Tuesday, July 30, 2013

የመድረክ ሕዝባዊ ስብሰባ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል

የመድረክ ሕዝባዊ ስብሰባ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል

ሐምሌ ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፭ / ኢሳት ዜና :- የአራት ፓርቲዎች ግንባር የሆነው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በአደባባይ ላይ ሊያካሂድ ያቀደውን የአደባባይ ሰልፍ ተገዶ ወደ ሕዝባዊ ስብሰባ መቀየሩ ታውቋል፡፡ በዚሁ መሠረት ግንባሩ የፊታችን እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 / ሕዝባዊ ስብሰባ መጥራቱን የአዲስ አበባው ዘጋቢ ገልጿል፡፡

ከወቅታዊ የአገራችን ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሐምሌ 7 ቀን 2005 . በአዲስአበባ ከስድስት ኪሎ እስከድላችን ሐውልት ድረስ ሕዝባዊ ሰልፍ ለማካሄድ ግንባሩ መርሃግብር ነድፎ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም የአዲስአበባ ከተማ አስተዳዳር ከተማዋ በተለያዩ ልማቶች የተቆፋፈረች በመሆኑዋ ሰልፉን ለማካሄድ አመቺ አይደለም በሚል ምክንያት ፈቃድ መከልከሉ ታውቋል፡፡መድረክ የአደባባይ ሰልፉን በቤት ውስጥ ስብሰባ በመቀየር በድጋሚ ለአስተዳደሩ እንዲያውቀው ያስገባው ይፋዊ ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ አግኝቶ ስብሰባው በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የመብራት ኃይል አዳራሽ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ታውቋል፡፡

No comments: