Wednesday, July 31, 2013

በደሴ ከተማ ሼህ ኑሩን ገድላቹሃል በሚል በሐሰት የተወነጀሉት

በደሴ ከተማ ሼህ ኑሩን ገድላቹሃል በሚል በሐሰት የተወነጀሉት ሙስሊሞች 

በማዕከላዊ አስር ቤት ኢ ሰብአዊ ድርጊት እየተፈፀመባቸው መሆኑ ተገለፀ:;

በደሴ ከተማ ከሳምንታት በፊት መንግስት ካስገደላቸው ሼህ ኑሩ ሞት ቡኋላ በደሴ ከተማ በርካታ ሙስሊም ወጣቶች 

መታሰራቸው የሚታወስ ነው፡፤ በዚህም ጉዳይ ተያይዞ የታየሰሩት ሙስሊሞች በቅድሚያ በደሴ ከተማ የፌደራል ፖሊስ ካምፕ 

ውስጥ ታስረው ከፍተኛ ድብደባ የተፈፀመባቸው ሲሆን በመቀጠልም ወደ አዲስ አበባ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል 

ምርመራ ወይም ማዕከላዊ ከተወሰዱ ቡሃላ በምርመራ ወቅት ከፍተኛ ኢ ሰብአዊ ድርጊት እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ምንጮች 

አጋልጠዋል፡፤ የታሰሩት ሙስሊሞች አብዛኞቹ በወጣትነት እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ በማዕከላዊ አስር ቤትም 

በፆመኛ አንጀታቸው እየተፈፀመባቸው ያለውን ድብደባ መቋቋም እንደተሳናቸው እና ከባድ ጉዳትም እየደረሰባቸው 

መሆኑ ተሰምቷ፡፡

ቀን እና ለሊት ያለ እረፍት በምርመራ ሰበብ እየተደበደቡ ሲሆን በአስር ቤቱም ኢ ሰብአዊ በሆነም አያያዝ እንደተያዙ ምንጮች 


አስታውቀዋል፡፤ ከወላጆቻቸው እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር አስካሁን እዳይገኛኙ የተደረገ ሲሆን ቤተሰብም ከብዙ ፍለጋ ቡሃላ 

ማዕከላዊ አስር ቤት መታሰራቸውን ለማወቅ ችለዋል፡፡ ሆኖም ልጆቻቸውን እና የታሰሩ ቤተሰባቸውን ለማየት 

ግን አለመታደላቸው ተሰምቷል፡፡ ምግብ እና ልብስ ከማቀበል ውጪ ታሳሪዎቹ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ለማወቅ 

አለመቻላቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በግፍ የታሰሩት ሙስሊም ወንድሞቻችን ፍርድ ቤት ስለመቅረባቸው አስካሁን የተገኘ መረጃ አለመኖ ተሰምቷል፡ በተጨማሪም 


ሌሎች ተጨማሪ ውንድሞችም በዚህ ሳምንት ከደሴ ከተማ አሸባሪ ተብለው ታፍነው ወደ ማዕከላዊ እንደተወሰዱም 

ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በዚህ በተከበረ ወር ልክ የዛሬ አመት ኮሚቴዎቻችንም ተመሳሳይ የስቃይ ገፈት እየተጋቱ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ዘንድሮ 


ደግሞ የደሴ ለጋ ወጣቶች በቦታው ተተክተው ቁም ስቅላቸውን በድብደባ እያዩ ይገኛሉ፡፡ አላህ ፅናቱን እና ብርታቱን 

ይለግሳቸው!!!

No comments: