Wednesday, July 31, 2013

ኢትዮጵያን ለማዳን እንተባበር!!!

ኢትዮጵያን ለማዳን እንተባበር!!!

ላለፉት 21 አመታት ዘረኛው የወያነ ቡድን በንፁሁ ህዝብ ላይ የሚያደርሰው 

ስቃይና  መከራ ተዘርዝሮ አያልቅም:: ከዚህም በከፋ ሁኔታ ሃገርንና ህዝብን 

ለማጥፋት በወጠነው እኩይ አላማው የምንወዳት ኢትዮጵያ ሃገራችንን ከምድረገፅ 

ለመሰረዝ ሲሯሯጥ እያየን አንጀታችን እያረረ ነገር ግን እጃችንን አጣጥፈን በትካዜና 

በሃዘን ብቻ እንድንኖር አስገድዶናል:: ይባስ ብሎ ይህ ፋሽስት የወሮበላ ቡድን እጅግ 

ለጆሮ በሚከብድ መልኩ እንደ ግራዚያኒ ለመሰሉ የውጭ ወራሪ ጨፍጫፊዎች 

ወግኖ ባደባባይ የሃገራችንን ታሪካዊ ክብር ሲያዋርድ : የገዛ ህዝቡን ሲደበደብ : 

ሲያስር በአይናችን አይተናል:: ባሁኑ ሰአት ይህ ቡድን ከአምባገነንነትም አልፎ 

የመጨረሻው አስቀያሚ ደረጃ ላይ መድረሱ ለማንኛችንም ግልፅ የወጣ ሃቅ ሆኗል:: 

ስለሆነም ይህንን የሃገርና የህዝብ ጠላት ከጫንቃችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ 

አሽቀንጥረን ለመጣል በሚደረገው ቀጣይ ህዝባዊ ርብርብ ከህዝብ ጋር በአንድነት 

በመቆም ታሪካዊ ግዴታችንን እንወጣ::

ዝምታው ይብቃ!!!


የምንወዳት ሃገራችን ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር!!

No comments: