Friday, November 29, 2013

ህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!!!!!

ህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!!!!!

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!
ግንቦት 7 ለፍትህና ለነፃነት!!!!!!!!
በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንም መከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው። ወያኔ ስላልቻለ ነው እንጂ ይህንን ከአለም አጽናፍ እስከ አለም አጽናፍ ያስተጋባ የወገን ደራሽ ድምጻችንን አዲስ አበባ ላይ እንደ አደረገው በሃይል ለማፈን ወደኋላ አይልም ነበር።
ሀፍረት የለሾቹ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች ይህን የተጋለጠ ሀገርና ህዝብ አዋራጅ ተግባራቸውን እና በውሸት የተበከለ ገመናቸውን ለመሸፈን ከዚያም አልፈው የዋሆችን በማታለል የፖለቲካ ትርፍ ለማትረፍ የተለመደ ቲያትር መስራቱን ተያይዘውታል። ቴዎድሮስ አድሃኖም ችግሩ ባለበት በሳውዲ መሬት ላይ ሳይሆን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በራሱ ወጪ አሳፍሮ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ባፈሰሳቸው ኢትዮጵያውያን መሃል እየተጎማለለ ያዛኝ ቅቤ አንጓች ቲያትሩን ሲሰራ ትንሽ እንኳን ሀፍረት አይታይበትም። እነዚሁኑ ወደ ሀገር የተመለሱ አእምሯቸው በችግር የተመሰቃቀለ ዜጎች ወደ ካሜራ እየገፉ ስለ ሳውዲ ኤምባሲያቸውና ስለመንግስታቸው ‘ድንቅ” አገልግሎት እንዲናገሩ ያስጠኗቸውን ተመሳሳይ አረፍተ ነገር መስማት የሚያሳዝን ባይሆን ኖሮ ተወዳዳሪ የሌለው ኮሜዲ ይወጣው ነበር። እውነቱ ዛሬ በሀገራችን የሰፈነው ስደትና አብሮት የሚመጣው መከራ ሁሉ ዋናው አምራች ፋብሪካ ወያኔ መሆኑ ነው። ወያኔ የገነባው ጥቂት ጀሌዎቹንና ሎሌዎችን ተጠቃሚ ያደረገና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በተለይ ወጣቱ በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ያደረገው ስርአት ነው።
የስደታችንና የመከራችን ምንጭ ስደት የሚመጣው በሀገር ተስፋ መቁረጥ ነው። እንጀራ ፍለጋና ጭቆናና አፈና ሽሽት አምልጠን በየባዕድ ሀገሩ እንድንከራተት የሚያደርገን የወያኔ ስርአት ነው። በታሪካችን ውስጥ ተሰደን በባዕድ የተዋረድነው በወያኔ ምክንያት ነው። በሀገር ውስጥ በአፈና ስር ሆናችሁ፣ በውጪው አለምም በየኢምባሲው የምታሰሙት ጩኸትና የምታፈሱት እምባ እብሪትና ትእቢት ያደነደነውን፣ ዝርፊያ ያደነዘዘውን የወያኔን ልብ እንደማያሸብረው ማወቅ አለብን። የወያኔ ሹማምንቶች ይግረማችሁ ብለው ከአላንዳች ሀፍረት ያውም በሳውዲ አረቢያ ወጪ ተጓጉዘው ሀገር የገቡትን ግራ የተጋቡ ስደተኞች ለፖለቲካቸው ማሳመሪያ በቴሌቪዥን ስእልና ፎቶግራፍ መነሻ ሲያደርጉትና ለፖለቲካ ስራ መሳሪያ ሲያውሉት እያየን ነው። በነሱ ቤት ብልጥ ፖለቲከኞች መሆናቸው ይሆናል። በኛ ቁስል ላይ እንጨት እየሰደዱ መሆናቸውን ግን ፈጽሞ አይሰማቸውም።
ወያኔ በመካከለኛው ምስራቅ ተሰደው ለፍተው የሚኖሩት ወገኖቻችን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ያውቃል። ቢያንስ በየኢምባሲው ያስቀመጣቸው ነጋዴዎች ይነግሩታል። ችግሩን እንዳላየና እንዳልሰማ የሚያየው ከዜጎች ይልቅ እነሱ አፈር ግጠው ለፍተው ለሚያመጧት የውጪ ምንዛሬ የበለጠ ፍቅር ስላለው ነው። በዚህ ተግባሩ ወያኔ ወገኑን የሸጠ ባሪያ ፈንጋይ ነጋዴ እንጂ የመንግስት መሪ መሆኑ ያጠራጥራል።
ግንቦት 7 የፍትህና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ዘወትር እንደሚለው ሁሉ ይህ የዜግነትና የሀገር ውርደት፣ ይህ ሁሉ የወገን መከራ የሚቆመው የዚህ ሁሉ መሰረት የሆነው ወያኔና ስርአቱ ከመሰረቱ ሲነቀልና ሲወገድ መሆኑን ላፍታም አይዘነጋውም። እንባችን የሚደርቀው ደማችን በየቦታው መፍሰሱ የሚቆመው መብታችን እንደዜጋ ተከብሮ ቀና ብለን የምንሄድበት ሀገር በትግላችን የተቀዳጀን ጊዜ ብቻ ነው። ግንቦት 7ን ተቀላቀሉ በያላችሁበት ግንቦት 7 ሁኑ!! እኛ ከዚህ ውርደት ሞቶ የሚገኘው ነጻነት ይሻላል ብለን የተነሳን ልጆቻችሁ ነን። እርሰዎስ?
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
ግንቦት 7 ለፍትህና ለነፃነትImage

Who is responsible for the slavery and death of our sisters in Saudi Arabia and the rest of Arabia ?

Who is responsible for the slavery and death of our sisters in Saudi Arabia and the rest of Arabia ?
1. The Tigray Liberators who sold our sisters to all over Middle East by manipulating using cadre delala agents and profited billions In the process of fulfilling their ethnic cleansing evil crime.
2. The Saudi Arabia and the rest of Arabia Governments and civilians slaving our sisters to death in barbaric way.
3. All the racist and kersam supporters of Tigray Liberators regime for helping all suffrage of Ethiopians to happen inside and outside Ethiopia directly or indirectly.
May God punish all of you ! Amen!!!


የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ከተቃዋሚዎችን ጋር ተወያዩ


የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ከተቃዋሚዎችን ጋር ተወያዩ


ለአውሮፓ፣ ኤዥያ፣ ካሪቢያን፣ፓስፊክና አፍሪካ ጉባኤ አዲስ አበባ የተገኙት የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች 

በቢሮአቸው ከተቃዋሚዎች ጋር ተወያዩ፡፡ ከስፔን፣ ፖርቱጋል፣ ማልታ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ የተወከሉ ልኡካን 


በኢትዮጵያ ስላላው አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ ከተቃዋሚዎች በኩል ከመድረክ ዶ/ር መረራ 


ጉዲና፣ ከአንድነት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና አቶ አስራት ጣሴ፣ ከመኢአድ አቶ አበባው መሀሪ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ 


ይልቃል ጌትነት እንዲሁም ከኢዴፓ አቶ ልደቱ አያሌውና የፓርቲው ፀሀፊ ተገኝተዋል፡፡


ከተወካዮቹ በኩል የተነሱት ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው፡-


1. የፓርቲዎች ቁጥርስ ለምን በዛ?

2. በህግ አግባብ የተመዘገቡ ስንት ናቸው?
3. በፕሮግራምና በርዕዮተ ዓለም ልዩነታቸውና ተመሳሳይነታቸው ምን ይመስላል?
4. የምርጫ ሥርዓታችሁ የትኛው ነው?
5. በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ቁጥር ስንት ይሆናል?
6. ተቃዋሚዎች ከህዝብ ጋር ለመገናኘት ምን ዘዴ ትጠቀማላችሁ? በገጠርና በከተማስ ምን ይማስላል?
7. ከዲያስፖራ ጋር ያላችሁ ግንኙነትስ እንዴት ያለ ነው?
8. ከሌሎች ሀገራት ፓርቲዎች ጋር ግንኙነት አላችሁ ወይ?
9. የአውሮፓ ህብረት ምን ማድረግ (ማገዝ) ይችላል?
10. ህብረ-ብሄራዊና ክልላዊ ፓርቲዎች የቁጥራችሁ ምጣኔ


ከተሰጡት መልሶች የሚከተሉት የዶ/ር ነጋሶ ሀሳብ ይገኙበታል፡-

ኢህአዴግና የመሰረተው መንግስት ህገ መንግስቱን በመጣስ መካናቸውን፤
ህገ- መንግስቱን የሚጥሱ ህጎችን ማውጣት ብርቁ እንዳልሆነ፤
የአንድ ፓርቲ አምባገነንነት ጥግ ድረስ ማድረሱን፤
የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን በውሸት ክስ እያሰሩ ፓርቲዎችን እንደሚያዳክሙ ለምሳሌ አንዱአለም አራጌና በቀለ 

ገርባ፤ ተቃወሚዎች ልሳን እንዳያሳትሙ እንደሚደረግና እንደሚዘጋባቸው ለምሳሌ የአንድነት ፓርቲዋ ፍኖተ-ነፃነት፤

የቢሮና የአደራሽ ኪራይ መከለልከል፤
የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማድረግ መከልከል፤
ቅስቀሳ ማድረግ መከልከል (ሰዎች፣ የቅስቀሳ መሳሪያዎችና መኪኖች እንደሚታሰሩ)፣
ሁል ጊዜ ያለው ዛቻ፣ ማስፈራሪያ፣ ድብደባ፣ ጠለፋ፣ ማሰቃየት፤
አባላትን ከመሬት፣ ከስራና ከቤታቸው ማፈናቀል፤
በውሸት ተቃዋሚዎችን ከአሸባሪዎች ጋር ማዛመድ፤
የስም ማጥፊያ ፊልሞችን መፈብረክ፤
እንቅስቃሴን መገደብ፤
መንግስት ፍትሃዊ የሆነና በህግ አግባብ የተቀመጠ የፋይናንስ ድጋፍ ማድረግ ሲገባው ያለማድረግ፤
ዜጎችን ዘር ማጥፋት እስኪመስል ድረስ ከይዞታቸው ማፈናቀል፤
ለውይይትና ለድርድር እንቢ ባይ መሆን የሚሉ የኢህአዴግ ባህሪያት ቀርበዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ምን ማድረግ ይችላል ለሚለው ደግሞ የሚከተሉት ማሳሰቢያዎች ተሰጥተዋል፡-


ለልማትና ለማህበራዊ ጉዳዮች ድጋፍ አትሥጡ ባይባልም ኢህአዴግ ግን የተሰጠውን ዕርዳታ

1. የራሱን ቢሮክራሲ እንደሚያጠናክርበት
2. አፋኝ የፀጥታና የፖሊስ ኃይሉን እንደሚያጠናክርበት
3. የፓርቲውን መዋቅሮች እንደሚያደራጅበት እንዲያውቁ ተብሏል፡፡ በቅርቡ እንኳ የአውሮፓ ህብረት የሰጠውን 

217 ሚሊዮን ዩሮ ይህ ሳይጠና መሆን እንዳልነበረበት


ተቃዋሚዎቹ የሚፈልጉት ነገር ቢኖር ሥልጣን ተቆርሶ እንዲሰጣቸው ሳይሆን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው 


እንዳይገደብና እውነተኛ ምርጫ እንዲደረግ ምህዳሩ መስተካከል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ በአጠቃላይ ሰብአዊና 


ዴሞክራሲያዊ መብት እንዲከበር ጫና እንዲያደርጉ፤ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር እንዲደራደር እንዲያግባቡ 


የሚሉ ናቸው፡፡


አቶ ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው ሁኔታው ወደ አስከፊ ደረጃ እያዘገመ በመሆኑና የኢህአዴግ ባህሪ ፍፁም 


አምባገነናዊ በመሆኑ ከንግዲህ ኢህአዴግ አጋር እንደማይሆናቸው ገልፀዋል፡፡

አቶ ልደቱ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የታይታ (window dressing)፣ በህብረተሰቡ፣ በተቃዋሚዎችና 

በመንግስት በኩል ኋላ ቀር የፖለቲካ ባህል እንዳለ፣ ድህነት በበኩሉ የዴሞክራሲ ጠንቅ መሆኑ፣ ነፃ የዴሞክራሲ 


ተቋማት እንደሌሉና መንግስትና ፓርቲ እንደማይለዩ አስረድተዋል፡፡


ሰብሳቢዋ በበኩላቸው “COMPREHENSIVE SYSTEM OF DIALOGUE” እንዳላቸው፣ ጠ/ሚ/ሩን 


በአመት ሁለቴ እንደሚያገኟቸው፣ በፀረ ሽብር ህጉ ህገ ወጥነት እንደሚያምኑ፣ ለ2007ቱ ምርጫ ከወዲሁ ዝግጅት 


እንደጀመሩና የምርጫ ግብረኃይል እንዳቋቋሙ ገልጸዋል፡፡ አና ጎሜዝ በበኩላቸው ከኢትዮጵያኑ ባልተናነሰ 


የመንግስትን ባህሪያት ሲተነትኑ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከዚህ ውይይት ብዙ ነገር እንደማይጠብቁ በማጠቃለያ ሀሳባቸው ገልጸውልናል፡፡

Thursday, November 28, 2013

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!
26351fb59e29fb0a1375427042
NOV28,2013
በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንምመከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው።
ወያኔ ስላልቻለ ነው እንጂ ይህንን ከአለም አጽናፍ እስከ አለም አጽናፍ ያስተጋባ የወገን ደራሽ ድምጻችንን አዲስ አበባ ላይ እንደ አደረገው በሃይል ለማፈን ወደኋላ አይልም ነበር።
ሀፍረት የለሾቹ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች ይህን የተጋለጠ ሀገርና ህዝብ አዋራጅ ተግባራቸውን እና በውሸት የተበከለ ገመናቸውን ለመሸፈን ከዚያም አልፈው የዋሆችን በማታለል የፖለቲካ ትርፍ ለማትረፍ የተለመደ ቲያትር መስራቱን ተያይዘውታል። ቴዎድሮስ አድሃኖም ችግሩ ባለበት በሳውዲ መሬት ላይ ሳይሆን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በራሱ ወጪ አሳፍሮ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ባፈሰሳቸው ኢትዮጵያውያን መሃል እየተጎማለለ ያዛኝ ቅቤ አንጓች ቲያትሩን ሲሰራ ትንሽ እንኳን ሀፍረት አይታይበትም።
እነዚሁኑ ወደ ሀገር የተመለሱ አእምሯቸው በችግር የተመሰቃቀለ ዜጎች ወደ ካሜራ እየገፉ ስለ ሳውዲ ኤምባሲያቸውና ስለመንግስታቸው ‘ድንቅ” አገልግሎት እንዲናገሩ ያስጠኗቸውን ተመሳሳይ አረፍተ ነገር መስማት የሚያሳዝን ባይሆን ኖሮ ተወዳዳሪ የሌለው ኮሜዲ ይወጣው ነበር።
እውነቱ ዛሬ በሀገራችን የሰፈነው ስደትና አብሮት የሚመጣው መከራ ሁሉ ዋናው አምራች ፋብሪካ ወያኔ መሆኑ ነው። ወያኔ የገነባው ጥቂት ጀሌዎቹንና ሎሌዎችን ተጠቃሚ ያደረገና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በተለይ ወጣቱ በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ያደረገው ስርአት ነው። የስደታችንና የመከራችን ምንጭ ስደት የሚመጣው በሀገር ተስፋ መቁረጥ ነው። እንጀራ ፍለጋና ጭቆናና አፈና ሽሽት አምልጠን በየባዕድ ሀገሩ እንድንከራተት የሚያደርገን የወያኔ ስርአት ነው። በታሪካችን ውስጥ ተሰደን በባዕድ የተዋረድነው በወያኔ ምክንያት ነው።
በሀገር ውስጥ በአፈና ስር ሆናችሁ፣ በውጪው አለምም በየኢምባሲው የምታሰሙት ጩኸትና የምታፈሱት እምባ እብሪትና ትእቢት ያደነደነውን፣ ዝርፊያ ያደነዘዘውን የወያኔን ልብ እንደማያሸብረው ማወቅ አለብን።
የወያኔ ሹማምንቶች ይግረማችሁ ብለው ከአላንዳች ሀፍረት ያውም በሳውዲ አረቢያ ወጪ ተጓጉዘው ሀገር የገቡትን ግራ የተጋቡ ስደተኞች ለፖለቲካቸው ማሳመሪያ በቴሌቪዥን ስእልና ፎቶግራፍ መነሻ ሲያደርጉትና ለፖለቲካ ስራ መሳሪያ ሲያውሉት እያየን ነው። በነሱ ቤት ብልጥ ፖለቲከኞች መሆናቸው ይሆናል። በኛ ቁስል ላይ እንጨት እየሰደዱ መሆናቸውን ግን ፈጽሞ አይሰማቸውም።
ወያኔ በመካከለኛው ምስራቅ ተሰደው ለፍተው የሚኖሩት ወገኖቻችን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ያውቃል። ቢያንስ በየኢምባሲው ያስቀመጣቸው ነጋዴዎች ይነግሩታል። ችግሩን እንዳላየና እንዳልሰማ የሚያየው ከዜጎች ይልቅ እነሱ አፈር ግጠው ለፍተው ለሚያመጧት የውጪ ምንዛሬ የበለጠ ፍቅር ስላለው ነው። በዚህ ተግባሩ ወያኔ ወገኑን የሸጠ ባሪያ ፈንጋይ ነጋዴ እንጂ የመንግስት መሪ መሆኑ ያጠራጥራል።
ግንቦት 7 የፍትህና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ዘወትር እንደሚለው ሁሉ ይህ የዜግነትና የሀገር ውርደት፣ ይህ ሁሉ የወገን መከራ የሚቆመው የዚህ ሁሉ መሰረት የሆነው ወያኔና ስርአቱ ከመሰረቱ ሲነቀልና ሲወገድ መሆኑን ላፍታም አይዘነጋውም።
እንባችን የሚደርቀው ደማችን በየቦታው መፍሰሱ የሚቆመው መብታችን እንደዜጋ ተከብሮ ቀና ብለን የምንሄድበት ሀገር በትግላችን የተቀዳጀን ጊዜ ብቻ ነው።
ግንቦት 7ን ተቀላቀሉ በያላችሁበት ግንቦት 7 ሁኑ!! እኛ ከዚህ ውርደት ሞቶ የሚገኘው ነጻነት ይሻላል ብለን የተነሳን ልጆቻችሁ ነን። እርሰዎስ?
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

«ሰው ለሰው» የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትእዛዝ ስክሪፕቱን እንዲቀይር ተገደደ።

«ሰው ለሰው» የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትእዛዝ ስክሪፕቱን እንዲቀይር ተገደደ።

«ሰው ለሰው» የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትእዛዝ ስክሪፕቱን እንዲቀይር ተገደደ።
ኢሳት ዜና :- በኢትዩጵያ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ በረዥምነቱ ቀዳሚውን ቦታ በመያዝ የሚታውቀው ሰው ለ ሰው ተከታታይ ድራማ 109 ክፍሎች ያህል ከተላለፈ በኃላ፣ ሰዎች በማህበራዊ ድህረ ገጾች የድራማው ተዋንያን የሆነውን በትወና ስሙ አስናቀ የተባለውን ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር በማመሳስል ገጸባህሪውና ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለስልጣናትን በገንዘብ ይገዛሉ ፤ ፍትህን ይረግጣሉ ፤ በሰው ህይዎት ይነግዳሉ፡ ፤ ሰው ያስገድላሉ፤ ህዝብን ያስለቅሳሉ፤ በወንጀል ይነግዳሉ፤ ሰው በላ እና ነፍሰ ገዳይ አምባገነን ናቸው ሲሉ እንደሚተቹዋቸው ይታወቃል።
ጉዳዩ ያሳሰባቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን ድራማው የመንግሰትን ስራ እያንቋሸሸ ፤ ከመንግስት ፍላጎት ውጭ እየሄደ በመሆኑ እንዲቀየር የኢቲቪን አስተዳዳሪዎች ማዘዛቸውን የወስጥ ምንጮች ገልጸዋል። ውስጥ አዋቂዎች ድራማው የወ/ሮ አዜብ መስፍንን ታሪክ የተከተለ እና አብዛኛውን የመንግስት ባለስልጣናት የመክበሪያ ዘዴ የጠቆመ በመሆኑ መንግሰት እንደ ነገሪ ሰሪ ተመልከቶታል ብለዋል። ጉዳዩ ዙሪያ የኢቲቪን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።Image

Wednesday, November 27, 2013

ተዋርደን አንቀርም!!!

ተዋርደን አንቀርም!!!

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)
ethiopia



ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡ መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡ በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡ ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣ እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡
አቶ ሽመልስ ከማል ለሚዲያወች የሰጡትን ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላና ሰበብ አዳምጨዋለው፡፡ “ሰላማዊ ሰልፉን ያገድንበት ምክንያት ጸረ-አረብ መፈክሮች ስለነበሩ ነው” ብለዋል፡፡ መጀመሪያ ደረጃ ሰልፉ ገና ከግቢው ፈቅ ሳይል ነው ያፈኑት፣ ሆኖም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አንድ በአንድ እየሆንን ወደ ሰላማዊ ሰልፉ መዳረሻ ለመሄድ ስንሞክር የተወሰኑ አመራሮችን አራት ኪሎ አካባቢ ያዙን፣ እነሱ ቀድሞውኑ ሰልፉ እንዳይካሄድ ስለወሰኑ ነው እንጅ ትንሽ እንኳ ተንቀሳቅሶ የሰልፉን ባህሪ ለመገምገም ምንም እድል አልሰጡንም፡፡
ለምሳሌ ሰልፉን እንደምናደርግ ይፋ ባደረግን ማግስት ከራዲዮ ፋና ተደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎች ተጠይቄ ነበር፡፡ በቃለ-መጠይቁ ሰላማዊ ሰልፉ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም እንደምናደርግ ተናግረናል፡፡ ጋዜጠኛው ለሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች መልዕክት ካለ ብሎ በጠየቀኝ ወቅት የሳውዲ አረቢያ ሰንደቅ አላማ ላይ ያለው ምልክትና ጽሁፍ ሀይማኖትን የሚመለከት በመሆኑ ዜጎች በስሜታዊነት ባንዲራ እንዳያቃጥሉ፣ እነሱ ቢያዋርዱንም እኛ ግን ክብር ያለን ዜጎች ስለሆንን ተቃውሟችንን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ማካሄድ እንዳለብን ተናግሬ ነበር፡፡ ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት በዚህና በተለያየ መንገድ በማያሻማ ሁኔታ መልዕክት ባስተላልፍም እነሱ ግን ይህን በመቁረጥ አላስተላለፉትም፡፡ እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ሲደመሩ የአቶ ሽመልስ ከማል ንግግር ነጭ ውሸት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡
ሁለተኛ የአንድ ሀገር መንግስት ዜጎቹ እየተደፈሩ፣ በማጎሪያ ካምፕ በረሀብና በውሃ ጥም፣ ሌላው ቢቀር መጸዳጃ ቤት እንኳ ተከልክለው ፍጹም ከሰውነት ክብራቸው ወርደው እየተበደሉ፣ እየተገደሉ ባለበት ወቅት ገና ለገና ተቃዋሚ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በሚንጸባረቅ ጥላቻና ተቃውሞ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ይበላሽብኛል ብለን መናገር እንችላለን? ሌላው ይቅር አንድ ክፉና ደጉን የለየ ሰው የሚያስበው ጤነኛ ሃሳብ ነው ማለትስ ይቻላል?
ከእገዳው ባሻገር የሚደንቀው ነገር ደግሞ በፓርቲያችን አመራሮችና አባላት ላይ የተደረገው ድብደባ ነው፣ የሆነ ማስተላለፍ የፈለጉት ነገር ያለ ይመስላል፡፡ የጭካኔያቸውን መጠን እንድናውቅ የሚደበድቡት አቅመ-ደካሞችን፣ ሽማግሌዎችንና ሴቶችን እየመረጡ በፍጹም አረመኔነት ነበር፡፡ ይህን ተግባራቸውን ስመለከት የደረሱበትን የዝቅጠት ደረጃ መታዘብ ችያለው፡፡ ከፖለቲካ ልዩነትም፣ ከአምባገነንነትም በላይ ሰዎቹ እንደታመሙ ነው ለመረዳት የቻልኩት፣ስር የሰደደ የቁስ ሰቀቀንና የስልጣን ጥም የተጣባቸው፣ ለዚያ ሲሉም የትኛውንም አይነት ውርደት ለመቀበል የቆረጡና የሞራል ልዕልናቸውን ሙሉ በሙሉ ያጡ ሰዎች ናቸው፡፡ ስነ-ልቦናቸው ክፉኛ ተቃውሷል እንጂ ሀገር እመራለው የሚል ቡድን እንዲህ ያለ ተግባር ይፈጽማል ለማለት እቸገራለው፡፡ በአባላቶቻችን ላይ ክፍኛ ድብደባ ተፈጽሟል፣ እስከዛሬም እግሮቻቸው መራመድ የማያስችላቸው፣ የሚያነክሱ ሰዎች አሉ፡፡ እውነት ለመናገር ይሄ እብደት ነው፡፡ አንዲት እራሷን መከላከል የማትችል ሴትን ለሶስት መደብደብን ከዚህ በተሻለ ልገልጸው አልችልም፡፡
አንድ ማስገንዘብ የምፈልገው ነገር ለኛ ዋናው ጉዳይ የዜጎቹ ህጋዊነት ወይም ህጋዊ ያለመሆን ጉዳይ አይደለም፡፡ በምንም አይነት መንገድ ሴቶች እየተደፈሩ፣ ወንዶች በየስርቻው እንደ ውሻ ተቀጥቅጠው እየተገደሉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ታጉረው ይህን ሁሉ መከራ መቀበላቸውን ልንታገሰው፣ ወይም ከህጋዊነት አንጻር እየተራቀቅን ልንመለከተው አንችልም፣ ስለ ህግም ከተወራ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ጭፍጨፋው ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ባላቸው ላይ ጭምር ሲፈጸም እንደነበር አምኗል፡፡
ባለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን የአንዱ ሀገር ዜጋ ካለ ሀገሩ መገኘት አገር ይያዝ የሚያስብል አይደለም፡፡ መውጣት ካለባቸው ጊዜ በመስጠት፣ ከመንግስታቸው ጋር በመነጋገር በዘዴ ነገሩን መከዎን እየተቻለ አንድ ሀገርና መንግስት በሰዎች ላይ እንዲህ የጭካኔ ጥግ የሆነን አቋም ይዘው መንቀሳቀሳቸው ፍጹም ኢ-ሰብአዊነት ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን እንዲህ ያለ አስከፊ ጊዜ የለም፣ እውነቱን ለመናገር ለአገዛዙ ሰዎች የነበረኝ ጭላንጭል ተስፋም አፈር ተደፍቶባታል፣ እንዲህ ግልጽ የሆነ ጭፍጨፋ እየደረሰብን እንኳ በድፍረት ለመናገር አልፈለጉም፡፡ ስለ ኢትዮጵያውያን መገደል ለማውራት ሲፈልጉ ሌላ ሀገር ይጠቅሱና እነሱም እኮ እየተገደሉ ነው ይላሉ፣ ወገን ከምንለው የማህበረሰባችን አካል ይሄን መስማቱ ከጥቃቱ ይበልጥ ያማል፡፡
ለምሳሌ ኢቲቪ ስለ ጉዳዩ ሲያወራ ህገ ወጥ ሊባል የሚችል ድርጊት ተፈጽሟል በማለት ነው፡፡ ተመልከቱ! እንዴት ያለ ባዕድነት ነው? ኢትዮጵያውያን በድህነትም ውስጥ እንኳ ለክብራችን የመሞት ባህሪ አለን፣ ይሄ ከቀደሙት አንጡራ ኢትዮጵያውያን የወረስነውና ዛሬም ያለን ሀብታችን ነው፡፡
ትናንት ፍየል ጠባቂ የነበረ በረኸኛ ይህን ክብራችንን ገፍፎ እንደውሻ ቀጥቅጦ ስርቻ ሲጥለን ያልተቆጣ መንግስት ኢትዮጵያዊ ነው? ከዜጎቹ የወጣና ለህዝቡ የቆመ እውነተኛ መንግስት ከዚህ የበለጠ የሚቆጣበት ጉዳይ ከወዴት ይመጣል? እውነተኛ መንግስት ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሳውዲ ካምፓኒዎችን በሰአታት ውስጥ ማባረር፣ ኤምባሲውን ዘግቶ አምባሳደሩን ማሰናበትን የመሳሰሉ ውሳኔዎችን ያሳልፉ ነበር፡፡ የሆነው ግን በተቃራኒው ነው፣ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ሊበላሽ ይችላል ብሎ እኛ ድምጻችን እንዳናሰማ ደበደበን፣ አፈነን፡፡ በግልጽ እንደሚታየው የጥቅም ትስስሩ ነው አፋቸውን ያዘጋቸው፣ ይህች ጥቅማቸው እንዳትቋረጥ በዜጎች ህይዎት መደራደርን መርጠዋል፡፡
ስነ ልቦናቸው የተቃወሰ በመሆኑና ተራ ስስታሞች በመሆናቸው እንጂ ኢንቨስትመንትም ሆነ ዲፕሎማሲ ግብአትነታቸው ለሰው ልጅ ነው፣ እንደ አህያ ሲያፈጋ ከርሞ ሬሳቸውን ለላከ መንግስት እንዴት ተመጣጣኝ ምላሽ ለመመለስ ይገዳል?እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ታሪካዊትና ለአፍሪካ የነጻነትና የኩራት ተምሳሌት የሆነች ሀገርን እየመሩ እንዴት ትናንት የነዳጅ ዘይት ባቆማቸው እረኞች ስትዋረድ ዝም ይላሉ?!::
እንዴት!
በዜጎች ህይወት የተደራደረው አገዛዝ ማለፉ አይቀርም፣ ለዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ ታሪክ ለመጥቀስ ብዙ ርቀት መሄድ አያስፈልግኝም፡፡ የቅርብ የሰሜን አፍሪካ አምባገነኖች የከፋ ፍጻሜ አለና፡፡ ኢትዮጵያውያን ፍቅርም ጸብም እናውቃለን፣ ሳውዲዎችም የፈጸሙትን ግፍ ማወራረዳቸው አይቀርም፡፡ በዚህ ክፉ ጊዜ ስለሰብአዊ መብት ቆመናል የሚሉ አለም አቀፍ ተቋማት ዝምታን መምረጣቸው እውነተኝነታቸውን ለመመርመር ጥሩ እድል ይሰጠናል፡፡
መንግስት ቢኖረን ኖሮ ይሄ ሁሉ ውርደት ይፈጸምብን ነበር ብየ አላስብም፡፡ በዚህ ሰአት ርዕሰ-መንግስት ብሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ድርጅት እንደመሆኑ፣ ወደየትኛውም ሀገር የሚደረገውን ጉዞ አቋርጨ ዜጎቸን ማስወጣትን አስቀድም ነበር፡፡ ያሄ ጥቂት ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ሊያመጣብን ቢችልም ከከፋው የዜጎች ስቃይ ጋር ግን በአንድ ሚዛን ላይ አይቀመጥም፡፡ የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ኮሚሽን የሚባል ድርጅት አለ፡፡ በዜጎቻችን ላይ ጎርፍና ድርቅ ሲመጣ ብቻ ነው የሚንቀሳቀሰው? ይሄም ሰው ሰራሽ አደጋ ነው ሙሉ ሀይሉን ወደዚህ አዙሮ ሊንቀሳቀስ ይገባው ነበር፡፡
እርግጥ ነው ባቀድነው መሰረት ሰላማዊ ሰልፉ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡ ጩኸቱ ግን ይቀጥላል… ባለን አቅም ሁሉ አፈናውንም፣ ወከባውንም ተቋቁመን ለዜጎቻችንና ለኢትዮጵያዊነት እንታገላለን፡፡ አገዛዙ ይሄን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያፍን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንድ መልእክት አስተላልፏል፣ ይህን መልእክት እንዲያስትላልፍ ማስገደዳችንም ለኛ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ የሳውዲ መንግስት ያሻውን ያደርግ ዘንድ የፈቀድኩት እኔ ነኝ፣ በመሆኑም እሱን በመቃወም ግንኙነቴን አታበላሹ ብሎ እርምጃ በመውሰዱ ህዝቡ የነገሩ ቁልፍ የት እንዳለ፣ የአጥቂወቹ በራስ መተማመን ምን ላይ እንደቆመ በጠራ ሁኔታ ለመመልከት እንዲችል ሆኗል፡፡
ይሄ ሁሉ ነገር እየተፈጸመ የተስተዋለ አንድ ነገር አለ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ እውነተኛ ማንነታቸው፣ እውነተኛ በአገዛዙ ውስጥ ያላቸውን ቦታ ያሳየን ክስተት ነው፡፡ እንደሚታወቀው እሳቸው በኢህአዲግ እንጂ በኢትዮጵያ ህዝብ የተመረጡ አይደሉም፡፡ ኢህአዲግ የሚናገረው ከሌለ እርሳቸው የሚሉት አይኖርም፡፡ እንደ አንድ ሀገርና ህዝብ መሪ ግን የመኮነንም ሆነ የማጽናናት ቃል ይጠበቅባቸው ነበር፡፡
ባሉበት ቦታ ያስቀመጣቸው ህወሀት ነው፤ ድርጅቱ ደግሞ ይሄን አቋም አልወሰደም፡፡ ስለዚህ እንደሚቆጣቸው ስለሚያውቁ ዝምታን መረጡ፣ ቸልታንም አስበለጡ፡፡ በሀገርም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ከዚህ በላይ ሽንፈት ያለ አይመስለኝም፡፡
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር

የግንቦት7 እና አክራሪ የእስልምና ሀይሎች በኢህአዴግ አባላት ስም ፓርላማውን በመቆጣጠር ኢህአዴግን ሊጎዱት ይችላል ሲሉ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ተናገሩ

የግንቦት7 እና አክራሪ የእስልምና ሀይሎች በኢህአዴግ አባላት ስም ፓርላማውን በመቆጣጠር ኢህአዴግን ሊጎዱት ይችላል ሲሉ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ተናገሩ
untitled
ህዳር ፲፯(አስራ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ይህን የተናገሩት ” በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመንግስት ቀጣዩ የምርጫ ፈተና” በሚል ርእስ ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ባቀረቡት ጽሁፍ ነው።
ኢሳት የሚኒስትሩን ሙሉ ንግግር የያዘ ሰነድ የደረሰው ሲሆን፣ በሰነዱ ግርጌ ላይ ” ለመደበኛ አባላት የማይነገር፣ ለከፍተኛ አመራሮች ብቻ” የሚል ተጽፎበት ይታያል። በዚህ ርእስ ስር ደግሞ ” ቀጣዩ የምክር ቤት አባላት ምርጫ የግንቦት ሰባት እና አክራሪ እስልምና ሀይሎችን የሚያስቀጥሉ አባላት ወንበሩ በኢህአዴግ አባላት ስም ሊነጠቅ ይችላል። ” ብሎአል። ሚኒስትሩ ለዚህ አስተሳሰባቸው የምርጫ 97ትን ሁኔታ እንደማጠቃሻ ተጠቅመዋል። ” የ97 የቅንጅት አሸናፊት አካሄድ ስልት ማለትም የተቃዋሚ አባላት ሁነው በህቡእ ተደራጅተው በኢህአዴግ የአባላትን ካርድ ሙሉ በሙሉ ፓርቲውን ሊጎዱት ይችላሉ” ሲሉ ሚኒስትሩ ጽፈዋል።
ሚኒስትሩ በዚህ ጽሁፋቸው፣ ቅንጅት በ97 ምርጫ ማሸነፉን እንዲሁም የኢህአዴግ አባላት ሆነው ለቅንጅት በውስጥ ይሰሩ የነበሩ ሰዎች እንደነበሩ ጠቅሰዋል። በክርስትና እና በእስልምና ሀይማኖት ሽፋን የሚካሄደውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሚኒሰትሩ በዝርዝር አቅርበዋል።
በክርስትና ሀይማኖት በኩል ” መንግስት በሃይማኖት አባቶች ሹመት ላይ እጁን ያስገባል፤ የዋልድባ ገዳም ተደፈረ፤ አልፎ አልፎ በአጋጣሚ ቤተክርስታያን ባለበት አካባቢ ከድርቅ ጋር ተያይዞ በሚነሳ ቃጠሎ ሆነ ተብሎ እንደተደረገ ማስወራት፤ ይህን የሚያግዝ የውጭ ሚዲያ መኖር ኢሳት በቀዳሚኒት ፣ የደርግ ስርዓት ደጋፊዎች የሆኑት ቪኦኤ በቀጣይነተወ የሚያራግቡት አካሄደ ጉዳዩን ትኩረት እንዲያገኝ ” ማድረጉን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የሙስሊሙ እንቅስቃሴንም በተመለከተ ሚኒሰትሩ ሲገልጹ” ከቅንጅት እስከ ህብረት፣ ከቪኦኤ እስከ ቲቪ አፍሪካ፣ ከጀርመን ድምጽ እስከ ቢላል ሬዲዮ፣ ከጅሃዳዊ ሀረካት እስከ ግንቦት ሰባት፣ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዓለም አቀፍ እስከ መድረክ እስከ ስደተኛው ሲኖዶስ ያሉ ሀይሎች በተናጠልና በህብረት” ተሳትፈውበታል ብለዋል።
የሙስሊሙ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ፍጥነት በመዳከም ሂደት ውስጥ የገባው በቡድኑ ቀንደኛ መሪዎች ላይ ህጋዊ ስርአቱን ተከትሎ የእስራት እርምጃ ከተወሰደ በሁዋላ ነው ብለዋል።
በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውለው አድረው እየተጋለጡና እየተዳከሙ መሄዳቸው ባይቀርም ባለፉት ሁለት ዓመታት ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን በሀይል ለመፈታተን ከሞከሩት የሁከት ሀይሎች ዋነኞቹ ነበሩ ማለት ይቻላል ብለዋል ሚኒሰትሩ።
“በሃይማኖት ስም የሚካሄደውን ንግድ ውጤታማ እንዲሆን በማድረግ ረገድ የድህነት መንሰራፋትና የመልካም አስተዳደር እጦት ወይም ጉድለት ተጠቃሽ ናቸው” የሚሉት ዶ/ር ሽፈራው በተለይ ከድህነትና ኋላቀርነት መውጫውን ትክክለኛ መንገድ የሚያመላክት መሪ ድርጅት በሌለበት ፣ በሃይማኖት ሽፋን የሚነግዱ የፖለቲካ ሀይሎች አንዱን በሌላው ላይ ማነሳሳት የፅድቅ መንገድ እንደሆነ አስመስለው በማቅረብ ዜጐችን ወደጥፋት ይመራሉ” ብለዋል።
መሪ ድርጅቱም ኖሮ በአመራርም ሆነ በአባላት ደረጃ በአንድ በኩል ከፀረ ድህነትና ኋላቀርነት ትግሉ ላይ ጽናትና ብቃት ያለው አመራር መስጠት ካልተቻለ፣ በሌላ በኩል ደግም የፓርቲና የመንግስት መሪዎች ስራቸውን ከየትኛውም ሃይማኖት ገለልተኛ በሆነ መንገድና ሁሉን ሃይማኖቶች እኩል በሚያስተናግድ አግባብ ካልፈፀሙ ይኸው ችግር ተባብሶ መቀጠሉ አይቀርም ሲሉ ዶ/ር ሽፈራው አስጠንቅቀዋል።
አሁንም ድህነትና ኋላቀርነት በመኖሩ፣ በፓርቲና በመንግስት አመራራችን የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች በመኖራቸውና የእምነት ጉዳይ ለሚዛናዊ አስተሳሰብ ያለው ተጋላጭነት ዝቅተኛ በመሆኑ አልፎ አልፎ የተካረረ ፍጥጫ እያጋጠመ መሆኑንም ሚኒስተሩ በጽሁፋቸው አብራርተዋል።
ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ለኢህአዴግ ባለስልጣናት ያቀረቡትን ሙሉ ጽሁፍ በድረገጻችን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመንግስት ቀጣዩ የምርጫ ፈተና
ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም
ህዳር 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ
1. በክርስትና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴና ቀጣይ አዝማሚያዎቹ፣
ü በክርስትና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው እንቅስቃሴ በዋነኛነት ኢትዮጵያ የክርስትና ሃይማኖት የበላይነት ሊኖርባት ይገባል በሚል ኋላቀርና ዘመን የሻረው አስተሳሰብና ሀይል የሚመራ ነው፡፡
ü በዚህ መሠረት ይህ ኋላቀር ሀይል መነሻና መድረሻውን የክርስትና ሃይማይማኖትን የበላይነት አድርጐ ይህን ሊያረጋግጡልኝ ይችላሉ የሚላቸውን መፈክሮች ጐላ አድርጐ ያሰማል፡፡
ü በዚህ ረገድ “ኢትዮጵያ የክርስትና ደሴት ነች”፣ “አንድ አገር አንድ ሃይማኖት” የሚሉ መፈክሮቹ የአስተሳሰቡን ጭብጥ የሚያሳዩ ናቸው፡፡
ü በዚህ ሀይል አስተሳሰብ መሠረት አገራችን በርካታ ሃይማኖቶችን ያስተናገደችና በማስተናገድ ላይ የምትገኝ አገር መሆኗ ቀርቶ የክርስቲያን ደሴት ብቻ ተደርጋ ትቀርባለች፡፡
ü እራሱ አንድ አገር አንድ ሃይማኖት የሚለው አስተሳሰብም በተመሳሳይ መልኩ በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሃይማኖት ብቻ እንዳለ ወይም ሊኖር እንደሚገባ የሚሰብክ ኋላቀር የፀረ እኩልነት አስተሳሰብ ነው፡፡
ü እነዚህ ሀይሎች አንደንዶቹ የሃይማኖት ጉዳይ ህብረተሰቡን በቀላሉ ሊያደናግርልን ይችላል ብለው የሚያምኑ ተቃዋሚ የፖለቲካ ሀይሎች ሲሆኑ
ü ከፊሎቹ ደግሞ ከሃይማኖት አኳያ የኦርቶዶክስ እምነት መንግስታዊ ሃይማኖት መሆኑ ቀርቶ ከሌሎች ሃይማኖቶች በእኩልነት የሚታይና የሚከበር መሆኑን ያልተቀበሉ በትላንቱ ዓለም የሚኖሩ ሀይሎች ናቸው፡፡
ü የፖለቲካ ሀይሎቹ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የክርስትና ሀይማኖትን መጠለያ በማድረግ የተለያዩ ቀስቃሽና ስሜትን የሚኮረኩሩ የፈጠራ አጀንዳዎችን ለማራገብ የሚሞክሩ ናቸው፡፡
ለምሳሌ፡- መንግስት በሃይማኖት አባቶች ሹመት ላይ እጁን ያስገባል፤ የዋልድባ ገዳም ተደፈረ፤ አልፎ አልፎ በአጋጣሚ ቤተክርስታያን ባለበት አካባቢ ከድርቅ ጋር ተያይዞ በሚነሳ ቃጠሎ ሆነ ተብሎ እንደተደረገ ማስወራት፤ ይህን የሚያግዝ የውጭ ሚዲያ መኖር ኢሳት በቀዳሚኒት እና ቪኦኤ /የደርግ ስርዓት ደጋፊዎች/ የሚያራግቡት አካሄደ ጉዳዩን ትኩረት እንዲያገኝ አድርግውታል፡፡ ፤
ü በራሳቸው ፖለቲካዊ መስፈርት የቤተ ክርስቲያኒቱን መሪዎችና ሀላፊዎች መሾምና መሻር የሚፈልጉ ተቃዋሚ ሀይሎች በተለይም ደግሞ በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚ ሀይሎች የራሳቸውን ሰው አዘጋጅተው ለማስመረጥ ብዙ ጥረት አድርገዋል፡፡
ü በዛሬማ ሸለቆ አካባቢ የስኳር ልማቱ የሚካሄደው በጣም ዝቅተኛና ቆላ ላይ ሲሆን፤ የዋልድባ ገዳም መሬት ደግም በደጋና ወይናደጋ ቦታዎች ላይ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ በገዳሙና በስኳር ማሳው መካከል ያለውን ከፍተኛ የመልክዓምድር ልዩነት በቅርቡ ለማያውቁ የክርስትና ምዕመናን ሁሉ ገዳሙ ተደፈረ የሚለው ቃል እልህና የቁጣ ስሜት ይፈጥርባቸዋል ብሎ በማመን ሰፊ ዘመቻ ሲካሄድበት ከርሟል፡፡
ü የዚህ ዘመቻ ፊታውራሪዎች በአሜሪካን ድምጽ ሬዲዮ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ የቀድሞ የኢህአፓዎችና የቅንጅት ትርፍራፊዎች ናቸው፡፡
ü በአንድ ወቅት በምዕራብ ኢትዮጵያ ጅማ አካባቢ በኻዋርጃ ስም የሚታወቁ አክራሪዎች በክርስቲያኖች ላይ ያደረሱትን ግድያ መጠጊያ በማድረግ “ክርስቲያኖች እየተጨፈጨፉ ነው ስለዚህም አፀፋው ሊመለስ ይገባዋል” በሚል ቅኝት መንቀሳቀስ ጀምረው ነበር፡፡
ü አልፎ አልፎ እንደምናየውም ከድርቅ ጋር በተያያዘ ምክንያት በሚነሳ ቃጠሎ አንድ ቤተ ክርስትያን ወይም ገዳም ባለበት አካባቢ በአጋጣሚ ቃጠሎ ከተነሳ ይህንኑ ሆን ተብሎና በክርስትና ላይ ጥቃት ለመፈፀም ሲባል እንደተደረገ አስመስሎ የማቅረብ፣
ü እንዲሁም ለቤተ ክርስትያን መስሪያ ተብሎ ባልተሰጠ ቦታ የቤተክርስትያን ግንባታ መጀመርና ህገ ወጥ ግንባታ እንዲቆም ሲጠየቅ በክርስትና ሃይማኖት ላይ ተዘመተ ብሎ የእኩልነት ጥያቄ ማንሳት አዘውትረው የሚጠቀሙባቸው ስልቶች ናቸው፡፡
ü ከመንግስትና ድርጅት ሀላፊዎች ውጭ ባሉ የተሳሳተ አስተሳሰብ ባላቸው ዜጐች የሚራመዱት እነዚህ ኋላቀርና ፀረ እኩልነት አስተሳሰቦች እንደተጠበቁ ሆኖ ሃይማኖታዊ አዝማሚያ ባልተለያቸውና በመንግስታዊ ሀፊነትና በእምነታቸው መካከል ያለውን ልዩነት በውል መገንዘብ የተሳናቸው ሀላፊዎች ደግሞ የየራሳቸውን ስህተት ሲሰሩ ማስተዋል የተለመደ ነው፡፡
ü በአጠቃላይ ሲታይ ወቅታዊና ለፖለቲካ ንግድ የሚያመች እንዲህ አይነት አጀንዳ ሲፈጠር አጋጣሚውን ለመጠቀም ምን ጊዜም ወደ ኋላ አይሉም፡፡
ü በክርስትና ስምና ሽፋን የሚነግዱ ፖለቲከኞች አነዚህን የመሳሰሉ መሠረተ ቢስ አጀንዳዎችን በመቅረጽና በማራገብ ክርስትና ሃይማኖት ተከብሮና ተቻችሎ በሚኖርባት አዲሲቷ ኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ክብርና ሞገሱን የተገፈፈ አስመስለው ያቀርባሉ፡፡
ü ለእምነቱ ክብርና ሞገስ የሌላቸው ራሳቸው በሃይማኖቱ ሽፋን የፖለቲካ ንግድ የሚያካሂዱት
ü ሀይሎች መሆናቸውን ደብቀው መንግስትና ስርዓቱን በመሰረተ ቢስ ወንጀል ይከሳሉ፡፡
2. በእስልምና ሀይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴና ቀጣይ አዝማሚያዎቹ፤
በክርስትና ሀይማኖት ሽፋን ከሚካሄደው እንቅስቃሴ ባልተናነሰ ይልቁንም አልፎ አልፎ በራሱ ባህሪ ከዚያም በከፋ ሁኔታ በእስልምና ሀይማኖት ስም ሚካሄድ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚታይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ü እንቅስቃሴው ውስጥ ውስጡን ሲካሄድ ቆይቶ ከቅርብ አመታት ወዲህ አክራሪነትን ለመታገል እንቅስቃሴ ሲጀመር ነው በግልጽ ፀረ ህገመንግስታዊ መልክ ይዞ መታየት የጀመረው፡፡
ü ከ20 ዓመታት በፊት በጨቋኙ ስርዓት ይደርስባቸው ከነበረው ግፍና በደል በዲሞክራሲያዊ ትግል ተላቀው የሃይማኖታቸውን እኩልነት ባስከበሩባት አዲሲቷ ኢትዮጵያ የሃይማኖት የበላይነትን በማስፈን ቅኝትና ከሌሎች ሃይማኖት ተከታይ ወንድሞቻቸው ጋር በመቻቻልና በእኩልነት የመኖር እድልን በሚዘጋ ሁኔታ የሚንቀሳቀሱ አክራሪ ዝንባሌዎች መታየት ጀምረዋል፡፡
ü እነዚህ አክራሪ እንቅስቃሴዎች በዋኛነት ከሰሜን አፍሪካና ከመካከለኛው ምስራቅ አገሮች አክራሪ ሀይሎች የመነጩ፤ በአንድ በኩል የእስልምናን የበላይነት በአካባያችን ለማስፈን የሚካሄደው እቅድ ማስፈጸሚያ፤ በሌላ በኩል በሃይማኖቱ በሚነግዱ ግለሰቦችና ቡድኖች በሃገሪቱ የተፈጠረውን የእኩልነት ስርዓት በመፃረር የበላይነትን ለማሰፈን የሚካሄደው እንቅስቃሴ መገለጫዎች ናቸው፡፡
ü በእነዚህ አክራሪ አስተሳሰቦች የሚመሩ ጽንፈኞች መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ በመገንዘብ በሀይማኖት ሽፋን የዜጐችን ሰብዓዊ መብቶች የሚረግጡ በርካታ አስነዋሪ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡ ነባር መስጊዶችን አቃጥለዋል፣ ነባርና ኢትዮጵያዊ መሠረት አላቸው የሚሏቸውን የሃይማኖት መጽሃፍት አቃጥለዋል፡፡
ü ይህን በመቃወም ለማስቆም የሞከሩ ዜጐችና የሃይማኖት ትምህርት ቤቶችንና መስጊዶችን የአመራር ቦታዎች በጉልበት ነጥቀዋል፣ ይህን የተቃወሙ ዜጐችን ሁሉ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅለዋል፡፡ ይህ ከሞላ ጐደል አክራሪዎቹ በደረሱባቸው ቦታዎች ሁሉ የተካሄደ ነው፡፡
ü የመጀመሪያው ሙከራ ያነጣጠረው በኢትዮጵያ ያሉ ብዙዎቹ ነባር ሃይማኖቶች ሁሉ መሠረታቸው መካከለኛው ምስራቅ መሆኑ እየታወቀ መንግስት አህባሽ የሚባል ሃይማኖት ከውጭ አመጣብን የሚለው መከራከሪያ ውሃ የማይቋጥር ቢሆንም መንግስት ይህኛውን ወይም ያኛውን ሃይማኖት ከዚህኛው ወይም ከዚያኛው አገር በብድር የሚያመጣበት ምክንያትም ሆነ ሎጂክ አልነበረውም፣ የለውምም፡፡ ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ በውጭ ገንዘብ ድጐማ የሚንቀሳቀሱት እነዚህ ሀይሎች ባላቸው አቅመ ሁሉ በመታገዝ
ü መንግስት አህባሽ የሚባል የውጭ እምነት አምጥቶ /በሃጂ አብዲላሂ መምህርነት የተስፋፋውን/ ሙስሊሙን ህብረተሰብ ሊጭንበት እየተንቀሳቀሰ ነው የሚል መሠረተ ቢስ ጉዳዮችን እያመጡ መንግስት በሃይማኖታችን ጉዳይ ጣልቃ ገባ ብለው ሲከሱ ሰንብተዋል፡፡ ቀላል ያልሆነ የህብረተሰብ ክፍል በተለይም ወጣት አደናግረዋል፡፡
ü የአስተምህሮ መሰረታቸው ብቻ ሳይሆን የየፋይናንስ ምንጫቸውም የውጭ ሀይል ለዚያውም በጣም በቅርቡ የምናውቀው መካከለኛው ምስራቅ በሆነበት ሁኔታ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ለመክሰስ የሚያስችላቸው ሞራላዊ ብቃት እንዴት ሊጐናፀፉ ቻሉ?
ü ገንዘብን በመጠቀም ነባሩን የሱፊ እምነት ለመገለባበጥ ያደረጉት ጥረትና በተወሰነ ደረጃ ያገኙት ውጤት የልብ ልብ ስለሰጣቸው ብቻ ራሳቸውን ምሉዕ በኩልሄ አገር በቀል ሌላውን ደግሞ መጤ ለማስመሰል እስከመሞከር ደርሰዋል፡፡
ü ደግነቱ በዚህች ዴሞክራሲያዊት ምድር አገር በቀል መሆን ወይም አለመሆን እምነትን ለማስተማር ቦታ የሌለው መሆኑ እንጅ አገር በቀል ያልሆነ እምነት ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ቦታ ሊኖረው አይገባም ቢባል ማን ይቀራል፤
ü ነገር ግን አዲሱቱ ኢትዮጵያ የሃይማኖት መለኪያዋ የዜጐች ምርጫ መሆን አለመሆኑ ነው፡፡ መሠረቱ ኢትዮጵያዊ፣ አፍሪካዊ ወይም የሌላ ዓለም መሆን አለመሆኑ አይደለምና ከመካከለኛው ምስራቅ አንዳንድ አገሮች በቅርቡ የገቡትን ሌሎች አስተምህሮዎች ያልከለከለችውን ያክል አህባሽም ሆነ ሌላ አስተምህሮ የዜጐች ምርጫ እስከሆነ ድረስ እንዳይገባ የምትከለክልበት አንዳችም ምክንያት አልነበረም፡፡
ü በዚህ ጉዳይ ላይ መንግስት ጉዳዩን አቃሎ በመመልከት ሰፊና አጥጋቢ ማብራሪያ ባለመስጠቱ ግን አክራሪዎቹ ፈቃጅና ከልካይ ሆነው አህባሽ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት የለበትም የሚል አስተምህሯቸው የብዙዎቹን ወጣት ሙስሊሞች አዕምሮ እንዲበርዝ እድል አገኘ፡፡
ü ሌላው መጠቀሚያ ሊያደርጉት የሞከሩት እና የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ ነበር፡፡
ü መንግስት ከት/ቤቱ የፈለገው ሃይማኖትና ፖለቲካ የተነጣጠሉ መሆናቸውን በመቀበል ከማናቸውም አይነት የፖለቲካ አስተምህሮ በፀዳ አኳኋን ተግባሩን እንዲፈጽም ብቻ ነው፡፡
ü ተቋሙ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን አክብሮ ከመንቀሳቀስ ይልቅ ለማንም ተጠያቂነት በሌላቸው ወገኖች እየተመራ ከሃይማኖታዊ ጉዳዮች በራቁና ለአክራሪዎች በተመቹ አጀንዳዎች ተጠምዶ ጊዜውን ሲያሳልፍ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ይህንኑ መነሻ በማድረግ ድርጅቱ በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሚመራና ተጠያቂነት ያለበት ተቋም እንዲሆን ተደርጓል፡፡
ü የሙስሊሙ ማህበረሰብ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤቶችን እንደ አዲስ መርጦ ማደራጀት እንደሚፈልግ ግልጽ ነበር – ከየአቅጣጫው በሚነሱ ጥያቄዎች፡፡ በዚህመ ሠረት ምክር ቤቶቹ በአፋጣኝ በሚካሄድ ምርጫ እንዲዋቀሩ ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡ ይህ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ህገ መንግስታዊ መብት በመሆኑ መንግስት ይህንኑ ተቀብሎ፤ ምክር ቤቶቹ ለዚህ የህዝብ ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ እንዲሰጡ ከእርሱ የሚጠበቀውን ምክር ለግሷል፡፡ ምክር ቤቶቹ በአፋጣኝ በሚካሄድ ምርጫ እንዲዋቀሩ የማድረጉን ዴሞክራሲይዊ አሰራርም ደግፏል፡፡
ü ልክ መንግስት ጣልቃ እንደገባና ያለሙስሊሙ ህዝብ ፍላጐት መራጮች በላዩ ላይ እንደተጫኑበት በማስመሰል ሲቀሰቅሱ ከቆዩ በኋላ ከዚህ ታላቅ የዴሞክራሲ ተግባር አቋርጠው ወጡ፡፡
ü በውጤቱም ህዝቡ ከአክራሪነት የፀዱ የሚላቸውን ሰዎች መምረጡን አረጋግጧል፡፡ ነገር ግን ይህ ምርጫ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ሆኖ መካሄዱ ያንገሸገሻቸው አክራሪ ሀይሎች ገና ከምርጫው ዋዜማ ጀምሮ ይህንኑ ለመቃወም ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡
ü ድምፃችን ይሰማ በማለት አርብ አርብ በአንዋር መስጊድና አልፎ አልፎም በሌሎች መስጊዶች ከመንግስት ጋር በከፍተኛ ደረጃ ሲፋጠጡ ከርመዋል፡፡
ü ከውጭ ሚዲያዎች ጋር በተቀናጀ አኳኋን በእስልምና ሃይማኖት ላይ ጥቃት የደረሰ በማስመሰል ለማነሳሳት ብዙ ጥረት አድርገዋል፡፡
ü በፖሊስና ፀጥታ አስከባሪ ሀይሎች ትዕግስት ወደ መካረርና ግጭት እንዳይመራ ተደረገ እንጂ ከሞላ ጐደል ለአንድ ዓመት ተኩል ያክል አክራሪዎቹ መንግስትን ወደ ግጭትና ደም መፋሰስ ለማስገባት ያላደረጉት ጥረት አልነበረም፡፡
ü በአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ ስብሰባ ወቅት ያልተፈቀደ የሚሊዮን ሰዎች ሰልፍ ለማድረግና የአዲስ አበባን መንገዶች በመዘጋጋት አደጋ ለመፍጠር ሙከራ አድርገው ነበር፡፡ እንደዚሁም ባለፈው ክረምት አንድ ሌሊት ላይ ከቢላል መስጊድ በመነሳት አዲስ አበባ ከተማን ለማተራመስ ሞክረው ነበር፡፡
ü እራሱን ጀሃዳዊ ሃረካት በሚል ስያሜ ለማስተዋወቅ ጥረት ያደረግ ከነበረ የአሸባሪዎች ድርጅት ጋር በመቀናት የአንዋር መስጊዱንም ሆነ ሌሎች መሰል የነውጥ ሙከራዎች በሽፋንነት መጠቀም መርጠው ነበር፡፡
ü ይህም ሆኖ መንግስት ረጀም ጊዜ ወስዶ ባካሄደው ጥናትና በሰበሰባቸው ማስረጃዎች ላይ በመመስረት በቡድኑ ቀንደኛ መሪዎች ላይ ህጋዊ ስርዓቱን ተከትሎ የእስራት እርምጃ ወስዷል፡፡
ü ከዚህ ጊዜ በኋላ ነው ንቅናቄው በከፍተኛ ፍጥነት በመዳከም ሂደት ውስጥ የገባው፡፡
ü በሌላ በኩል ደግም ሃይማኖትን በሽፋንነት ለመጠቀም የሞከረው ይኸው ሀይል በተለይ በውጭ ከሚገኙ ደጋፊዎቹ ጋር በመቀናጀት አሉ የተባሉትን ፀረ ኢትዮጵያ ሚዲያዎች ከመጠቀሙም ባሻገር ከግንቦት 7 እስክ ስደተኛው ሲኖዶስ ባለ የትምክህት ሀይሎች ለመደገፍና ብርቱ ጥረት አድርጓል፡፡ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚል ፈሊጥ እርስ በእርስ ተሳስረውና ተደጋግፈው ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡
ü በማጠቃለል ሲታይ በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውለው አድረው እየተጋለጡና እየተዳከሙ መሄዳቸው ባይቀርም ባለፉት ሁለት ዓመታት ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን በሀይል ለመፈታተን ከሞከሩት የሁከት ሀይሎች ዋነኞቹ ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡
ü በሀይማኖት ሽፋን የሚካሄደው እንቅስቃሴ በጽንፈኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጥታ ከተደረገው የነውጥ ማነሳሰት በእጅጉ የላቀ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
ü ምንም እንኳን ነውጠኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከ97 ውድቀታቸው በኋላ በተመሳሳይ ደረጃ ወደሚገለጽ የጐዳና ላይ ነውጥ ለማምራት በከፍተኛ ደረጃ እየተቸገሩ ቢሆኑም በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደውን እንቅስቃሴ በመደገፍና ነዳጅ በማርከፍከፍ ለማቀጣጠል ያደረጉትን ጥረት ጨምሮ የወቅቱ ፀረ ህገ መንግስታዊ ንቅናቄ መገለጫ የሃይማኖት ልባስ ይዞ የሚካሄደው እንቅስቃሴ ነው ማለት ይቻላል፡፡
ü በሃይማኖት ሽፋን ለመንቀሳቀስ የተመረጠበትን ዋነኛና ደጋፊ ምክንያቶች መለየትና ከዚህም አኳያ መሠረታዊ መፍትሄ ማበጀት ይገባል፡፡
3. ሃይማኖትን በሽፋንነት ለመጠቀም የተመረጠባቸው ምክንያቶች፣
ü ሃይማኖትን በሽፋንነት በመጠቀም የፖለቲካ እንቅስቃሴውን ማካሄድ የመረጡት ሀይሎች የተለያየ መጠሪያ ያላቸው ነገር ግን በመሰረቱ የትምክህት ወይም የጠባብነት መፈክሮችን አንግበው ለመፋለም የሞከሩ የፖለቲካ ሀይሎች እንደሆኑ ይታወቃል፡፡
ü ከቅንጅት እስከ ህብረት፣ ከቪኦኤ እስከ ቲቪ አፍሪካ፣ ከጀርመን ድምጽ እስከ ቢላል ሬዲዮ፣ ከጀሃዳዊ ሃረካት እስከ ግንቦት ሰባት፣ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዓለም አቀፍ እስከ መድረክ እስከ ስደተኛው ሲኖዶስ ወዘተ ያሉ ሀይሎች በተናጠልና በህብረት የተሳተፉበት ነው፡፡
ü ሁሉም ያነገቡትን ዓላማ በተለያዩ ፀረ ህገ መንግስታዊ ስልቶች በመታገዝ ለማስፈፀም ሞክረው የከሸፈባቸው ሀይሎች ናቸው፡፡
ü እነዚህ አላማቸውን በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በማራመድ ለስኬት መብቃት ያቃታቸው ድርጅቶችና ሀይሎች ከፍ ሲል እንደተመለከትነው የፖለቲካ ዓላማቸውን በሃይማኖት ሽፋን ማራመድ የመረጡት ይህ ስልት ምን ዓይነት እድል ቢሰጣቸው ነው ብሎ ጥያቄ ማንሳትና ጉዳዩን መመርመር በዚሁ ዙሪያ በቀጣይነት መካሄድ ያለበትን ትግል በትክክል ለመወሰን አስፈላጊ ነው፡፡
ü በድሃና ኋላቀር ህብረተሰብ ውስጥ በእምነት ጉዳይ ዜጐችን ብዥታ ውሰጥ መክተት ይህን ስልት ለመረጡ ወገኖች በቀላሉ ያለመጋለጥ እድል ያጐናጽፈናል፡፡ ከዚህም አለፍ ሲል ለድል ያበቃናል ብለው ማመናቸው ነው፡፡
ü የእምነት ጉዳይ ለሚዛናዊ አስተሳሰብ ያለው ተጋላጭነት በተነፃፃሪ አነስተኛ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
ü በሃይማኖት ለሚመራ ሰው ወደ ማንኛውም ድርጊት ለማምራት ማመን ብቻውን በቂ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
ü “በእምነትህ የመጣ ነው” ተብሎ የቀረበለትን ጉዳይ ያለማንገራገር ተቀብሎ ወደ ድርጊት ማምራት በብዙ የሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ የሚታይ ክስተት ነው፡፡
ü ስለሆነም ይህ አካሄድ በሃይማኖታቸው ቀናዒ የሆኑ ሰዎች በሃይማኖት ሽፋን የሚራመዱ የፖለቲካ አጀንዳዎች ሰለባ ለማድረግ የተሻለ እድል ይፈጥርልናል በማለት ነው፡፡
ü በበለፀገው ዓለምም በአሸባሪነትም ሆነ በፀረ አሸባሪነት ጐራ ተሰልፈው የሚፋለሙ ሀይሎች ሃይማኖታዊ ጥሪ በማስተላለፍ የፖለቲካ ዓላማቸውን በሃይማኖት ግጭት መልክ ሲያስኬዱ ማየት የተለመደ ነው፡፡
ü የትኛውንም ጎራ በመሠረተ ቢስ እምነት ነክ ውንጀላዎች በቀላሉ በስሜት በማነሳሳት ሌላውን እንዲገጥሙ ማድረግ ይቻላል ተብሎ ይታመናል፡፡
ü በመሆኑም የከሰሩ ፖለቲከኞች ሁሉ ሃይማኖትን በሽፋንነት በመጠቀም መንቀሳቀሳቸው የእምነት ጉዳይ ለሚዛናዊ አስተሳሰብ ያለው ተጋላጭነት በተነፃፃሪ አነስተኛ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
ü በሃይማኖት ስም የሚካሄደውን ንግድ ውጤታማ እንዲሆን በማድረግ ረገድ አጋዥ ሚና የሚጫወቱ ችግሮች ደግሞ ይኖራሉ፡፡ በዚህ ረገድ የድህነት መንሰራፋትና የመልካም አስተዳደር እጦት ወይም ጉድለት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ü በተጨባጭ እንደሚታየው በበለፀገና ሰርቶ የመጠቀም እድል በሰፋበት ማህበረሰብ ውስጥ ለጽንፈኝነት መሠረት የሚሆን ተስፋ መቁረጥ አይገኝም፡፡ ሰርቶ መክበርና ማደግ ስለሚቻል ለተስፋ መቁረጥ ምክንያት የሚሆን ችግር አይኖርም፡፡
ü መልካም አስተዳደር በሰፈነበት ሁኔታ ዜጐችና ህዝቦች በደስታና በስምምነት ይኖራሉ፡፡ በአንፃሩ ድህነትና ኋላቀርነት በተስፋፋበት ህብረተሰብ ውስጥ ተስፋ መቁረጥ ያይላል፡፡ ዜጐች የምድራዊ ኑሯቸውን ከሲኦል ያልተለየ አድርገው በመውሰድ በሃይማኖት ስም ለሚቀርቧቸው ሃሳዊ መሲሆች ሁሉ አመኔታቸውን ሊሰጡ ይገደዳሉ፡፡ ኢትዩጵያ በመጭው ምርጫ ፈተና ይሆንብናል፡፡
ü በተለይ ከድህነትና ኋላቀርነት መውጫውን ትክክለኛ መንገድ የሚያመላክት መሪ ድርጅት በሌለበት በሃይማኖት ሽፋን የሚነግዱ የፖለቲካ ሀይሎች አንዱን በሌላው ላይ ማነሳሳት የፅድቅ መንገድ እንደሆነ አስመስለው በማቅረብ ዜጐችን ወደጥፋት ይመራሉ፡፡
ü መሪ ድርጅቱም ኖሮ በአመራርም ሆነ በአባላት ደረጃ በአንድ በኩል ከፀረ ድህነትና ኋላቀርነት ትግሉ ላይ ጽናትና ብቃት ያለው አመራር መስጠት ካልተቻለ፣ በሌላ በኩል ደግም የፓርቲና የመንግስት መሪዎች ስራቸውን ከየትኛውም ሃይማኖት ገለልተኛ በሆነ መንገድና ሁሉን ሃይማኖቶች እኩል በሚያስተናግድ አግባብ ካልፈፀሙ ይኸው ችግር ተባብሶ መቀጠሉ አይቀርም፡፡
ü ከዚህ አኳያ ሲታይ ድህነትና ኋላቀርነነት እንዲሁም እነዚህን ለማስወገድ የሚያስችል ብቃት ያለው አመራር እጦት የፖለቲካ ጽንፈኝነትና የሃይማኖት አክራሪነት የሚስፋፋባቸው ለም አፈሮች ብቻ ሳይሆኑ በሃይማኖት ሽፋን የሚነግዱ ፖለቲከኞችም እንደመልካም አጋጣሚ የሚመለከቷቸው ናቸው፡፡
ü በመሆኑም እነዚህን ችግሮች በመፍታት በሃይማኖት ሽፋን ለሚነግዱ ፖለቲከኞች መንቀሳቀሻ አድማሱን ማጥበብ እጅግ ተፈላጊ ሆኖ ይገኛል፡
IV. በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደውን የፖለቲካ ንግድ በአስተማማኝ ደረጃ ለማሸነፍ ምን እንስራ?
ü ከፍ ሲል እንደገለጽነው ፈጣንና ህዝብ የሢቀምበት ለውጥና ብዝሃነነትን በአግባባ የማስተናገድ ችሎታተ የያለው ህብረተሰብ በመፈጠሩሪ ምክንያት በሀይማኖት ሽፋንም ሆነ በግላጭ ሲካሄድ የቆየው ጽንፈኛ እንቅስቃሴ የህዝብ ይሁንታን ሊያገኘ ባለመቻሉ ትርጉም ያለው ሁከትና ብጥብጥን ለመቀስቀስ ሳይቻለው ቆይቷል፡፡
ü ይህ መሠረታዊ ሃቅ አንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም ድህነትና ኋላቀርነት በመኖሩ፣ በፓርቲና በመንግስት አመራራችን የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች በመኖራቸውና የእምነት ጉዳይ ለሚዛናዊ አስተሳሰብ ያለው ተጋላጭነት ዝቅተኛ በመሆኑ አልፎ አልፎ የተካረረ ፍጥጫ የሚያጋጥመን ሆኖ ቆይቷል፡፡
ü ይህ ፍጥጫ በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከሞላ ጐደል ሁሉንም ተፋላሚ ሀይሎች በሁለት ጐራ ከፍሎ ያፋጠጠ ሆኖ ከርሟል፡፡
ü ምንም እንኳን ችግሩ ለጊዜውም ቢሆን በመንግስት ታጋሽነትና አርቆ አስተዋይነት እንዲሁም በሰላም ወዳዱ ህዝብ ብርቱ ትግል የከሸፈም ቢሆን ለችግሩ መቀስቀስ ምክንያት የሆኑት ጉዳዮች በሙሉ ዛሬም በተጨባጭ ይገኛሉና ይህንን ታሳቢ ያደረገ የመፍትሄ ሃሳብ ማመላከት ተገቢ ይሆናል፡፡
1. ፀረ- ድህነትና ፀረ-ኋላቀርነት ትግላችንን እናፋፍም፣
ü በድህነት የተጐዳ ህብረተሰብ ሁሌም በምሬት ውስጥ የሚኖርና ከዚህ ችግር የሚያላቅቀው ትክክለኛ አማራጭ ካልቀረበለት በስተቀር በሌሎች ጽንፈኛና መሰረተ ቢስ አማራጮች ሊማለል የሚችል ነው፡፡
ü በተለይ ደግም በምድራዊው ህይወቱ ያላለፈለትን ህዝብ በሰማይ ቤት ያልፍልሃልና ማንኛውንም ጽንፈኛ አቋም ተግባራዊ አድርግ ለሚሉ አይነት ቅስቀሳዎች ተጋላጭ ይሆናል፡፡
ü ኋላቀርነትም እንደዚሁ አንድን ህብረተሰብ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር እድል በመንፈግ ለተስፋ መቁረጥና ጽንፈኝነት ሊዳርገው ይችላል፡፡
ü ምሬቱ የከፋና ተስፍ የቆረጠ ህዝብ ባለበት ሁሉ ጽንፈኝነት ሲስፋፋ የምንመለከተው በዚህ ምክንያት ነው፡፡
ü ይህ አዲስ ግኝት ሳይሆን ድርጅታችን ቀደም ሲል ጀምሮ የተገነዘብነውና ለመፍትሄውም የታገለለት ጉዳይ ነው፡፡
ü ድርጅታችንና በርሱም የሚመራው ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ድህነትና ኋላቀርነት ጽንፈኝነትንና፣ ፀረ እኩልነት የሆኑ የትምክህትና ጠባብነት አዝማሚያዎችን ወዘተ ሊሸከም የሚችል ለም አፈር መሆኑን ታሳቢ በማድረግ በድህነትና ኋላቀርነት ላይ ጦርነት ካወጀ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡
ü ፈጣንና ብዙሃኑ ህዝቦች የሚቀጠሙበትን ልማት አስፋፍቷል፡፡
ü መሠረተ ሰፊና አሳታፊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ገንብቷል፡፡ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቀጣይ ትግል አካሂዶ በመስኩ ከፍተኛ ድሎችን አስመዝግቧል፡፡
ü ይህም በመሆኑ ዛሬ አገራችን ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ በፈጣንና ህዝብ በሚጠቀምበት ዴሞክራሲያዊ የእድገት አቅጣጫ እየገሰገሰች ትገኛለት፡፡
ü እድገታችን ፈጣንና መሰረተ ሰፊ በመሆኑም የህዝቡን ተስፋ አለምልሟል፡፡
ü ዴሞክራሲያችን ብዝሃነትን በማወቅና በማክበር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ በህዝቦች መካከል ፍቅርን መከባበርና መቻቻልን አጐልብቷል፡፡
ü የእርስ በርስ መናቆርና ከዚህም ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችል ተስፋ መቁረጥ መሰረት ተንዷል፡፡ ብዙ አገሮች በቀለም አብዮቶች ሲናጡና ከቀውስ ወደ ቀውስ ሲረማመዱ በአገራችን ሰላምና መረጋጋት እንደሰፈነ የቀጠለው በዚህ ምክንያት ነው፡፡
2. ወጣቱን ከስራ አጥነትና ተስፋ መቁረጥ እንታደግ?
ü አብዛኛውን ጊዜ በስሜት የሚያነሳሱ ጉዳዮች በቀላሉ ተጽዕኖ የሚያሳርፉት በወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ላይ ነው፡፡
ü በተለይ ወጣቱ ለስራ አጥነት፣ ጥራት ለሌለው ትምህርት፣ ከተደራጀ ፖለቲካዊ ተሳትፎ መገለልና ለመልከም አስተዳደር የሚያመች ሁኔታ ባልገጠመው ወቅት ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ አቀራረቦች በደካማ ጐኑ ለመግባት የተሻለ እድል ያገኛሉ፡፡
ü በአገራችን በተለይ ከ97 ዓ/ም ድህረ ምርጫ ቀውስ በመማር የወጣቱን የልማትና የተጠቃሚነት፣ የመልካም አስተዳደርና የተሳትፎ ጥያቄዎች ለመመለስ ጥረት ያደረግነውና የተሳካ ውጤት ያገኘነውም በመሰረቱ ለስራ አጥነትና ለተስፋ መቁረጥ የተጋለጠ ወጣት ሊኖርበት የሚችለውን ተጋላጭነት በማስወገድ ንቁ የአገር ገንቢ ለማድረግ ነው፡፡
ü ወጣቱ ያለበትን የመነሻ ካፒታል ችግር በከፊልና የራሱን ተሳትፎ ባረጋገጠ አኳኋን ልንቀርፍለት፣ የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎችን ገንብተን በማቅረብ ለልማታዊ ጥረቱ የተሻለ ሁኔታ ልናመቻችለት ይገባናል፡፡
ü በገጠርም በግብርናና ከግብርና ውጭ በሚካሄዱ ልማታዊ ሰራዎች ተሳትፎውንና ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ ይገባናል፡፡
ü ከዚህ ጐን ለጐን ወጣቱ ትውልድ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በሚካሄደው ትግል ዋነኛ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ተጠናከሮ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡
ü ይህ ሲሆን ብቻ ነው ወጣቱ ሚዛናዊ አስተሳሰብ እንዲይዝ ለማድረግ የምናደርገውን አስተምህሮ በቅን ልቦና ተመልክቶ ሊቀበል የሚችለው፡፡
3. የመንግስትና ፓርቲ አመራርን ሃይማኖታዊ ገለልተኝነት እናጠናክር፣
ü ህዝቡ ለመብቱና ለጥቅሙ የሚያደርገውን ትግል በትክክለኛ መስመር ለመምራት የተነሳው ድርጅታችንም ሆነ ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን የብሄርና የሃይማኖት ልዩነት ሳያደርግ አላማውን የተቀበሉና መንግስታዊ ተልዕኮን ለመፈፀም ዝግጁ የሆኑ ታጋዮችንም ያሰባስባል፡፡
ü ይህም በመሆኑ ድርጅታችንም ሆነ ልማታዊ መንግስታችን የተለያዩ እምነቶች ተከታዮች የሚሳተፉባቸው ተቋማት እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡
ü ይህ መሠረታዊ የግል እምነትን የማክበርና የማስከበር ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ ድርጅታዊ አመራርን የማረጋገጥም ሆነ መንግስታዊ አገልግሎትን የመስጠት ጉዳይ ከሃይማኖት /ከራስህም እምነት ጭምር/ ገለልተኛ በሆነ መንገድ መካሄዱን ማረጋገጥ ይገባል፡፡
ü ዜጐችና የተለያዩ እምነት ተከታዮች ከድርጅት የሚያገኙት አመራርና ከመንግስት የሚያገኙት አገልግሎት በእኩልነት ከሀይማኖት ገለልተኛ በሆነ መንገድ ሊፈፀም ይገባዋል፡፡
ü በየደረጃው የሚገኙ ሀላፊዎች ከዚህ አኳያ በተጨባጭ ከሚፈፀሙ ገለልተኝነትን ለድርድር ከሚያቀርቡ ስህተቶች መጽዳታቸውን ማረጋገጥ ይገባል፡፡
4. የህገ መንግስታዊና ሚዛናዊ አስተሳሰብ ትምህርትን ማስፋፋት፣
ü ሆን ብለውና እያወቁ በሀይማኖት ሽፋን የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ጥረት የሚያደርጉ ወገኖችን ከተሳሳተ አቅጣጫቸው በትምህርት መመለስ አይቻልም፡፡
ü እነዚህ ጥቅማቸውን በጥገኛ ወይም የኪራይ ሰብሳቢ መንገድ ለማሳካት የሚንቀሳቀሱና ለዚህም የቆረጡ ናቸው፡፡
ü ስለሆነም ተጋልጠው የፖለቲካ ተፅዕኖ የማሳረፍ አቅማቸው እንዲዳከምና የማታ ማታ ደግሞ ተነጥለው ወደ ዳርቻ እንዲገፉ /marginalized/ ማድረግ ብቻ የሚጠይቁ ወይም የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ስለሆነም ስለህገ መንግስታዊና ሚዛናዊ አስተሳሰብ አስተምህሮ ስናነሳ ለእነዚህ እንደማይሆን በመገንዘብ ጭምር ነው፡፡
ü ህገ መንግስታዊና የሚዛናዊ አስተሳሰብ ትምህርት ከማንም በላይ የሚያስፈልገውና የሚጠቅመው ከልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ሂደቱ ተጠቃሚ ለሆኑት ብዙሃን ህዝቦች ነው፡፡
ü ስለሆነም ለራሳችን ማህበራዊ መሰረቶች በህገ መንግስታዊ ስርዓታችን ላይ ግልጽነት፣ እምነትና ስርዓቱን ከአደጋ የመጠበቅ ቁርጠኝነት እንዲያዳብሩ የሚያግዝ ትምህርት ልንሰጥ ይገባናል፡፡
ü እያንዳንዱ ዜጋ በማንኛውም ጉዳይ ላይ አቋም ከመውሰዱ በፊት ለምን? ለማንና መቼ? እንዴትና የት? ወዘተ የሚሉ መሠረታዊ ጥያቄዎችን በማንሳት መመርምር እንደሚገባው ማስተማር ይገባናል፡፡
ü እነዚህን ጥያቄዎች በማንሳት የህዝብንና የአገርን ጥቅም የሚጐዳን ማናቸውም ጉዳይ መቃወም፣ የሚጠቅመን ጉዳይ ደግሞ መደገፈ እንዳሚገባ ማስተማር ይገባል፡፡
ü ሌላው ሰው አድርጐታል በማለትና በመንጋ ቅኝት በመመራት አቋም መውሰድ እንደማይገባ ይልቁንም አያንዳንዱ ሰው ራሱን ችሎና በህሊናው አመዛዝኖ አቋም መውሰድ እንዳለበት ማስተማር ይገባናል፡፡
ü በአንድ በኩል ከእያንዳንዱ ሚዛናዊ አቋምና ተግባር በሌላ በኩል ደግሞ ከእያንዲንዱ ሚዛናዊነት የጐደለው አስተሳሰብና ተግባር ተፈላጊውን ትምህርት መስጠትና የሚዛናዊ አስተሳሰብን የበላይነት ማረጋገጥ ይገባናል፡፡
5. በሃይማኖት ሽፋን የሚነግዱትን ሀይሎች በቀጣይነት ማጋለጥና መሰረት ማሳጣት፣
ü እነዚህ ተግባራት በትክክል ከተፈፀሙ አክራሪነትንና ጽንፈኝንት ከማሸነፍ አኳያ ረጅም ርቀት እንደሚወስዱን አያጠያይቅም፡፡ ይህም ሆኖ ብቻቸውን በቂ ናቸው ሊባሉ የሚችሉ አይደሉም፡፡ በሃይማኖት ሽፋን የሚነግዱ ጽንፈኞችን ሁሉ በማጋለጥ ትግል ሊደገፉ የሚገባቸው ናቸው፡፡ ከዚህ ትግል ውጭ የምናገኛቸው ውጤት ምሉዕነት ሊኖረው የሚችል አይደለም፡፡
ü ህዝቡ ህይወቱን በሚመለከቱ መሠረታዊ ጉዳያች ላይ ሁሉ ብቁ፣ ዝርዝርና ወቅታዊ መረጃ እንዲኖረው ማድረግ ነው፡፡
ü የመንግስትን እቅዶችና አፈፃፀም እንዲሁም በአፈፃፀም ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችና መልካም አጋጣሚዎችን የሚመለከት መረጃ ለህዝቡ በፍጥነትና በግልጽ ማቅረብ ይገባናል፡፡
ü ከዚህ አኳያ በየመስሪያ ቤቱና በየድርጅት ጽ/ቤቱ ያሉትን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊዎች አደረጃጀቶች በብቃት ማንቀሳቀስ ይጠበቅብናል፡፡
ü ይህን የማጋለጥና መሠረታቸውን የመናድ ስራ እየሰራን አስፈላጊ ሆኖ በተገኘበት ደረጃና መጠን ደግም ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ይገባናል፡፡
ü እነዚህን በተናጠልና በድምር በመፈፀም በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ አፍራሽና አክራሪ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን በተሟላ አኳኋን አይሳነንም፡፡
ለመደበኛ አባላት የማይነገር ፤ ለከፍተኛ አመራሮች ብቻ
ቀጣዩ የምክር ቤት አባላት ምርጫ የግንቦት ሰባት አና አክራሪ እስልምና ሃይሎችን የሚያስቀጥሉ አባላት ወንብሩ በኢህአዴግ አባላት ስም ሊነጠቅ ይችላል፡፡
የ97 የቅንጅት አሸናፊነት አካሄድ ስልት ማለትም የተቃዋሚ አባለት ሁነው በህቡእ ተደረጅተው በኢህአዴግ የአባላትንት ካርድ ሙሉ በሙሉ ፓርቲው ሊጎዱት ይችላሉ፡፡

ኢቴቪ ጠፍቷል ያለውን የአኬልዳማ ዶክመንተሪ ፊልም ሙሉ ቅጂ አቀረበ

ኢቴቪ ጠፍቷል ያለውን የአኬልዳማ ዶክመንተሪ ፊልም ሙሉ 

ቅጂ አቀረበ

በዳዊት ሰለሞን

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር የሆነው አንዷለም አራጌና የብሄራዊ 

ምክር ቤት አባል ናትናኤል መኮንን በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉ 

በኋላ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ እነ አንዷለምን የያዝነው 

በቂ ማስረጃ ሰብስበን ነው ሲሉ ከቆዩ በኌላ የኢትዩጵያ ቴሌቪዥን 
‹‹አኬልዳማ››የተባለ ዶክመንተሪ ፊልም በማስረጃ መልክ ለእይታ ማቅረቡ 

አይዘነጋም፡፡


በፊልሙ የአንድነት የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ የሆነው አንዷለም አራጌ ከግንቦት ሰባት 

ጋር ግኑኝነት እንዳለው በማስመሰል ከመቅረቡም በላይ የአንድነት አባላት ያልነበሩ 

በደረቅ ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦችን የፓርቲያችን አባላት መሆናቸውን እንዲመሰክሩ 

ተደርገዋል፡፡

በህጋዊ መንገድ ፓርቲያችን ከህዝብ ጋር ለመወያየት በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የጥናት 

ጽሁፍ አቅራቢነት አዘጋጅቶት የነበረውን ውይይት በህቡዕ የተዘጋጀ በማስመሰል 

በፊልሙ ለክስ በሚመች መልኩ መቅረቡም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስረጃ አሰባስበን 

ነው የያዝናቸው ማለታቸውን ትዝብት ውስጥ የከተተ ነበር፡፡


አኬልዳማ ፊልም ለህዝቡ በቀረበበት ወቅት በፍርድ ቤት ጉዳያቸው መታየት 

ያልጀመረን ተጠርጣሪዎች ሽብርተኞች በማለት መፈረጁና በህጋዊ መንገድ 

የሚንቀሳቀሰውን ፓርቲያችንን ጭምር ‹‹የግንቦት ሰባት ጉዳይ አስፈጻሚና 

የሽብርተኞች ተላላኪ››በማለት መፈረጁም አግባብ አለመሆኑን በመጥቀስ የጣብያው 

ሃላፊዎች እርምት እንዲያደርጉና በአንድነት ፓርቲ የተዘጋጀን ፊልም ለህዝብ 

እንዲያሳዩ በደብዳቤ ጭምር ቢጠየቁም ፈቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ፓርቲያችን 

ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ተገድዷል፡፡

ጉዳዩን በ2004 ወርሃ ታህሳስ መመልከት የጀመረው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ 

ልደታ የፍትሃ ብሔር ምድብ ችሎት መዝገቡን ለ15 ጊዜያት ከሳሽና ተከሳሽን 

ሲያከራክር ከቆየ በኋላ ለታህሳስ 11/2006 ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ይዟል፡፡

ከትናንቱ ቀጠሮ ቀደም ብሎ የኢቴቪው ጠበቃ አኬልዳማ የተባለው ዶክመንተሪ 

ፊልም መጥፋቱን እንዲሁም የዶክመንተሪው ሃላፊ የነበሩት ግለሰብ ወደ ውጪ አገር 

በመሄዳቸው የተነሳ ቅጂውን ለማቅረብ ደምበኞቹ መቸገራቸውን ገልጾ የነበረ 

ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ዶክመንተሪውን የግዴታ ማቅረብ እንደሚኖርባቸው 

በማዘዛቸው በተለዋጭ ቀጠሮ ቅጂውን ይዘው ቀርበዋል፡፡

የአንድነት ጠበቃ ተከሳሽ ያቀረቡትን ፊልም ቅጂ ለማመሳከር እንዲሰጣቸው 

ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ይህንን ማዘዝ እንደማይችል በመጥቀስ ለውሳኔ 

ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡