Friday, July 26, 2013

Today @ኑር መስጂድ ነር — at ታሪካዊ ተቃውሞ ከፍተኛ የህዝብ ማዕበል በኒ እና አንዋር ተጋጠሙ


Today @ኑር መስጂድ ነር — at ታሪካዊ ተቃውሞ ከፍተኛ የህዝብ ማዕበል በኒ እና አንዋር ተጋጠሙ
እያንዳንዷ ጁምአ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪክ የሚጻፍባት ገጽ ከሆነች ቆይታለች። 

ጁምአ የፍትሕ፣ የነጻነትና የህዝብ ድምጽ ቀን ናት ለእኛ። የዛሬዋ ጁምአ ደግሞ 

በበኩሏ ታሪካዊ ሆና ውላለች። እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በአለም አቀፍ 

ደረጃ አገሪቱ ውስጥ እየተፈጸመ ላለው የሃይማኖት ጭቆና ድምጹን አሰምቷል። ዛሬ 

በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በተጠራው አለም አቀፍ ተቃውሞ በመላው አለም የሚገኙ 

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እለቱን ስለ ፍትህ በመጣራት ሲያሳልፉት ውለዋል፡፡

በዛረው እለት በአዲስ አበባ የተካሄደው የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አለማቀፍ 

የድምጻችን ይሰማ የተቃውሞ ሂደት በከፊል ይህን ይመስላል::

https://www.facebook.com/photo.php?

v=411212085665798&set=vb.100003310305307&ty

pe=2&theater


"ጥቂቶች"(ያው መንግስት ሊገባው የሚችለው በራሱ አባባል ነው) ዛረ በኒ(ኑር) መስጂድ ። ማሻአላህ በኒ ይደረጋል 

የተባለው ተቃውሞ ከበኒ ተነስቶ አንዋር ደረሰ አንዋር መስጊድ እና በኒ አንድ ሆኑ ዛረ .......ፎቶ ፥ድምፃችን ይሰማ













በዛሬው ዕለት ፒያሳ ለመጀመሪያዋ አስፋልቷም፤ አደባባዩዋም፤ ህንፃዎቿም ሳይቀሩ መቆሚያ አጥተው ጥቅጥቅ ባሉ ጀግኖች 

ተሞልታ ተክቢር ስትል ላያት የደስታ ዕንባ ታስነባ ነበር፡፡ “ድምፃችን ይሠማ”ዎች ቀናሁባችሁ፡፡ እንዲህ ሰጥ ለጥ ብሎ ለአሚሩ 

የሚታዘዝ፤ ለመስዋዕትነት የተዘጋጀ፤ በፕሮፓጋንዳ የማይሸነገል ቆራጥ ህዝብን ለመምራት በመታደላችሁ አላህን ልታመሰግኑ 

ይገባል፡፡ እኛም ታግሎ ለማታገል የቆረጠ መሪ ስለሰጠን ሃያሉን አላህእናመሠግናለን፡፡



No comments: