተለያዩ የኦሎምፒክ አደባባዮችና በበርካታ የሩጫ ውድድሮች አይበገሬና ረቺ በመሆን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ አንዲውለበለብ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ክብር ከፍ አድርጓል፡፡ ድሮ ነው፤ አሁን አሁን ግን የኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ክብር ዝቅ እያደረገ ማዋረዱን ስራዬ ብሎ ከተያያዘው ከራረመ፡፡ 

ባለፈው 2004 . ክረምት ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት ጋር በተያያዘእሳቸውን የሚተካ መሪ መቸም ቢሆን ሊፈጠር አይችልም…” በማለት ድምድም አደረገ፡፡ ታቱ የተባለ አንድ የስዊድን ፕሮፌሰርና ጓደኛው በእስራኤል የሚገኙፈላሻታዳጊዎችን IQ ለክተው 70 በታች ሆነ ብለውኢትዮጵያዊያን በሙሉ የአእምሮ ዘገምተኞች ናቸውከሚል ድምዳሜ ላይ ሲደርሱ / ብርሃኑ የተባለ ምሁር ጥናቱን “Black intellectual genocide” እንዳለው ኃይሌ ገብረስላሴም “All Ethiopian youth genocide” ነው የፈፀመብን፡፡ 

ሲገርመን አሁን ደግሞ ኃይሌ ልደቱን አክብሮ በያዝነው ክረምትም ከአዲስ ጉዳይ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ በርካታ ህሊናን የሚያደሙና አሳፋሪ ሃሳቦችን ሰንዝሯል፡፡ ኃይሌ በምርጫ ተወዳድሮ ፓርላማ የመግባትና ከዚያም የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት የመሆን ህልም አንዳለው ተናግሯል፡፡ ይህ የኃይሌ ብቻ ሳይሆን የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሆነ ሰው ሁሉ መብት ነው፡፡ ነገር ግን ኃይሌ ለዚህ ኃላፊነት ብቁ ነው ወይ አይደለም የሚለው ነው ትልቁ ጥያቄ፡፡ በእኔ መከራከሪያ ነጥብ ብቃት ሲባል ከፖለቲካ እውቀትና ልምድ ጋር የተያያዘ አይደለም ከቅንነት፣ ለህሊና ከመኖርና ለእውነት ከመሞት ጋር እንጂ፡፡ ምንም አንኳን የፖለቲካ ዕውቀትና ልምድ አንዲሁም የመምራት ተሰጥኦ እጅግ አስፈላጊ ቢሆንም ቢያንስ ቢያንስ ኃይሌ አባዱላ ገመዳን መሆን አያቅተውም፡፡ 

አትሌት ኃይሌ ለሚድያ በሚናገራቸው ሃሳቦቹ አድርባይ፣ ፈሪና ውሸታም ሰው መሆኑን ነው እኔ በትክክል ላረጋግጥ የቻልኩት፡፡ በመሆኑም እጅግ በጣም በከፋ የጠመንጃና የጡንቻ አገዛዝ ስር እየማቀቀች የምትገኘውና በምጣኔ ሃብት የዓለም ጭራ የሆነችው ኢትዮጵያ ባሁኑ ዘመን የሚያስፈልጓት አንደ ኃይሌ አይነት አድርባይ፣ ፈሪና ውሸታም የህዝብ ተወካዮች አይደለም እውነት እውነቱን በድፍረት ተናገረው መሽቶባቸው ቃሊቲ የሚያድሩ የአንዷለም አራጌና እስክንድር ነጋ አይነት ንፁህ ኢትዮጵያዊያን አንጂ፡፡ ለማጨብጨብ ለማጨብጨብማ ያሉትም የፓርላማ አባላት መች አነሱ፡፡ 

ኃይሌ በአዲስ ጉዳይ ጠያቂ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ስለመሆን ህልሙ ሲጠየቅ አንድ ግለሰብ ለፕሬዚዳንትነት ስለሚበቃበት ህጋዊ አካሄድ ባጭሩ ለማስረዳት ከሞከረ በኋላአንደው ለነገሩ ለመሆኑ ፕሬዚዳንት መሆን የሚጠላ ይኖራል?” ብሏል፡፡ እኔ በበኩሌ አንደ / ነጋሶ ጊዳዳና መቶ አለቃ ግርማ ወልደጊዮርጊስ በፕሬዚዳንትነት ስም ተቀምጨ የመለስ ዜናዊ /ህወሓት/ መጫወቻ አሻንጉሊት ከምሆን አፋር በርሃ ወርጄ ግመል ብጠብቅ መቶ አጅ አመርጣለሁ፡፡ 

በተጨማሪም ኃይሌ ዋናው ስልጣን የጠ/ሚኒስትሩ አንደሆነ ፕሬዚዳንት በመሆን ምንም ሚና መጫወት አንደማይችል በአዲስ ጉዳይ ጠያቂ ሲሞገት ህገ መንግስቱ ላይ የተዘረዘሩትን የፕሬዚዳንቱን ስልጣንና ኃላፊነት በአስረጂነት ጠቅሷል፡፡ / ነጋሶ ጊዳዳ በፕሬዚዳንትነት በቆየባቸው 10 አመታት ውስጥ መለስ ዜናዊ /ህወሓት/ የተባለ የፖለቲካ ልምሻ አግሮቹን ሽባ አድርጎ አስልሎ በማሽመድመድ አንዴት ወጣገባ በበዛበት ኮረኮንች የፖለቲካ ጎዳና ላይ አላራምድ ብሎ አንዳገደው በዳንኤል ተፈራ የተፃፈውንየነጋሶ መንገድመጽሓፍ ያው አንደለመደው አውሮፕላን ውስጥ ሲሆን አንዲያነብብ ኃይሌን አመክረዋለሁ፡፡ ኃይሌ ይህንምይቻላልካለ በፖለቲካ እውቀትና ልምድ ከደ/ ነጋሶ አበልጣለሁ እያለን ነው፡፡ ሲጀመር ኃይሌ አድርባይ፣ ፈሪና ውሸታም ስለሆነ አንደ መቶ አለቃ ግርማና ጀነራል አባዱላ ፍፁም አሻንጉሊት ከመሆን አያልፍም፡፡ 

“…ምን ያህል ሰዎች ናቸው በኢትዮጵያ ውስጥ 100 ያላነሱ አገራትን የዞሩ? በጣም ጥቂት ሰዎች ይመስሉኛል፡፡ እኔ ደግሞ አነዚህን መቶ አገሮች ማየት ችያለሁ…” በማለት አትሌት ኃይሌ አገር ለመምራት የሚያስችለውን የፖለቲካ እውቀት ያካበተበትን መንገድ ተናግሯል፡፡ቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂ…” ዓመት ያስቃል፡፡ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ከመማርና መጽሓፍትን ከማንበብ ይልቅ አገር ለአገር መዞር ብቻውን ለአገር መሪነት አንደሚያበቃ ስሰማ ይሄ የመጀመሪያዬ ነው፡፡ 

አትሌት ኃይሌ የአሻንጉሊት ስብስብ ስለሆነው የኢህአዴግ ፓርላማ ከተናገረው፦
! ፓርላማው አሁን እሳት ሆኗል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ፓርላማው ውስጥ የሚነገሩ ነገሮች ትኩረት እየተሰጣቸው ይመስለኛል…” 

ጥያቄ፦ 2005 . አጋማሽ ላይ ያየነው ፓርላማ ጥርስ አንዳወጣ ከተሰማ ኃይሌ ሲገባ የጥርሶቹ ብዛት ይጨምራል ብለን እናስብ?

ከዚህ በፊትም ጥርስ ያለው ይመስለኛል፡፡ ምናልባት አሁን ገንኖ የወጣው ለተለያዩ ነገሮች መፍትሔ እንዲሰጥ ሙግት ሲፈጥሩ ተመልክተህ ይሆናል አንጂ ቀደም ሲልም መጥፎ ነገር አልተመለከትኩም…” 

ታድያ ከዚህ በላይ ፈሪነት፣ ውሸታምነትና አድርባይነት ምን አለ? አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያን ህዝብ በጠመንጃ አፍኖ 21 ዓመታት በጉልበት እየረገጠ ሲገዛ ተቃዋሚዎችን በስድብ ሲያሸማቅቅ ከመሳቅና ከማጨብጨብ ውጭ አንድ የፓርላማ አባል በፓርላማው ውስጥ እጁን አውጥቶ ሲቃወመው የተመለከትንበት ቀን አንደሌለ መቶ በመቶ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፡፡ ታድያ አንዴት አትሌት ኃይሌቀደም ሲልም መጥፎ ነገር አልተመለከትኩምበማለት ይናገራል፡፡ 1997 . ያለፓርላማው እውቅና እና ውሳኔ አምባገነኑ መለስ በራሱ ስልጣን ብቻ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲያውጅ፣ ህገ መንግስቱ ከሚፈቅድለት ስልጣን ውጭ ሜጀር ጀነራል አበበ ተክለኃይማኖትንና ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤን ማረጋቸውን በመግፈፍ ሲያባርር የትኛው የፓርላማ አባል ነው የተቃወመው? መቶ ሺህ የድሃ ልጅ የረገፈበት ድንበራችንን በተለይም ባድመንየኢትዮጵያ መሬት አይደለምእያሉ የወያኔ መሪዎች በአደባባይ ሲናገሩ ማን ነው የተከራከራቸው? ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረንና የዜጎችን ሰብዓዊ መብት የሚያፍን የፀረ-ሽብር ህግ ሲወጣ አጅን አውጥቶ ከማፅደቅ ውጭ ማነው ለህዝብ በመቆርቆር የተቃውሞ ሀሳቡን ሲያሰማ ያየነው? ምንም የማያውቁ ድሃ ገበሬዎች በቋንቋ ልዩነት ብቻ ቤት ንብረታቸውን እየተነጠቁ ተደብድበው በየቦታው ሲፈናቀሉ ማን ነውይህ ነገር ጥሩ አይደለምበማለት ሲናገረ የሰማነው…? ታድያ ከዚህ በላይ ምንስ መጥፎ ነገር አለ? ለመሆኑ የፓርላማ አባላት ለውሳኔ እጅ ከማውጣትና ከማጨብጨብ በስተቀር የየግል አቋማቸውን ገልፀው ያውቃሉ? ይቅርታ ይደረግልኝና የፓርላማ ሰዎች በጠቅላላ ለእኔየሬሳ ፈስማለት ናቸው፡፡ ሲጀመር የይስሙላህ አንጂ በህዝብ ተመርጦ ለህዝብ የቆመ እውነተኛ እንደራሴ እስካሁን ፈፅሞ የለም፡፡ 

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝፍርድ ቤትውስጥ ችሎትፊት ቆሞአሁንም ፓርላማው የውሸት ስለሆነ ይፍረስ…” እያለ በድፍረት ይናገራልደክተርሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ደግሞፓርላማው እሳት ሆኗል፤ የሰራው ምንም መጥፎ ነገር የለም…” እያለ ያወድሳል ማነው ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ? ፍርዱን ለእናንተ ትቸዋለሁ፡፡

No comments: