Wednesday, September 30, 2015

አገር የምትኖረው በ3 ነገር ነው በወታደር በገበሬ እና በመምህር!!! – ከአዲስ ብርሃኑ


Ethiopia
 አገር ለማፍረስ ቆርጦ የተነሳው ወያኔ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እንድትኖር በመሰሪ ሃሳቡ ሌት ተቀን የማይቆፍረው ግድጓድ የለም የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ነገር ግን እንደ አሳቡ ሊሆንለት አልቻሉም ዘር ከዘር ሊያጋጭ ብዙ ጣረ አልተሳካለትም፤ ሐይማኖት ከሃይማኖት ሞከረ ይሄም አልሰራ አለው ሃሳቡ ሁሉ መና ሲቀርበት እራሱ ከሳሽ እራሱ ፈራጅ በሆነበት ፍርድ ቤት የብዙሃን ነጽሃን ሰው መሰቃያ ወደ ሆነው ወህይኒ እየወረወረ ባልሰራበት ወንጀል ባላደረጉት ድርጊት ንጽሐኑን ማሰቃየት ከጀመረ ድፍን 24 አመት አለፈ።
መምህር…..
አንድ አገር ከሚያስፈልጋት ዋናው መሰረታዊ ነገር መምህር ነው። መምህር ከሌለ የተማረን ህብረተሰብ ማግኝት አይቻልም። መምህር በጠመኔው ለአገር የሚሆን ፍሬ ለህዝብ የሚጠቅም ዘር በሰው አእምሮ ውስጥ የሚዘራ እና ብዙ ጥበቦች ባለ ብዙ እውቀት ባለቤት አገርን በጥበብ የሚመራ ላገሩ በእውቀት የሚያገለግል ለአገር የሚጠቅመውን ካመነበት የሚሰራ ካላመነበት ደግሞ እንቢ የሚል ማንኛውንም ነገር ሰለ ህዝብ ብሎ ስለ አገር ብሎ ማድረግ የሚቻል ዜጋን የሚቀርጹት መምህራናን ናቸው። ዛሬ ወያኔ እያደረገ ያለው እኔ የምላቹሁን አድረጉ እኔ የምላቹሁን አስተምሩ እኔ የምላቹሁን መመርያ ተቀበሉ ብሎ አገርን የሚያጠፋ ሆኖ ሰላገኙት የወያኔ ደጋፊ ባለመሆናቸው ብቻ አገርን የሚያቀኑን መምህራን ትውልድን የሚቀርጹ መምህራን በካድሬ በመተካት የተማረ እንዳይበቅልባት ያወቀ እንዳይወጣባት ትምህርት ቤቶችና ዪንቨርስቲዎች ያቃጣሪወች መናህርያ አድርጓታል። እንግዲህ ወገኔ የመምህራን መነካት የኢትዮጵያ አንዱ መሰረቱ እየተናጋ ነውና ልትነቃ እና የወያኔ አገር አጥፊነቱን አውቀን በቃህ ልንለው ይገባል።
ገበሬ……
አገር የምትኖረው ገበሬው አምርቶ በሚያበቅለው ምርት ነው ገበሬው ጠንክሮ በማረስ አገርን በመመገቡ ሂደት የአገርን መሰረት ነው። ዛሬ ገበሬው ከመሬቱ በማፈናቀል ለውጪ ባለሃብት ለኢንቬስተር በመስጠት እንዲሁም በግድ ማደበርያ እንዲወስድ እያደረጉት ባለ እዳ በማድረግ እዳውን መክፈል ሳይችል ሲቀር መሬቱን ጥሎ እንዲሄድ በማድረግ ተሳዳጅ አድርገውታል። ገበሬ የለም ማለት አገር የለችም ማለት ነው ።ገበሬው በማሰቃየት እረፍት በመንሳት እስመርረውት ያሉት ወያኔወች ሃሳባቸውም ራያቸውም ሰለ ኢትዮጵያ እና ሰለ ሕዝቧ ስላልሆነ ስለሚያደርጉት ነገር መጸጸት እንኳን አያሳዩም ስለዚህ ገበሬው ሲነካ የአገር መሰረት መነካት ነውና ወገኔ እንግዲህ ንቃ።
ወታደር…..
አገር የምትጠበቀው በወታደር ነው አንድ አገር ጠንካራ የወታደር ከሌላት ጠላት በቀላሉ ይዳፈራታል። ስለዚህ ጠንካር የወታደር ተቋም ለአገር አጥርም መሰረት ነው። ዛሬ ግን ወያኔ እየሰራ ያለው የወታደር ተቋም በወታደራዊ ስልጠና እንዲሁም ትምርት በብቃት የሚበልጣቸው እያሉ ትግሬ በመሆኑ ብቻ አዛዥ ቦታ ላይ እንዲቀመጥ ይደረጋል ይሄ አካሄድ ለወያኔወች የአገር ማፍረስ አላማቸው ስለሆነ ምንም አይሰማቸው ለትግሬወች ግን ጊዚያዊ ሹመት ሲሰጣቸው ሁሉንም ቦታ ያለ እውቀታቸው ቦታውን እንዲይዙት ሲደረግ ለምን ብላቹ መጠየቅ ሲገባቹሁ የተሰጣችሁን ስልጣን ተቀብላቹ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ላይ በደልና ጫና የምትፈጥሩ እንግዲህ እዳው በእጃቹ ነው። የወያኔ ባለስልጣን ባንተ ስም የአገርን ንብረት እየዘረፉ እያሸሹ ይገኛሉ አንተ ግን ከህብረተሰቡ ጋር የትም አትሄድም ያኔ በሰፈሩት መስፈርያ እንዳይሆንባቹሁ የትግሬ ተወላጆች በወታደር ላይ የምታደርጉትን በደል ታቆሙ ዘንድ ያስፈልጋል። እንተም ከጥቂት የአገር አጥፊ እና ዘረፊ ጋር ባለመወገን አንድነታቹሁን የምታሳዩበት ጊዜ በጣም አጭር ነውና ይታሰብበት። ካለበለዚያ ግን ወደ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ደምና ጉልበት እንዲሁም በኢትዮጵያ ሕዝብና ሃብት እንደፈለጋቹ እየሆናቹ የምትኖሩበት ጊዜ ማብቂያው ይመጣል።
ወታደሩም እራሱንና አገሩን ሕዝቡን የመጠበቅ ነጻ የማውጣት ሃላፊነት እንዳለበት ወያኔ የሚያውቅበት ጊዜ ቅርብ ነው። ወያኔወች የመከላከያ ሰራዊት የሃገር መሰረት ስለሆነ ይህንም ለማፍረስ እና ለመበተን ሌት ተቀን እየሰሩ ነው። እውነት ነው መምህሩም ወደቀድሞ ቦታቸው ተመልሰው ባላቸው እውቀት ጠመኔን ይዘው ያለምንም ተጽእኖ ዜጋን የሚያፈሩበት ጊዜ ቅርብ ነው። እውነት ነው ገበሬው ሞፈሩን አንስቶ እርሻውን አስፍቶ በትራክተር አርሶ ሕዝቡን የሚመግብበት ቅርብ ነው ። እውነት ነው ወታደሩ ወያኔን የተባለ ወንበዴን አጥፍቶ ለሕዝቡና ለአገሩ ዘብ የሚቆምበት ጊዜ ቅርብ ነው ።
ሞት ለወያኔ!!!
አዲስ ብርሃኑ
29.09.2015
Source: Zehabesha

የሽብር ተግባር ለመፈጸም ፌደራል ፖሊስነት ተቀጥረዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

የግንቦት 7 ድርጅትን ተልዕኮ በመቀበል የሽብር ተግባር ለመፈጸም የፌዴራል ፖሊስ አባል በመሆን መረጃ ሲያስተላልፉ ተደርሶባቸዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሁለት ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡
በፌደራል ፖሊስ ተቋም ውስጥ ተመድበው ሕገ መንግሥቱን ለመጠበቅ የተጣለባቸውን አደራ በመተው፣ የግንቦት 7 ጥምረት ነው የተባለውን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች የሰጣቸውን ተልዕኮ በመቀበል ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉት፣ ኮንስታብል ነገደ ሸዋ ቀናና ረዳት ሳጅን እንዳለ ዘየደ የሚባሉ መሆናቸውን፣ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት መስከረም 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ያቀረበው ክስ ይገልጻል፡፡
ኮንስታብል ነገደ የተባለው ተጠርጣሪ ኤርትራ ከሚኖርና የግንቦት 7 ድርጅት አባል ጋር በስልክ በመገናኘት፣ ለመንግሥት ጥሩ አመለካከት የሌላቸውን እየመለመለ አድራሻቸውን እንዲሰጠው መስማማታቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ በፌዴራል ፖሊስ ተመሳሳይ የሥራ ድርሻ የነበረው ተከሳሽ ረዳት ሳጅን እንዳለ ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸሙን የሚገልጸው የዓቃቤ ሕግ ክስ፣ ሁለቱም ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ በማናቸውም መልኩ መሳተፍ ወንጀል ክስ መሥርቶባቸዋል፡፡ ክሱን ተቀብሎ ያየው ተረኛ ችሎትም ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ በማዘዝ፣ ክሱን ለመስማት ለጥቅምት 2 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ሌላው የመከላከያ ሠራዊት አባል መሆኑ የተጠቀሰውና የኦነግ አባል በመሆን አባላትን በመመልመልና መረጃ በማስተላለፍ ተጠርጥሮ ክስ የተመሠረተበት ወታደር አማኑኤል ደስታ ጅማ ይባላል፡፡
ተከሳሹ ኅብረተሰቡን አደጋ ላይ ለመጣል፣ ሕይወት ለማጥፋትና ንብረት ለማውደምና በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠር፣ ከመስከረም ወር 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሻኪሶ አካባቢ ከድርጅቱ አባላት ጋር ይገናኝ እንደነበር የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡
ተከሳሹ የኦነግን ተልዕኮ ለማሳካት በጥር ወር 2007 ዓ.ም. በአገር መከላከያ ሠራዊት በመቀጠርና ለአራት ወራት ሁርሶ ወታደራዊ ሥልጠና በመውሰድ፣ ሠራዊቱን ተቀላቅሎ መመደቡን ክሱ ያብራራል፡፡
በሠራዊቱ ውስጥ ከተመደበ በኋላ አባላትን በመመልመልና በማደራጀት በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን፣ ሻኪሶ ወረዳ፣ ሻኪሶ ከተማ ከሚገኘውና የኦነግ አባል ከሆነው ደበበ ሚደቅሳ ከተባለው የድርጅቱ አባል ጋር ግንኙነት ሲያደርግ መቆየቱ በክሱ ተጠቅሷል፡፡
የመለመላቸውን ሻምበል ባሻ ስንታየሁና ሃምሳ አለቃ ሸለመ ሞቱማ የተባሉ የመከላከያ ሠራዊት አባላትንና ሌሎች ወታደሮችን አስከድቶ፣ ወደ ኤርትራ ሄደው ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ እያሉ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ክሱ ይገልጻል፡፡ ክሱን ለመስማት ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Tuesday, September 29, 2015

በአፋር የስልጣን ውዝግብ የህወሃት ደጋፊዎች ማሸነፋቸው ተሰማ

መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሃት ነባር ታጋይና በሁዋላም የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( አብዴፓን) መስርተው ክልሉን ላለፉት 24 ዓመታት ሲመሩት የቆዩት አቶ እስማኤል አሊ ሴሮ፣ ከስልጣን ተነስተው ወደ ፌደራል ሲዛወሩ እርሳቸውን ለመተካት በተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ፣ ህወሃት የደገፋቸው ቡድኖች አሸናፊዎች ሆነው መውጣታቸውን የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። ቀድም ብለው ፓርቲውን እንዲመሩ የተመረጡት ወጣቱ አቶ ጣሃ አህመድ ፣ የድርጅቱ ሊቀመንበር ቢሆኑም፣ ክልሉን በፕሬዚዳንትነት መምራት አይችልም የሚል ተቃውሞ የህወሃት ደጋፊና ታማኞች በሆኑት በጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው በአቶ ስዩም አወል፣ በአቶ ሙሃመድ አምበጣና በአቶ እስማኤል ተነስቶባቸዋል። ምንም እንኳ በኢህአዴግና በደጋፊ ፓርቲዎች አሰራር መሰረት የድርጅት ሊቀመንበር የክልል ፕሬዚዳንት የመሆን እድሉ ከፍተኛ ቢሆንም፣ ይህ አሰራር ለአቶ ጣሃ አህመድ አልተፈቀደም። አቶ ጠሃ ወጣት፣ በቢዝነስ ማኔጅመንት የማስተርስ ዲግሪ ያላቸውና በተወሰነ ደረጃም ቢሆንም የህወሃትን የሞግዚት አስተዳደር የሚቃወሙና በሙስና የተዘፈቁ ባለስልጣናትን ለፍርድ ለማቅርብ የሚተጉ መሆናቸው የአቶ እስማኤልን ቡድንና የህወሃት አመራሮችን አላስደሰተም የሚሉ አስተያየቶች ይቀርባሉ። አቶ ጠሃን በመደገፍ አቶ አህመድ ሱልጣን፣ አቶ አወል አርባና አቶ ሙሃመድ ኡስማን ከጎናቸው ቆመዋል። ሁለቱ ቡድኖች ሲያደርጉት የነበረው ውዝግብ ክልሉ ለ3 ወራት ያክል በሞግዚት አስተዳደር እንዲመራ የተደረገ ሲሆን፣ የፌደራል ባለስልጣናት ወደ አካባቢው በመሄድ የአቶ አሊ ሴሮና የህወሃት ታማኞች አሸናፊ ሆነው እንዲወጡ አድርገዋል። 39 መቀመጫ ባለው የድርጅቱ ምክር ቤት አቶ ጠሃ መሃመድ 16 ድምጽ ሲያገኙ ፣ የእሳቸውን ሹመት የሚቃወሙት የአቶ አሊ ሴሮ ደጋፊዎች ደግሞ 20 ድምጽ አግኝተዋል። ሶስት ሰዎች በስብሰባው ባለመገኘት ድምጽ አልሰጡም። የድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ የድርጅቱ ሊቀመንበር ስልጣኑን የሚያጣው በ2/3ኛ ድምጽ ነው የሚል ሲሆን፣ በዚህ ስሌት መሰረት አቶ ጠሃን ለማውረድ 26 የተቃውሞ ድምጽ ቢያስፈልግም፣ የህወሃት ባለስልጣናት ህጉን በመጣስ አቶ ጠሃ በ20 ድምጽ ከ4 ወራት ሹመት በሁዋላ ከስልጣን እንዲወርድ አድርገዋል። በእርሳቸው ምትክ አዲስ ሰው ለመሾም እንቅስቃሴ መጀመሩንና በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት አዲሱ ሰው እንደሚሾም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የድርጅቱን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም

Source: ethsat

Thursday, September 24, 2015

Zone9 Bloggers Are Not Alone: More Ethiopian Citizens Face Terrorism Charges

by Tedla D. Tekle | GlobalVoices
Alongside the now-famous case of the Zone9 bloggers, there are so many detained Ethiopian bloggers, online activists and politicians, whose names are not yet on the map.
Zelalem, Yonatan, Bahiru and Abraham
Zelalem, Yonatan, Bahiru and Abraham. Photo used with permission from debirhan.com
Last year on July 8, 2014, Ethiopia detained a number of local opposition leaders, bloggers, online activists and concerned citizens. Some were released after four months of interrogation. However, ten were charged on October 31, 2014 under Ethiopia’s Anti-Terrorism Proclamation with having links to diaspora-based Ethiopian opposition groups such as Ginbot 7, applying to attend an online security training, and engaging in online activism. Three of the 10 defendants are not members of any political party but ordinary citizens who were arrested for applying to attend a course. These are Zelalem Workagenegu, Yonatan Wolde and  Bahiru Degu.
The controversial Anti-Terrorism Proclamation was adopted in July 2009. Ethiopian officials tend to defend the law by arguing that its controversial provisions were copied from the existing laws of countries such as the United Kingdom. Article 6 of the Proclamation, which has been used to curtail freedom of expression, provides that:
[w]hosoever publishes or causes the publication of a statement that is likely to be understood by some or all of the members of the public to whom it is published as a direct or indirect encouragement or other inducement to them to the commission or preparation or instigation of an act of terrorism [is subject to between 10 and 20 years in prison].
Zelalem, the first defendant, is a human rights activist who blogs at DeBirhan. Yonatan and Bahiru, who are best described as concerned citizens, had applied along with Zelalem for a social media and Internet security training that was brought to their knowledge by a US-based Ethiopian journalist. After an email from the Ethiopian journalist in the US was found in their possession, these young men were also arrested and later charged with applying for “a terror training” when in fact the training was about Internet safety and security.
Ethiopian court last month acquitted Abraham Solomon, detained for having connections with the first defendant Zelalem, along with four other opposition politicians namely Abraha Desta, an official of the opposition Arena Tigray Party and social media activist, Yeshiwas Assefa, council member of the Blue (Semayawi) Party, Daniel Shibeshi, official of the now defunct Unity for Democracy and Justice (UDJ) party and Habtamu Ayalew, former Public Relations Head of the defunct UDJ. However, until today they have not been released because the Prosecutor has reportedly appealed the decision.
An article by the Electronic Frontier Foundation shows the increasing attempts of silencing online activists and netizens in Ethiopia. The organisation called Ethiopia to:
Immediately free all journalists in prison, including the remaining Zone 9 bloggers, and relieve them of all charges for the “crime” of reporting the news.
End the prosecution of individuals for pursuing security training and using encryption technologies, and free Zelalem Workagegnehu, Yonatan Wolde, Abraham Solomon, and Bahiru Degu.
Cease and desist from using invasive surveillance technologies like FinFisher and Hacking Team’s Remote Control System to spy” on Ethiopian journalists, Diaspora, and opposition groups.
While Zone9 remains among Ethiopia’s best-known case of its kind, stories like that of Zelalem demonstrate that the issues these bloggers face extend far beyond a few individuals. The next court appearance of Zelalem, Yonatan and Bahiru is between November 7-9, 2015.
Source: ecadforum

Wednesday, September 23, 2015

የአባይን ግድብ እንዲያጠና የተሰየመው የሆላንዱ ኩባንያ ስራውን በገለልተንነትና በጥራት ለመስራት ባለመቻሉ ኮንትራቱን ማቋረጡን ገለጸ

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሆላንዱ ዴልታሬስ ኩባንያ ከፈረንሳዩ ቢአር ኤል አይ ኩባንያ ጋር በመሆን በአባይ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ጥናት እንዲያካሂድ በግብጽና በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተወክሎ ነበር። ይሁን እንጅ ጥናቱ ከመጀመሩ በፊት በምን መንገድ መካሄድ አለበት በሚለው ነጥብ ዙሪያ ከፈረንሳዩ ኩባንያ ጋር ሲነጋገሩ ቢቆዩም መስማማት አልቻሉም። ኩባንያው ከኢሳት ለቀረበለት የጽሁፍ ጥያቄ በሰጠው መልስ ” ጥናቱን በጥራትና ገለልተኛ በሆነ መንገድ ለማካሄድ እንደ ቅድመ ሁኔታ ብናሰቀምጥም፣ ሌላው ኩባንያ የሚቀበለው አልሆነም” ብሎአል። ዴልታሬስ ገለልተኛ ተቋም እንደመሆኑ ፣ ይህንን ውስብስብና ጠቃሚ ፕሮጀክት በጥራት ለማካሄድ ያሳየው ፍላጎት ተቀባይነት በማጣቱ ከስምምነቱ መውጣቱን ቢገልጽም፣ ውሳኔውን በተመለከተ እስካሁን ከሁለቱም መንግስታት መልስ እንደላገኘ ተናግሯል።
ዴልታሬስ የሰጠውን ውሳኔ በተመለከተ ሁለቱም አገራት እስካሁን በይፋ የተናገሩት ነገር የለም። ይሁን እንጅ በግብጽ የተመረጠው ዴልታሬስ ኩባንያ ያነሳው የገለልተኝነትና የጥራት ጥያቄ፣ ግብጾች በፈረንሳዩ ኩባንያ ላይ ጥያቄ እንዲያነሱ የሚያደርጋቸው ነው። በኢትዮጵያ በኩል የተመረጠው የፈረንሳዩ ኩባንያ በሆላንዱ ኩባንያ ለቀረበው ጥያቄ በይፋ መልስ አልሰጠም፣ ጥናቱን እንደሚቀጥል ወይም እንደማይቀጥል አላስታወቀም።
Source: Ethsat

Ethiopians on Terror Charges Over Food Security Meet, Groups Say

by William Davison
(Bloomberg) — Six human-rights groups urged Ethiopia’s government to free three citizens charged with terrorism after trying to attend a Kenyan food-security workshop.
Pastor Omot Agwa was charged by Ethiopian authorities under the anti-terrorism law after being detained for nearly six months.
Pastor Omot Agwa was charged by Ethiopian authorities under the anti-terrorism law after being detained for nearly six months.
The Sept. 7 charges against Omot Agwa, Ashinie Astin and Jamal Oumar Hojele include trying to attend a “terrorist group meeting,” according to a statement e-mailed by Human Rights Watch, the New York-based advocacy group. The workshop was organized by Bread for All, the development wing of Swiss protestant churches; GRAIN, a Barcelona-based non-profit organization; and the Anywaa Survival Organisation, based in Reading, U.K., which campaigns for the rights of the Anuak people who live in Ethiopia’s western Gambella region.
“Ethiopia should be encouraging debate about its development and food security challenges, not charging people with terrorism for attending a workshop organized by respected international organizations,” said Miges Baumann, deputy director at Bread for All, which also signed the petition. “These absurd charges should be dropped immediately.”
The U.S., European Union and United Nations have criticized Ethiopia’s frequent use of a 2009 anti-terrorism law to criminalize dissent by politicians, journalists and activists. Four bloggers from the Zone 9 group face their 37th hearing next month on charges of supporting terrorism, while a group of Muslim protest leaders were sentenced to between seven and 22 years last month, according to the statement.
Communications Minister Redwan Hussien’s mobile phone was switched off when Bloomberg called seeking comment and State Minister of Communications Shimeles Kemal wasn’t immediately available for comment.
Surging Growth
Economic growth in Ethiopia has surpassed every other sub- Saharan country over the past decade and is forecast by the International Monetary Fund to exceed an annual rate of 8 percent over the next two years. The state-planned economy may be opening up to foreign investors following its sale of $1 billion of Eurobonds last year and plans to start an equities and secondary debt market, London-based Exotix Ltd. said in May.
Gambella is a low-lying, impoverished and unstable Ethiopian region that borders South Sudan. Sporadic clashes occur between the indigenous Anuak and other communities, including migrants from Ethiopia’s highlands. Recent commercial-farming and resettlement programs in the region were the latest federal government interventions criticized by advocacy organizations for violating the rights of local groups.
In February 2014, Omot, an Anuak, worked as a translator for World Bank officials looking into allegations the lender broke its own laws by financing resettlements, according to the statement. He was charged with being a leader of the rebel Gambella People’s Liberation Movement, it said.
Senior administrators from the ethnic Mazinger zone in Gambella were among 46 people charged with inciting violence over the past two years that led to the death of 126 people and displacement of 7,000, Addis Ababa-based Fana Broadcasting Corp. said on its website on Sept. 19.
Source: ecadforum

ኢሕአዴግ በአዲስ አበባ አስተዳደር ሹም ሽር እያካሄደ ነው

የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት አብዛኛዎቹን የክፍላተ ከተሞችና የወረዳ አመራሮች በማንሳት፣ በአዳዲስ አመራሮች እየተካ መሆኑ ታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት
ወረዳዎችና ክፍላተ ከተሞች መመራት ያለባቸው ዲፕሎማና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ባላቸው መሆን አለበት የሚል አዲስ አቋም መያዙ፣ ለሹም ሽሩ ምክንያት መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
በዚህ መሠረት በአሥሩም ክፍላተ ከተሞችና በሥራቸው በሚገኙ 116 ወረዳዎች የሚገኙ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አመራሮች ተነስተዋል፡፡ በተጨማሪም ሹም ሽሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰፈነውን የመልካም አስተዳደርና የሙሰኝነት ችግር ለመቅረፍ መንግሥት ከያዘው ዕቅድ ጋር የሚያያዝ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
ይህን ችግር ለመቅረፍ በቅድሚያ ይህ ችግር ያለባቸው አመራሮች ተገምግመው እንዲነሱ መደረጉም ተገልጿል፡፡ ለማሳያ ያህል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ 12 ወረዳዎች ከዲፕሎማ በታች ያላቸው አመራሮች 70 የሚጠጉ ሲሆን፣ እነዚህ ሁሉ እንደተነሱ ተገልጿል፡፡ በሙስናና በተለያዩ ግድፈቶች ደግሞ 30 አመራሮች እንዲነሱ መደረጉም ተመልክቷል፡፡
በሌሎች ክፍላተ ከተሞችና በሥራቸው በሚገኙ ቀበሌዎችም በተመሳሳይ ከ100 ያላነሱ አመራሮች በእነዚህ ሁለት ምክንያቶች መነሳታቸው ተገልጿል፡፡ ይሁንና ከዲፕሎማ በታች የትምህርት ደረጃ ኖሯቸው አመራር ሲሰጡ የቆዩ አባላት ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት እነዚህ አመራሮች ትምህርት ለመማር ጥያቄ በሚያቀርቡበት ወቅት መንግሥት ቅድሚያ ሥራችሁን ሥሩ የሚል ምላሽ የሰጣቸው በመሆኑ ትምህርት መማር እንዳልቻሉ አስታውሰው፣ ውሳኔው ፍትሐዊ እንዳልሆነ ጠቁመዋል፡፡
በአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ይህንን አለመግባባት ለማስቀረት የውይይት መድረኮች ፈጥሮ እንደነበርም ታውቋል፡፡ በዚህም ያላቸው የትምህርት ደረጃ ዝቅተኛ በመሆኑ የተነሱ አመራሮች የሦስት ወራት ደመወዝ፣ በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ሥራዎችን እንዲሠሩ ወይም ዕድሜያቸው ለጡረታ የደረሰው ደግሞ በጡረታ እንዲገለሉ ሐሳብ ቀርቦ፣ ከሞላ ጎደል መግባባት ላይ መደረሱ ተመልክቷል፡፡
ዋነኛው የአዲስ አበባ ከተማ ችግር የመልካም አስተዳደር እጦትና ኪራይ ሰብሳቢነት [ሙስና] እንደሆነ ነዋሪዎች ባገኙት አጋጣሚ ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ ይህ ችግር የ2007 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም በሚገመገምበት ወቅት በሰፊው ተነስቷል፡፡ በተለይ በመሬት፣ በንግድና በአገልግሎት መስጫ ዘርፎች ላይ ኅብረተሰቡ ከፍተኛ እሮሮ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡
በእነዚህ ዘርፎች ለተገልጋዮች ተገቢውን አገልግሎት አለመስጠት፣ ተገልጋዮችን ለማስተናገድ ዝግጁ አለመሆን፣ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ውሳኔ አለመስጠት፣ ‹‹ጉዳዩ አልታየም›› በማለት ተገልጋዮችን ማጉላላትና ጉቦ መጠየቅ ከሚቀርቡት ቅሬታዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በንግድ በኩል የንግድ ፈቃድ ዕድሳት፣ የንግድ ስያሜ አሰጣጥ፣ የንግድ አድራሻ ማረጋገጫ አሰጣጥ፣ ሕገወጥ ንግድ በሰፊው የሚታዩ ችግሮች ከመሆናቸውም በተጨማሪ፣ በአጠቃላይ የንግድ ሥርዓቱ የተተረማመሰ እንደሆነ ቅሬታ ይቀርባል፡፡
በእነዚህ ሁሉ ችግሮች ሙስና ዋነኛ መገለጫ መሆኑ ከኅብረተሰቡ በሰፊው የሚነሳ ጉዳይ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህንን የኅብረተሰብ ሮሮ በመቀበል፣ የራሱን ግምገማ አካሂዶ ችግሩ እንዳለ አምኗል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ ከሕዝብ ጋር ተወያይቶ ወደ ተግባር እንደሚገባ ገልጾ ነበር፡፡
ይህንን ችግር ለመፍታት በተካሄዱ ተከታታይ ግምገማዎች ግድፈት እንዳለባቸው የተለዩ አመራሮችን ከክፍላተ ከተሞችም ሆነ ከወረዳዎች ማንሳት ዋነኛ ዕርምጃ ሆኗል፡፡
በዚህ መሠረት ቢያንስ ችግሩ ጎልቶ በሚታይባቸው ክፍላተ ከተሞች ከ30 በላይ አመራሮች፣ በወረዳ ደረጃም በተመሳሳይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አመራሮች እንደተነሱ ምንጮች ተናግረዋል፡፡
ይሁንና በአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ባለቤትነት የሚካሄደው ይህ ሹም ሽር ባለፈው ሳምንት መገባደዱን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረ ፃድቃን ሥራው እየተካሄደ መሆኑን ለሪፖርተር አረጋግጠው፣ ሥራው ባለመጠናቀቁ መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በመቀጠል የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በማዕከል ደረጃ የሚገኙ ቢሮዎችንና ኤጀንሲዎችን የሚመሩ አመራሮች ላይ ሹም ሽሩን እንደሚቀጥልም ተገልጿል፡፡ ሹም ሽሩ በርካታ አመራሮችን ከካቢኔ የሚያስወጣና በምትካቸው አዳዲስ የካቢኔ አባላትን እንደሚሾም ምንጮች ተናግረዋል፡፡
የካቢኔ አባላቱ ሹም ሽር በቅርቡ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ቀርቦ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኢንጂነር ይልቃል ካቢኔያቸውን እንደ አዲስ አዋቀሩ

ከነሐሴ 16 እስከ ነሐሴ 17 ቀን 2007 ዓ.ም. ለመጀመርያ ጊዜ በተካሄደው የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ፓርቲውን ለመጪዎቹ ሦስት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ በድጋሚ የተመረጡት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ያዋቀሩትን አዲስ ካቢኔ መስከረም 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ለብሔራዊ ምክር ቤቱ አቅርበው አፀደቁ፡፡
ብሔራዊ ምክር ቤቱ ያፀደቀው አዲስ ካቢኔ በአብዛኛው አዳዲስ አባላትን ያካተተ ሲሆን፣ ከቀድሞው ካቢኔ አባላት መካከል የተካተቱት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ዮናታን ተስፋዬ ብቻ ናቸው፡፡
ፕሬዚዳንቱ ለብሔራዊ ምክር ቤቱ አሥር የካቢኔ አባላትን እንዲያፀድቅላቸው አቅርበው ምክር ቤቱ የሰባቱን ዕጩዎች ምርጫ ሲያፀድቅ፣ ለሁለት አባላት ድምፅ እንዳልሰጠና አንድ ዕጩ ደግሞ ራሳቸውን ከዕጩነት እንዳገለሉ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ከምክር ቤቱ ድምፅ ያላገኙት ሁለቱ የካቢኔው ተጠቋሚ አባላት የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት አቶ ወረታው ዋሴና የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት አቶ እያስፔድ ተስፋዬ ሲሆኑ፣ ራሳቸውን ከዕጩነት ያገለሉት ደግሞ የፓርቲው የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ስለሺ ፈይሳ ናቸው፡፡
በዚህም መሠረት አቶ ነገሰ ተፈረደኝ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ አቶ ዮናታን ተስፋዬ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ አቶ አበበ አካሉ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ፣ አቶ ጋሻው መርሻ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ፣ ወይዘሮ መዓዛ መሐመድ የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ እስክንድር ጥላሁን የጥናትና ስትራቴጂ ኃላፊ፣ እንዲሁም አቶ አዲስ ጌታነህ የሕግ ጉዳይ ኃላፊ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት አቶ ነገሰ ተፈረደኝና የውጭ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አበበ አካሉ ከቀድሞው አንድነት ፓርቲው የተቀላቀሉ አባላት ናቸው፡፡
የደኅንነትና የአባላት ክትትል ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ በዕጩነት ቀርበው የነበሩት ፓርቲውን በምክትል ፕሬዚዳንትነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ስለሺ ፈይሳ፣ ዕረፍት በመፈለግና ለሌሎች ዕድል ለመስጠት ሲሉ ራሳቸውን ከዕጩነት ማግለላቸውን አቶ ዮናታን አስረድተዋል፡፡
ከዕጩነት ራሳቸውን ያገለሉት አቶ ስለሺ ‹‹ሰማያዊ የወጣቶች ፓርቲ ነው፡፡ ስለዚህ እኔ ለወጣቶች ሥፍራውን ብለቅና በምክር ቤቱ ውስጥ በንቃት ብሳተፍ የተሻለ ይሆናል በሚል ራሴን ከዕጩነት አግልያለሁ፤›› በማለት ምክንያታቸውን ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡
የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ ሆነው ፓርቲውን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ወረታው ዋሴን በተመለከተ፣ ‹‹ምንም እንኳን በአዲሱ ካቢኔ እንዲካተቱ ዕጩ ሆነው በፕሬዚዳንቱ አማካይነት ቀርበው የነበረ ቢሆንም፣ ምክር ቤቱ ድምፅ ስላልሰጣቸው አልተመረጡም፤›› ሲሉ አቶ ዮናታን አስረድተዋል፡፡
በተመሳሳይ ድምፅ ሳያገኙ የቀሩት የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የአቶ እያስቤድ ተስፋዬ ጉዳይ በእንጥልጥል ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዝርዝር ጉዳዩን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡
ከካቢኔ አባላት በተጨማሪ ብሔራዊ ምክር ቤቱ የፓርቲውን የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ የመረጠ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት አቶ አበራ ገብሩ ሰብሳቢ፣ አቶ ሳምሶን ገረመው ምክትል ሰብሳቢ፣ አቶ ኃይለ ገብርኤል አያሌው ደግሞ ጸሐፊ ሆነዋል፡፡ አቶ ብርሃኑ መሰለና አቶ ሀብታሙ ደመቀ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ አባላት በመሆን ተመርጠዋል፡፡

Tuesday, September 22, 2015

የመንግስትን ቀጣይ እቅድ አስመልክቶ ለውውይት የተጠራው የአዲስ አበባ ህዝብ “ያልተጠበቁ” ጥያቄዎችን አነሳ

መስከረም ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ መስተዳድር የኢህዴግ ድርጅት ጽ/ቤት ፣ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ረቂቅ ዕቅድ ዙሪያ በከተማው 10 ክ/ከተሞች በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ የህ/ብ ክፍሎችን በሚያወያይበት መድረክ ፣ ነዋሪዎች አወያይ ካድሬዎችን ያስደነገጡ ጥያቄዎችን አንስተዋል። በጉለሌ ክ/ከተማ ስር የሚገኙ የ10 ወረዳዎችን የህብረተሰብ ክፍል በያዘው የወረዳ 9 አዳራሽ በርካታ ጥያቄዎች መነሳታቸውን ስብሰባውን የተካፈሉ ዜጎች ለኢሳት ገልጸዋል። በእለቱ ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል ግንቦት7ትን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቧል። ጠያቂዎች " የእውነት ለለውጥ ከሆነ የምታስቡት ግንቦት 7 የሚባል ጠንካራ የምሁራን ስብስብ ያሉበት ድርጅት እንዳለ እየሰማን ነው፤ ይህን ድርጅት አሸባሪ እያላችሁ በድርጅቱ ሰበብ ወጣቱ እንዲታሰርና ምሁራን ከሃገር እንዲሰደድ ምክንያት ሆናችኋል፣ ዕቅዱ እንዲሳካ ከተፈለገ፣ለውጥ እንዲመጣም ከተፈለገ ዕርቀ ሠላም መምጣት አለበት አለዚያ ምንም ዓይነት ለውጥ እንደማይመጣ ከሁኔታዎች መረዳት እየተቻለ ነው" የሚል ይገኝበታል። እንዲሁም " ድርጅታችን የምትሉት የውሸት ነው፤ ድርጅታችሁ ገምቷል፣ ድርጅታችሁ ሸቷል፣ በአሁኑ ወቅት የ17 ብር ሽንኩርት ለአንድ ጊዜ ወጥ አይበቃም፣ ኑሮው ተወዷል፣የኮንዶሚኒየም ቤት የምትሉትንም በኑሮ ውድነት መክፈል አቅቶን አቋርጠናል እናንተ ግን ልማት ልማት ትላላችሁ፤ ህዝብ ጠግቧል፣ኢኮኖሚ አድጓል ትላላችሁ፣ ለምን ዝቅ ብላችሁ ወደ ታች አታዩም! ፤ መንገድ ሰርታችኋል ትክክል ነው! ባቡር ተጀምሯል ትክክል ነው! ነገር ግን በዚህ ልማት ሰበብ በዲዛይንና በመንገዱ አቅጣጫ እቅድ ችግር ብዙ ዜጎች ቦታቸውንና ቤታቸውን አጥተው ተጎድተዋል፤ አዳዲስ የመንገድ አስፋልቶች በስህተት ዕቅድ ምክንያት ፈርሰዋል! ኪራይ ሰብሳቢነትን መዋጋት ያለበት ህዝቡ ነው ትላላችሁ ችግሩ ግን ከላይ ነው! ድርጅታችሁ ምንድን ነው የሚሰራው?" የሚል ጥያቄ ለካድሬዎቹ ቀርቦላቸዋል። " ልማቱን ማየት አልቻላችሁም፣ በዓለም ፈጣን እድገት እያመጣን ነው ትላላችሁ፡፡ ሃገራችን እንዲታድግ ከተፈለገ ነገሮችን በግልጽ መነጋገር አለብን! ቆሻሻ ዘይት ከውጪ ታስገባላችሁ በምትኩ የሃገራችንን ንጹህ ዘይት ወደ ውጪ ትልካላችሁ! ቆሻሻ ዘይቱን እንኳን በአግባቡ ማግኘት አልቻልንም! " የሚሉ አስተያየቶች ሲቀርቡ፣ አንዳንድ ደጋፊ አስተያየት ሰጪዎች መልስ ለመስጠት ሲሞክሩ፣ በተቃውሞ ጭብጨባ ንግግራቸው ተቋርጧል። "ለምን ችግሩን ለመሸፈን ትሞክራላችሁ? አልሠራችሁም! የወረዳ አመራር ተብለው የሚሾሙት ምንድን ነው ስራቸው?" የሚሉ ጠንካራ ጥያቄዎች መቅረባቸውንም ተሳታፊዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

Source: ethsat

‹‹ለማንም አቤት ማለት አልቻልኩም፡፡››

የ6 አመት ፍርደኛ ነኝ፡፡ ከኤች አይ ቪ በሽታ ጋር እኖራለሁ፡፡ የአንጀት ካንሰርም አለብኝ፡፡ ልጆቼን ያለ አባት ነው ያሳደኳቸው፡፡ በእኔ እስር ምክንያት አሁን እነሱም እየተጎዱ ነው፡፡ አሁን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ አራት አመት ሊሞላኝ ነው፡፡ በህዳር 2007 ዓ.ም በአማክሮ እንድፈታ ማረሚያ ቤቱ ወስኖ ነበር፡፡ ሆኖም ባላወኩት ጉዳይ እንደገና አመክሮዬን ከልክለውኛል፡፡
ቦሌ አየር ማረፊያ ‹‹23›› የሚሉት ስራ አለ፡፡ መንገደኛን ጠብቆ በመኪና አሳፍሮ መንገድ ላይ ይዘርፉና ጥለዋቸው ይሄዳሉ፡፡ አንዲት ልጅ በዚህ ወንጀል ተከሳ ታስራ ነበር፡፡ ከእኔ ጋር ከመገናኘታችን በፊት ከአንድ አመት በላይ ሌላ ቦታ ታስራ ነበር፡፡ ከእኔ ጋር ደግሞ አራት ወር ነው የታሰረችው፡፡ በማላውቀው ወንጀል ይች ልጅ እንድትመሰክርብኝ ተደረገ፡፡
ልጅቱ ወረዳ ዘጠኝ የሚባለው እስር ቤት ውስጥ ታስራ በነበረበት ወቅት በእግዚቪት የተያዘባት ልብስ ብቻ ነው፡፡ ፖሊሶቹም ከዚህ ውጭ ያዝን አላሉም፡፡ እኔም ብጠይቅ ሌላ ነገር ተይዞባታል የሚል አላገኘሁም፡፡ እኔን ግን የሰረኩትን ገንዘብ እስር ቤት ውስጥ ሰጥቻታለሁ ብላ መሰከረችብኝ፡፡ እንግዲህ ገንዘብ ወደ እስር ቤት ሲገባ ተመዝግቦ ነው፡፡ ሳታስመዘግብ አትገባም፡፡ ደግሞ ሰጠኋት የምትለው ገንዘብ እስር ቤት ውስጥ ሊገባ የሚችል አይደለም፡፡ እሷ ለእኔ ሰጠኋት ያለችው ወደ በኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር 40 ሺህ ብር ያህል ነው፡፡ የዱባይ ገንዘብ ነው ሰጠኋት ያለችው፡፡ ስሙን እንኳ በደንብ አታውቀውም፡፡ ሪያድ ነው ያለችው፡፡ ሪያድ የከተማ ስም ነው እንጅ የገንዘብ ስም አይደልም፡፡ የዱባይ ገንዘብ ደግሞ ስሙ ከዚህ ጋር የሚገናኝ አይደለም፡፡ ይህን ያህል ገንዘብ ወደ እስር ቤት ሊገባም አይችልም፡፡ እኔ እጅ ላይ ምንም ገንዘብ ሊገኝ አልቻለም፡፡ ምንም አይነት ማስረጃ አላቀረቡብኝም፡፡ ባለወኩት ምክንያት ሊያጠቁኝ ፈልገው ነው፡፡ ምን እንደሆነ ግን እኔም ሊገባኝ አልቻለም፡፡
ይች ልጅ ይህን ያህል ገንዘብ እስር ቤት ውስጥ ሰጥቻታለሁ ብላ ስለመሰከረችብኝ አመክሮዬን ተከልክያለሁ፡፡ የሚያሳዝነው የሰረኩትን ገንዘብ ለእሷ ሰጠኋት ያለችው ልጅ በእኔ ላይ ከመሰከረች በኋላ ከእስር ተለቃለች፡፡ እኔን ለምን እንዲህ እንደሚያጠቁኝ አላወኩም፡፡ የኤች አይ ቪ በሽተኛ መሆኔን ያውቃሉ፡፡ ሌሎች ችግሮቼንም እንዲሁ፡፡ ይህ በደል እየደረሰብኝ ለማንም አቤት ማለት አልቻልኩም፡፡ የሚሰማ የለም፡፡ ወደ አለቆቻቸው ሄጄ አቤቱታ ማቅረብ አልቻልኩም፡፡
ልጅቱ ገንዘብ ሰርቄ ሰጥቻታለሁ ብላ ለማረሚያ ቤቱ ሰዎች ብትመሰክርብኝም አመክሮዬን ከለከሉኝ እንጅ በፍርድ ቤት ክስ አልተመሰረተብኝም፡፡ እኔም ለፍርድ ቤትም ለሌላም አካል አቤቱታ ማቅረብ የምችልበት አጋጣሚ አላገኘሁም፡፡ ከጠበቃ ጋር እንዳልገናኝ ተደርጌያለሁ፡፡ ለ3 ወር ከ9 ቀን በአጃቢ ነበር ቤተሰብን የማገኘው፡፡ ቤተሰቦቼ እንዳይደነግጡ ብዬ ‹‹እዚህኮ ሁሉንም እንዲህ ነው የሚያደርጉት፡፡ እኔን ብቻ አይደለም›› እላቸው ነበር፡፡ ሽንት ቤት ስሄድም ሳይቀር ይከታተሉኛል፡፡ አደራ ይህን መረጃ ስታወጣ ስሜን እንዳትጠቅስ፡፡ እነሱስ ማንን እንዲህ እንደበደሉ ያውቁታል፡፡ ቤተሰቦቼ እንዳይረበሹብኝ ስለፈለኩ ነው፡፡
(የነገረ ኢትዮጵያ ባልደረባ ያነጋገራት እስረኛ)

Tuesday, September 15, 2015

International Press Freedom Awards for Zone 9 Bloggers

Zone 9 Bloggers, Ethiopia

(Endalkachew H/Michael)
(Endalkachew H/Michael)
In April 2014, Ethiopian authorities arrested six bloggers affiliated with the Zone 9 collective. The bloggers--Abel Wabella, Atnaf Berhane, Mahlet Fantahun, Natnail Feleke, Zelalem Kibret, and Befekadu Hailu--were charged with terrorism.
The Zone 9 blogging collective was formed in May 2012 in response to the evisceration of the independent press and the narrowing of space for free expression. The name, “Zone 9,” is derived from the zones in Kality Prison, the main jail where Ethiopia's political prisoners, including several journalists, are held. While Kality Prison is organized into eight different zones, the bloggers refer to the entire country as “Zone 9” because of Ethiopia’s lack of democratic freedoms, one of the bloggers told CPJ.
The collective is made up of nine bloggers--the six named above, and Soleyana S Gebremichael, Endalk Chala, and Jomanex Kasaye, all of whom are in exile. Soleyana has been charged in absentia.
In July 2015, weeks before U.S. President Barack Obama visited the country, Ethiopian authorities released Mahlet and Zelalem.
The Zone 9 bloggers were arrested along with three other journalists--editor Asmamaw Hailegeorgis and freelancers Tesfalem Waldyes and Edom Kassaye, who were later released. The initial charges against the group included working with international human rights organizations and taking part in email encryption and digital security training. The group was subsequently charged with terrorism.
Since 2009, when Ethiopia’s anti-terror law was implemented, the government has used the sweeping legislation to imprison more than a dozen critical journalists, according to CPJ research. In 2012, blogger Eskinder Nega was sentenced to 18 years in prison and Woubshet Taye to 14 years, both on terrorism charges. CPJ’s 2014 prison census found that Ethiopia was the fourth worst jailer of journalists in the world, with at least 17 journalists behind bars. Ethiopia also ranked fourth on CPJ's 2015 list of the 10 Most Censored Countries.
With the motto "We Blog Because We Care," the Zone 9 collective has voiced concerns over domestic issues, including political repression, corruption, and social injustice. The collective’s posts were frequently blocked inside Ethiopia, but gained a following with Ethiopians in the diaspora, according to local reports. Their posts on Facebook solicited some 12,000 responses a week, reaching 200,000 during a four-part “campaign” they ran on Facebook.
By awarding the Zone 9 bloggers with its International Press Freedom Award, CPJ recognizes the important role that bloggers play in environments where traditional media are weak or have been all but shuttered by financial hardship and direct or indirect state attacks.
Country facts:
  • Ethiopia released at least six journalists from prison in 2015, but is still holding around a dozen journalists in jail in relation to their work.
  • In May 2015, the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) won 100 percent of the vote.
  • In 2014, at least eight independent publications were shut down, according to CPJ research.
  • Between 2013 and 2014, in response to the continued government crackdown on the media, more than 40 journalists fled into exile from Ethiopia.

Thursday, September 10, 2015

የዞን 9 የ2007 ዓ/ም የእስር መስመር

የዞን 9 ጦማርያን ከታሰሩ አንድ አመት ከአምስት ወራት የተቆጠረ ሲሆን ወዳጅ ጋዜጠኞችን ጨምሮ ከጠቅላላው ዘጠኝ እስረኞች መካከል አራት ጦማርያን አሁንም በእስር ላይ በመሆናቸው ሁለተኛ እንቁጣጣሻቸውን በቅሊንጦ እስር ቤት ያከብራሉ ፡፡ ባለፉት አንድ አመት ከአምስት ወራት 36 ግዜ ፍርድ ቤት የተመላለሱ ሲሆን እስራቸው እና የፍርድ ሂደቱ በ2007 ዓ/ም ምን ይመስል እንደነበረ በመጠኑ እናያለን፡፡
የዞን 9 የእስር መስመር
መስከረም 2007  -የዓመቱ መጀመሪያ ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በጻፈው  የቀድሞው አብዮተኛ ኑዛዜ  ተጀመረ፡፡ ጽሁፉ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ የዞን9 ጦማር ላይ ታትሟል፡፡
ጥቅምት 2007 የህግ የበላይነት እና ጸረ ሽብርህጉ ሲገመገም የሚለው ‹‹የጸረ ሽብር ሕጉና›› የአሁኗ ኢትዮጲያ ያላቸውን ግንኙነት አንዲሁም ምን ተፅእኖ እንዳለው የሚያሳየው ልዬ ሪፓርተዥ ተዘጋጀ፡፡ 
ጥቅምት 11 2007 ዓ/ም በእስር ላይ ይገኙ የነበሩትን ጦማሪት ማህሌት ፋንታሁንን እና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬን የእስር ቤት አያያዝ አስመልክቶ የቀረበውን አቤቱታ ለማየት ችሎቱ ተሰየመ፡፡ በእለቱም እስር ቤቱ የተለየ አያያዝ መኖሩን ክዶ የተከራከረ ሲሆን ፍርድ ቤቱም አንደተለመደው እንዳይደገም በሚል የማረሚያ ቃል ችሎቱን አጠናቀቀው፡፡
ከጥቅምት 12 ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ለዞን9 ጦማርያን 6 ወር የእስር ቆይታን አስመልክቶ ለቤተሰቦቻቸውን ድካም የማገዝ የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ በዞን9 ጦማርያን ወዳጆች አማካኝነት በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ፡፡
ጥቅምት 25 - የዞን9 ጦማርያን ለአስረኛ ፍርድ ቤት ቀረቡ ፡፡
ህዳር 2007  -
ህዳር 1 ቀን የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይማርያም ደሳለኝ በተለያዬ ሚዲያዎች ላይ ሲቀርቡ የሚሰጡትን አስተያየት ሕገ-መንግስታዊነትን የጣሰ መሆኑን አስመልክተው ደብዳቤ ጻፉ፡፡ ደብዳቤው የተከሳሾችን በህግ ፊት ንጹህ ሆኖ የመቆጠር መብት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየጣሱ እንደሆነ እና እንዲታረም የሚጠይቅ ነበር፡፡
ሕዳር 3  ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ ለ11ኛ ፍርድ ቤት ቀረቡ ፡፡ በዚህ የፍርድ ቤት ውሎም አቃቤ ህግ በአምስት ጉዳዬች ላይ ክሱን አንዲያሻሽል ትእዛዝ ተሰጠው ፡፡ ( ሊፈጽሙ ነው የተባለውን የሽብር ወንጀል በግልጽ ማስቀመጥ፣ ቡድኑ እየተባለ የተቀመጠው ቡድን ማን እነደሆነ በግልጽ ማስቀመጥ፣ የሥራ ክፍፍልን አስመልክቶ የተጠቀሰውን በግልጽ መስቀመጥ ፣ ተላከ የተባለውን 48000 ብር አስልክቶ በግልጽ ከማን አንደተላከ ማስቀመጥ ፣ ስልጠና የተባሉት ምን እንደሆኑ በግልጽ ማስቀመጥ እና የሽብር ስልጠና ሰጪ ድርጅቱን በግልጽ ማስቀመጥ ይገኙበታል)
ሕዳር 17 - በጦማርያኑ የዋስትና መብትን አስመልክቶ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደርጎ በእስር መቆየታቸው እርግጥ ሆነ ፡፡
ሕዳር 24 - ተሻሻለ የተባለው ክስ በድጋሚ ለፍርድ ቤት ቀረበ ፡፡ ጠበቆች የተሻሻለው ክስ ላይ አስተያየታቸውን አንዲሰጡ ተነገራቸው፡፡ ተሻሻለ የተባለው ክስ ቡድኑ ግንቦት 7 ነው ከማለት ውጪ ምንም አይነት መሻሻል ሳይደረግበት ነበር ለፍርድ ቤት የቀረበው ፡፡
ታህሳስ 2007
ታህሳስ 7 - ጦማሪ ዘላለም ክብረት በእንግሊዘኛ የጻፈው የናፍቆት ደብዳቤ ታተመ
ታህሳስ 9 - ጦማሪ አቤል ዋበላ ‹‹ሕልም እንደሆነ አይታሰርም›› የሚለው ተወዳጅ ጽሁፉ በዞን9 ጦማር ላይ ታተመ ፡፡
ታህሳስ 27 ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ፍርድ ቤቱ ክሱ አንዲሻሻል ታዞ ነገር ግን በተለያዩ አራት ጉዳዮች ላይ አሁንም ባለመሻሻሉ በድጋሚ አንዲሻሻል ሁለተኛ ትእዛዛ ሰጠ፡፡
ጥር 2007
ጥር 6 የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኛ ወዳጆች በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀረቡ ፡፡ በእለቱ አቃቤ ህግ በድጋሚ አሻሻልኩት ያለውን ክስ ይዞ ቀረበ፡፡
ጥር 20 - ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ያቀረበውን ያልተሻሻለ ክስ እንደተሻሻለ መቁጠሩን በመግለጽ ተከሳሾች የህብረተሰቡን ደህንነት ወይም ጤና በማወክ በጸረ ሽብር ህጉ አንቀጽ 4 መከሰሳቸውን አጸና፡፡ የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ የተጠቀሰበትን አንቀጽ በቀደመው ብይን ውድቅ በማድረጉም የተከሳሾች ጉዳይ ‹‹በጸረ ሽብር›› ሕግ ብቻ እንዲዳኝ ተወሰነ፡፡ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ተቀጠረ፡፡
ጥር 26 - የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ፍርድ ቤቱ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ከመስጠታቸው በፊት መሃል ዳኛው አንዲነሱላቸው አቤቱታ አቀረቡ፡፡ ችሎቱም አቤቱታውን ሰምቶ ለመወሰን ሌላ ቀጠሮ ተሰጠ፡፡
ጥር 27 - በዚህም ቀጠሮ የተገኙት ተከሳሾች ሁለቱ ዳኞች ተሟልተው የዳኛው ይቀየርልን አቤቱታን መስማት ስላልቻሉ  በማግስቱ ለጥር 28 ተቀጠሩ ፡፡
ጥር 28 - በዚሁ እለት መሃል ዳኛው ባልተገኙበት ሁለቱ ዳኞች ጉዳዩን አይተው መሃል ዳኛው በፍርድ ሂደቱ ወቅት ጣልቃ አልገቡም አንዲሁም አፋጣኝ ፍትህን አላጓደሉም በማለት ውሳኔ መስጠታቸው ተገለጸ፡፡ ይህንን ተከትሎ የመሃል ዳኛው ምንም አንኳን በጉዳዩ ላይ ዳኞች ችሎቱ ላይ አንድቀጥል ቢፈልጉም ለእኔ ግን አንዲህ እየተባል ክሱ ላይ መቆየት አግባብ ስለማይሆን ራሴን ከችሎቱ አግልያለሁ በማለት አስተያየታቸው ሰጡ ፡፡ ( ነገር ግን ችሎቱን አሁንም የሚያስችሉት እኚሁ ዳኛ ናቸው) ፡፡
በተመሳሳይ እለት ጦማሪ አቤል ዋበላ ከማረሚያ ቤት የደረሰበትን የመብት ጥሰት ( በውሻ ሰንሰለት ታስሮ መቀመጥ እና በማዕከላዊ ሳለ በደረሰበት ድብደባ እንዲጠቀም የተገደደውን የጆሮ ማዳመጫ መሳሪያውን መቀማት) አስመልክቶ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቀረበ ፡፡ ይህን አቤቱታውን በጽሁፍ አንዲያቀርብ ከፍርድ ቤት ቢነገረውም በእለቱ የነበረው ሂደት ብዙዎን በፍርድ ቤት ውስጥ እንባ አራጨ፡፡ በእለቱ የነበሩት የእስር ቤት ተጠሪ የማውቀው ጉዳይ የለም በማለት የመብት ጥሰቱን ክደዋል፡፡
የካቲት 2007
የካቲት 11 - የዳኛው መቀየር አቤቱታን ፍርድ ቤቱ ውድቅ ካደረገው በኋላ የዞን 9 ጦማርያ እና ጋዜጠኞች የካቲት 11 ቀን ለ20ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት በመገኘት የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ በእለቱን ጦማሪ በፍቃዱ ‹‹የሽብር ተግባር አልፈጸምኩም ሽብር ተፈጽሞብኛል›› ሲል፣ ጦማሪ ናትናኤል በበኩሉ ‹‹እዚህ አገር ፍትህ ቢኖር ኖሮ እኔ የቆምኩበት ቦታ ላይ መቆም የሚገባቸው ከሳሾቼ ናቸው፤ ምንም አይነት ወንጀል አልፈጸምኩም›› የሚል ቃሉን ሰጥታል፡፡ ጦማሪ አጥናፍ ‹‹ምንም አይነት ወንጀል አልፈጸምኩም›› ያለ ሲሆን ጦማሪ አቤል በበኩሉ ‹‹የኅብረተሰቡን ደህንነት ለመጉዳት አላቀድኩም ለሽብር ተግባርም አላሴርኩም ብሏል፡፡››  የሴት እስረኞችን አያያዝ አስመልክቶ አጭር ቀጠሮ የሰጠን ሲሆን አጠቃላይ የማስረጃ ማሰማት ሂደቱን ግን ከአንድ ወር ከ10 ቀን በኋላ በተከታታይ ለሶስት ቀን ቀጥሮታል፡፡
የካቲት 18 - የሴት እስረኞችን አያያዝ አስመልክቶ ችሎቱ የተሰየመ ጉዳዬን ለማየት በድጋሚ ቀጠሮ ሰጥታል፡፡  
መጋቢት 2007
መጋቢት 21 - የሰው ምስክር ናቸው ተብለው የቀረቡ ሰዎችን ምስክርነት መስማት ተጀመረ ፡፡ ሁሉም ምስክሮች እቃዎች ሲፈተሹ ያየን ነን በማለት የተያዙ እቃዎቸን ከማየታቸው በስተቀር ያቀረቡት የተለየ የወንጀል ምስክርነት አልነበረም ፡፡ ምስክሮቹ ተከሳሾን መለየት ሲያቅታቸው የተስተዋሉ ሲሆን በመጀመሪያው ቀን 6 ሰዎች ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ የተከሳሽ ጠበቆች ባልተካደ ነገር ላይ የፍርድ ቤቱም የተከሳሾችም ጊዜ መባከን አይገባውም እቃውም የእኛ አይደለም የሚል ቃል አልሰጠንም ስለዚህ የደረጃ ምስክሮች መስማት ይቁም ቢሉም ፍርድ ቤቱ ታዛቢዎቹን መስማት መቀጠል አለበት በማለቱ የተገኙ እቃዎችን ሲዘረዝሩ ከርመዋል ( መጽኃፍት ፣ መጽሄቶች፣ አርቲክሎች ላፕ ቶፕ ስልኮች እና ሲምካርዶች የመሳሰሉት ከፍተሻ ዝርዝሩ ውስጥ የተገኙ ናቸው)
መጋቢት 22 - ተጨማሪ 8 ምስክሮች በተመሳሳይ ሁኔታ ቃላቸውን ሲሰጡ ውለዋል፡፡ ከነዚህ በላይ ምስክሮችን ማቅረብ ያልቻለው አቃቤ ህግ ተጨማሪ ጊዜ በመጠየቁ ለመጋቢት 30 ቀጠሮ ተሰጥታል፡፡
መጋቢት 30 - አቃቤ ህግ ምስክሮቼ ጠፍተውብኛል፡፡ የሲዲ ማስረጃዎችንም የያዘው ሰው በአገር ውስጥ ስለማይገኝ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ የሚል ጥያቄ አቅርቦ በመፈቀዱ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶ ችሎቱ ተበትናል ፡፡
መጋቢት 25 - ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ይድረስ ለኢቢሲ ጋዜጠኞች የጻፈው ጽሁፍ ታትሞ ወጥቷል፡፡
ሚያዝያ 2007
ሚያዝያ 16-19 የ6ቱ ጦማርያንን እና የ3ቱን ጋዜጠኞች እስር አንደኛ አመት አስመልክቶ ለነጻነታቸው ዋጋ የሚከፍሉትን እናወድስ የሚል የሁለት ቀናት ማስታወሻ ተዘጋጀ፡፡ በማስታወሻው ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ የደረሰባቸውን የመብት ጥሰት ዝርዝር እና የተያዙበትን እለት የነበረውን ድባብ ያሳየ ሲሆን ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች በሁነቱ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል ፡፡  በዚሁ የማስታወሻ ዝግጅት ላይ የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች የላኩት የአንደኛ አመት ማስታወሻም ተስተናግዷል፡፡
ግንቦት 2007
ግንቦት 2
በዞን 9 ወዳጆች አማካኝነት የተዘጋጀው ሁለተኛው የቤተሰቦቻቸውን ሸክም መጋራት የሚለው የአንድ ሳምንት ዘመቻ ለሁለተኛ ጊዜ ተካሄዷል፡፡
ግንቦት19-21 በነዚህ ቀናት በዋለው ችሎት ላይ ከፍተኛ መወዛገብ ያሳየው አቃቤ ህግ ሲዲዎቹን እንደማስረጃ ማስመዝገብ ባለመቻሉ እና ምስክሮችንም ማቅረብ ስላልቻለ ሲዲዎቹ ከማስረጃ ላይ አንዲወገዱ እንዲሁም ተጨማሪ ምስክሮችን ለማቅረብም የተወሰነው ጊዜ በቂ ሆኖ አልተጠቀመበትም በሚል ምክንያት ተጨማሪ እድል እንዳይሰጠው ተወስኗል ፡፡
አቃቤ ህግ አንደኛ ተከሳሽ ሶልያና ሽመልስ ላይ አለኝ ያለውን የሲዲ ማስረጃ አስመልክቶ ሌሎች ተከሳሾች ማየት አለባቸው ወይስ ፍር ቤቱ በጽህፈት ቤት ማየት አለበት የሚለውን ለመወሰን ሰኔ 8 ተቀጥሯል፡፡
በተመሳሳይ ቀን ችሎት ውስጥ አቤል ዋበላ ከዳኞች ጋር በነበረው አለመስማማት የተነሳ የችሎት መድፈር ጥፋተኛ ተብሎ ለቅጣት ለግንቦት 25 ተቀጠረ፡፡
ግንቦት 23 - ሥነ-ስርዓት የሚለው የጦማሪ አቤል ዋበላ ጽሁፍ ታትሟል፡፡
ግንቦት 25 አቤል ዋበላ በችሎት መድፈር በገደብ 4 ወር ተፈርዶበታል ፡፡
ሰኔ 2007
ሰኔ 8 - ፍርድ ቤት የቀረቡት 9 ተከሳሾች ከብይን ለሃምሌ 13 የተቀጠሩ ፡፡ በእለቱም አንደኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበውን የሲዲ ማስረጃ በጽህፈት ቤት አይተን እንደማስረጃ ቆጥረነዋል፡፡ ለሌሎች ተከሳሾም መድረስ አይገባውም በማለት ችሎቱ ወሰነ
ሃምሌ 2007
ሃምሌ 1 ቀን 2007 ዓ/ም ባተጠበቀ ሁኔታ ሶስቱ ጋዜጠኞች እና ሁለት የዞን9 ጦማርያን ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር መፈታታቸው ዜና ተሰማ ፡፡ በእለቱ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ፣ ጋዜጠኛ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ እና ጦማሪ ዘላለም ክብረት ሲፈቱ በማግስቱ ጠዋት ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ እና ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን ተፈቱ፡፡
በተመሳሳይ ቀን በቀሪዎቹ 5ቱ ተከሳሾች ላይ ክሱ አንደሚቀጥል የመንግስት ወዳጅ የሆነው ሬዲዬ ፋና በድረ ገጹ አሳወቀ ፡፡
ሃምሌ 9-11 ለሶስት ቀናት የሚቆይ እስቲ አንነጋገር የማስረጃን ነገር በሚል የተዘጋጀው ዘመቻ ተካሄደ ፡፡ ይህ ዘመቻ ሃሳቡ ተከሳሾች ላይ ማስረጃ ተብለው የቀረቡ ጉዳዬችን ለአደባባይ ማብቃትና ቀሪ አራት ታሳሪዎች የሚከላከሉት ምንም ነገር እንደሌለ ለማሳወቅ የታለመ ነበር ፡፡
ሃምሌ 10 - ጦማሪ በፍቃዱ ቁዘማ፣ ከአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች በፊት እና ጦማሪ ናትናኤል የዕለት ተዕለት ጥያቄዎቻችን ብይናቸውን አስመልክቶ የጻፋቸው ጽሁፎች ታተሙ፡፡
ሃምሌ 13 - ፍርድ ቤቱ የአንድ ምስክር ቃል ተገልብጦ አልደረሰኝም በማለት ብይኑን መስራት አለመቻሉን ገልጾ ጽሁፉ መገልበጡን ለማረጋገጥ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ ፡፡
ሃምሌ 22 - የተከሳሾች ጽሁፍ ተገልብጦ ማለቁን አረጋግጫለሁ ያለው ፍርድ ቤቱ ከጽህፈት ቤት በማስቻል በድጋሚ ለጷጉሜ 2 ቀጠሮ ሰጠ
ሃምሌ 25 - ጥቂት ስለማእከላዊ የሚል ጽሁፍ ታተመ፡፡
ጷጉሜ 2007

በአመቱ የመጨረሻ ሳምንት የመጨረሻ የእስር ሳምንታቸው ይሆናል ተብሎ ተስፋ ቢደረግም ፍርድ ቤቱ ዳኞች አልተሟሉም በሚል ሌላ ሰበብ ሁለተኛ እንቁጣጣሻቸውን በእስር እንደሚያሳልፉ ያረጋገጠውን የ31 ቀን ቀጠሮ በመስጠት ለመስከረም 27 ለአራተኛ ጊዜ በአጠቃላይ ደሞ ለ37ተኛ ጊዜ ቀጠሮ ሰጠ ፡፡

Source: Zone9

Wednesday, September 9, 2015

በአርበኞች ግንቦት7 ስም የተከሰሱት በእስር ቤት የደረሰባቸውን በደል ተናገሩ

ጷግሜን ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል የቀድሞው አንድነት ፓርቲ ዋና ጸሃፊ የነበረው አቶ ተስፋዬ ታሪኩ በእስር ቤት እየደረሰባቸው ያለውን ስቃይ እንዲሁም መስክሮች በሃሰት መስክሩ ተብለው እግራቸው እንደተሰበረ ሲገልጽ፣ የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ የታች አርማጭሆ ተወካይ አቶ አንጋው ተገኝ ደግሞ በእስር ቤት ውስጥ በጨለማ ቤት በመቀመጡ አይኑን መታተመሙንና ህክምና መከልከሉን ገልጿል። ኢሳት ያናገረው አንደኛው የሃሰት ምስክር ደግሞ "የግዳጅ ስራ ስለሆነ ምንም አማራጭ አልነበረንም" በማለት በጫና ውስጥ ሆኖ መናገሩን ገልጿል። አቃቤ ህግ በ1ኛ ተከሳሽ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን፣ በ8ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ታሪኩ፣ በ13ኛ ተከሳሽ እንግዳው ቃኘው፣ በ15ኛ ተከሳሽ አግባው ሰጠኝ ላይ የሰነድ ማስረጃ እንጅ የሰው ምስክር እንደሌለው ገልጾ፣ በ2ኛ ተከሳሽ በላይነህ ሲሳይ፣ 3ኛ ተከሳሽ አለባቸው ማሞ፣ 4ኛ ተከሳሽ አወቀ ሞኝ ሆዴ፣ 5ኛ ተከሳሽ ዘሪሁን በሬ እና በትናንትናው ዕለት ምስክሮች የተሰሙበት 7ኛ ተከሳሽ አማረ መስፍን ላይ ምስክሮቹን ማሰማቱን ነገረ -ኢትዮጵያ ዘግቧል። "የአቶ አማረ መስፍን ቤት በፖሊስ ተከቦ ሲበረበር የጦር መሳሪያና ሰነዶች ይኖራሉ ተብሎ ለእማኝነት እንደተጠራ የተናገረው 7ኛ ምስክር ፣ ‹‹በአቶ አማረ መስፍን ቤት ይኖራል ተብሎ የተጠበቀው መሳሪያና ሰነድ አልተገኘም፡፡›› ሲል መስክቷል፡፡ "በተከሳሹ የግል ድርጅት በሆነው ሱቅ ውስጥ ሽጉጥ እንደተገኘ የተናገረው ምስክሩ፣ መሳሪያው ህጋዊ ነው ወይስ አይደለም ተብሎ ሲጠየቅ፣ ‹‹መተማ ውስጥ ሁሉም ሰው የድርጅት መጠበቂያ መሳሪያ አለው፡፡ እኔ በዚሁ ከተማ ስለሆነ የምኖረው አውቀዋለሁ፡፡ መንግስት አስመዝግቡ ብሎ ይመጣል እንጅ ነዋሪው ለድርጅቱ መጠበቂያ ያልተመዘገበም ቢሆን መሳሪያ ይኖረዋል፡፡›› ሲል ያልተጠበቀ ምስክርነት ሰጥቷል። "በውንብድና ወንጀል ተከሶ 10 አመት ተፈርዶበት ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2005 ዓ.ም ታስሮ እንደተፈታ የገለፀው 8ኛ ምስክር" ደግሞ፣ በአቶ በላይነህ ሲሳይ በኩል ስልካቸውን አገኘሁ ያላቸው ሰዎች ኤርትራ ውስጥ የሚኖሩ የአርበኛው ግንባር አመራሮች በኢትዮጵያ የስልክ ቁጥር ሲደውሉለት እንደነበር፣ የአርበኛው ግንባር አመራሮች መሳሪያና ገንዘብ እንዲወስድ ሲጠይቁት ለገንዳውሃ አስተዳደር አመልክቶ መሳሪያውንና ገንዘቡን እንዲቀበል እንዳበረታቱት፣ መልምለውኛል ያላቸውንና ተመልምለዋል ያላቸውን ሰዎች እንቅስቃሴ ለመንግስት ሲያሳውቅ" እንደቆየ ተናግሯል። በአቶ አለባቸው ማሞ ላይ የመሰከረው 9ኛ ምስክር የኢህአዴግ አባል መሆኑን እንዲሁም በመስቀለኛ ጥያቄ የደህንነት ሰራተኛ መሆኑን አምኗል፡፡ ኤርትራ የነበሩ አመራሮች ‹‹ብአዴን አይቀጥልም፡፡ በመሆኑም ከህዝብ ጋር አትቀያየም፡፡ ክፉ ስራ አትስራ›› እያሉ ሲደወሉለት እንደነበር ገልጾ፣ ተከሳሹ ስልኩን ለግንቦት7 አመራሮች እንደሰጠበት መስክሯል፡፡ 9ኛ ምስክርን ጨምሮ ሌሎችም የአቃቤ ህግ ምስክሮች ፍርድ ቤት በተገኙ የተከሳሾች ቤተሰቦች ማስፈራሪያና ዛቻ እየተፈፀመባቸው ነው ሲል አቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ማቅረቡን ጋዜጣው ዘግቧል። አቶ አወቀ ሞኝሆዴ ላይ የመሰከረው 10ኛ ምስክር ወደ ኤርትራ ለመሄድ ማይካድራ ላይ እንደተያዘ ገልጾ፣ ‹‹ማይካድራ ላይ ያዙን፡፡ ሁመራ ወሰዱንና ተገረፍን፡፡›› ብሏል፡፡ በእስር ላይ እንደቆየም ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ በተመሳሳይ አቶ ዘሪሁን በሬ ላይ የመሰከሩት 12ኛ ምስክርም ‹‹ማይካድራ ላይ ከተያዝኩ በኋላ ሁመራ ላይ ተቀጥቻለሁ፡፡›› ብሎአል። አቃቤ ህግ በዛሬው ዕለት ሁሉንም ምስክሮች አሰምቼ እጨርሳለሁ ብሎ የነበር ቢሆንም፣ ሁለቱ ምስክሮች መጥሪያው ደርሷቸው ስላልመጡ፣ እንዲሁም አራት ምስክሮች መጥሪያ ስላልደረሰላቸው ረዥም ቀጠሮ እንዲሰጠው ቢጠየቅም ተከሳሾች ተቃውመዋል። 8ኛ ተከሳሽ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ ‹‹ባለፉት 11 ወራት ያለጠያቂ፣ ቤተሰብም እኛም ብዙ ተሰቃይተናል፡፡ በግፍ እየተሰቃየንም እንገኛለን፡፡ አቃቤ ህግ ምስክሮቹን በታቀደው ጊዜ ማቅረብ አለመቻሉ ደግሞ ከበደላችን በላይ በደል እየተፈፀመብን ነው፡፡ ስቃዩ በእኛ ብቻ ሳይሆን በምስክሮች ላይም ጭምር ነው፡፡ የሀሰት ምስክርነት ስጡ ተብለው ሁለት ሰዎች አካላቸውን አጥተዋል›› ሲል ተናግሯል። ፍርድ ቤቱ የተስፋዬን ንግግር ማስቆሙም ተዘግቧል። 14ኛ ተከሳሽ አቶ አንጋው ተገኝ ደግሞ ‹‹በማዕከላዊ 6 ወር ጨለማ ቤት ስለቆየሁ አይኔን ታምሜያለሁ፡፡ ለአይኔ መነፀር እንደሚያስፈልግ ቢታወቅም ህክምና እንዳላገኝ ተከልክያለሁ፡፡›› በማለት ቅሬታ አቅርቧል። የተከሳሽ ጠበቃ ‹‹አቃቤ ህግ ችሎቱን እየመራው ነው›› ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡ በመጨረሻም የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት የአቃቤ ህግን ቀሪ 6 ምስክሮች ለመስማት ለህዳር 13/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ኢሳት አንደኛውን የሃሰት ምስክር በስልክ ያናገረው ሲሆን፣ ምስክሩም " የግዳጅ ስራ ስለሆነ ምንም አማራጭ የለንም፣ የተባልነውን ብቻ ስራ መስራት ነው" የሚል መልስ ሰጥቷል። ዝርዝር መረጃ እንዲሰጥ ሲጠየቅ "እባካችሁ ታስፈጁናላችሁ" በማለት በዝርዝር ለመናገር ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል

Source: ethsat

ፍርድ ቤቱ በእነ ጌታቸው መኮንን ላይ ተጨማሪ ምስክሮችን ለመስማት ለህዳር 13 ቀጠረባቸው

• ‹‹እኛ ብቻ አይደለም የተሰቃየነው፡፡ የሀሰት ምስክርነት ስጡ ተብለው ሁለት ሰዎች አካላቸውን አጥተዋል›› አቶ ተስፋዬ ታሪኩ
• ‹‹በማዕከላዊ 6 ወር ጨለማ ቤት ስለቆየሁ አይኔን ታምሜ ህክምና ተከልክያለሁ›› አቶ አንጋው ተገኝ
• ‹‹ማይካድራ ላይ ያዙን፡፡ ሁመራ ወሰዱንና ተገረፍን፡፡›› ምስክር
የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ ስር የሚገኙ ተከሳሾች ላይ ተጨማሪ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ለህዳር 13/2008 ዓ.ም ቀጥሮባቸዋል፡፡ ትናንት ጳግሜ 3/2007 ዓ.ም 13 ምስክሮችን እንዲሁም በዛሬው ዕለት 7 ምስክሮችን በማሰማት አጠናቅቃለሁ ብሎ የነበረው የፌደራል አቃቤ ህግ በትናንትናው ዕለት 6 እንዲሁም በዛሬው ዕለት 8 ምስክሮችን ብቻ ያሰማ ሲሆን ተጨማሪ 6 ምስክሮችን ለማሰማት ረዥም ቀጠሮ ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡
በትናንትናው ዕለት በ6ኛ፣ በ7ኛ፣ በ9ኛ እና በ12ኛ ተከሳሾች ላይ ምስክሮቹን ያሰማው አቃቤ ህግ በ1ኛ ተከሳሽ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን፣ በ8ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ታሪኩ፣ በ13ኛ ተከሳሽ እንግዳው ቃኘው፣ በ15ኛ ተከሳሽ አግባው ሰጠኝ ላይ የሰነድ ማስረጃ እንጅ የሰው ምስክር እንደሌለው አስረድቷል፡፡ በዛሬው ዕለት በ2ኛ ተከሳሽ በላይነህ ሲሳይ፣ 3ኛ ተከሳሽ አለባቸው ማሞ፣ 4ኛ ተከሳሽ አወቀ ሞኝ ሆዴ፣ 5ኛ ተከሳሽ ዘሪሁን በሬ እና በትናንትናው ዕለት ምስክሮች የተሰሙበት 7ኛ ተከሳሽ አማረ መስፍን ላይ ምስክሮቹን አሰምቷል፡፡
የአቶ አማረ መስፍን ቤት በፖሊስ ተከቦ ሲበረበር የጦር መሳሪያና ሰነዶች ይኖራሉ ተብሎ ለእማኝነት እንደተጠራ የተናገረው 7ኛ ምስክር ሆኖም ‹‹በአቶ አማረ መስፍን ቤት ይኖራል ተብሎ የተጠበቀው መሳሪያና ሰነድ አልተገኘም፡፡›› ሲል መስክቷል፡፡ የተከሳሽ የግል ድርጅት በሆነው ሱቅ ውስጥ ሽጉጥ እንደተገኘ የተናገረው ምስክር መሳሪያው ህጋዊ መሆን አለመሆኑን ሲጠየቅ ‹‹መተማ ውስጥ ሁሉም ሰው ድርጅት መጠበቂያ መሳሪያ አለው፡፡ እኔ በዚሁ ከተማ ስለሆነ የምኖረው አውቀዋለሁ፡፡ መንግስት አስመዝግቡ ብሎ ይመጣል እንጅ ነዋሪው ለድርጅቱ መጠበቂያ ያልተመዘገበም ቢሆን መሳሪያ ይኖረዋል፡፡›› ብሏል፡፡
በውንብድና ወንጀል ተከሶ 10 አመት ተፈርዶበት ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2005 ዓ.ም ታስሮ እንደተፈታ የገለፀው 8ኛ ምስክር በበኩሉ በአቶ በላይነህ ሲሳይ በኩል ስልካቸውን አገኘሁ ያላቸው ኤርትራ ውስጥ የሚኖሩ የአርበኛው ግንባር አመራሮች በኢትዮጵያ የስልክ ቁጥር ሲደውሉለት እንደነበር፣ የአርበኛው ግንባር አመራሮች መሳሪያና ገንዘብ እንዲወስድ ሲጠይቁት ለገንዳውሃ አስተዳደር አመልክቶ መሳሪያውንና ገንዘቡን እንዲቀበል እንዳበረታቱት፣ መልምለውኛል ያላቸውንና ተመልምለዋል ያላቸውን ሰዎች እንቅስቃሴ ለመንግስት ሲያሳውቅ እንደቆየ መስክሯል፡፡
በአቶ አለባቸው ማሞ ላይ የመሰከረው 9ኛ ምስክር በዋና ጥያቄ የኢህአዴግ አባል መሆኑን እንዲሁም በመስቀለኛ ጥያቄ ደህንነት መሆኑን አምኗል፡፡ ምስክሩ ‹‹ብአዴን አይቀጥልም፡፡ በመሆኑም ከህዝብ ጋር አትቀያየም፡፡ ክፉ ስራ አትስራ›› በሚል ኤርትራ ከሚገኙ አመራሮች ሲደወሉለት እንደነበር ስልኩንም ተከሳሹ ለአመራሮቹ እንደሰጠበት መስክሯል፡፡ 9ኛ ምስክርን ጨምሮ ሌሎችም የአቃቤ ህግ ምስክሮች ፍርድ ቤት በተገኙ የተከሳሾች ቤተሰቦች ማስፈራሪያና ዛቻ እየተፈፀመባቸው ነው ሲል አቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርቧል፡፡
አቶ አወቀ ሞኝሆዴ ላይ የመሰከረው 10ኛ ምስክር በአሁኑ ወቅት ኤርትራ ውስጥ ይገኛሉ ያላቸው አቶ አንለይ ተስፋው የተባሉ ግለሰብ ወደ ኤርትራ የሄዱበት እሱም እንዲሄድ የተጠየቀበትን ምክንያት ሲያስረዳ ‹‹ኤርትራ ውስጥ ቅንጅት ስላለ ነው፡፡›› ብሏል፡፡ ለምስክርነት የመጣበት ተከሳሽ ለምን እንደተከሰሰ ሲጠየቅም ‹‹የቅንጅት አባል በመሆኑ ነው የተከሰሰው›› ብሏል፡፡ ወደ ኤርትራ ለመሄድ ማይካድራ ላይ እንደተያዘ የገለፀው ምስክሩ ‹‹ማይካድራ ላይ ያዙን፡፡ ሁመራ ወሰዱንና ተገረፍን፡፡›› ብሏል፡፡ በእስር ላይ እንደቆየም ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ በተመሳሳይ አቶ ዘሪሁን በሬ ላይ የመሰከሩት 12ኛ ምስክርም ‹‹ማይካድራ ላይ ከተያዝኩ በኋላ ሁመራ ላይ ተቀጥቻለሁ፡፡›› ብለዋል፡፡
አቃቤ ህግ በዛሬው ዕለት ሁሉንም ምስክሮች አሰምቼ እጨርሳለሁ ብሎ የነበር ቢሆንም ሁለቱ ምስክሮች መጥሪያው ደርሷቸው ስላልመጡ፣ እንዲሁም አራት ምስክሮች መጥሪያ ስላልደረሰላቸው ረዥም ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ የተከሳሾቹ ጠበቆች በበኩላቸው አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ያላቀረበበት ምክንያት ግልፅ እንዳልሆነ ደጋግመው ለፍርድ ቤቱ መናገራቸውን፣ በተለይ ደንበኞቻቸው ዋስትና ተነፍጓቸው በእስር ላይ የሚገኙ በመሆኑ አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ማሰማት እንዳልፈለገ ተቆጥሮ በቀጣዩ ቀጠሮ ብይን እንዲሰጥ፣ ይህ ባይሆን አጭር ቀጠሮ ተሰጥቶ የቀሩት ምስክሮች እንዲሰሙ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡
ከተከሳሾቹ መካከል 8ኛ ተከሳሽ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ ‹‹ባለፉት 11 ወራት ያለጠያቂ፣ ቤተሰብም እኛም ብዙ ተሰቃይተናል፡፡ በግፍ እየተሰቃየንም እንገኛለን፡፡ አቃቤ ህግ ምስክሮቹን በታቀደው ጊዜ ማቅረብ አለመቻሉ ደግሞ ከበደላችን በላይ በደል እየተፈፀመብን ነው፡፡ ስቃዩ በእኛ ብቻ ሳይሆን በምስክሮች ላይም ጭምር ነው፡፡ የሀሰት ምስክርነት ስጡ ተብለው ሁለት ሰዎች አካላቸውን አጥተዋል›› ብሏል፡፡ በሀሰት ምስክርነት ስጡ እየተባሉ በደል እየደረሰባቸው ስለሚገኙ ግለሰቦች በሚናገርበት ወቅትም ፍርድ ቤቱ አስቁሞታል፡፡ 14ኛ ተከሳሽ አቶ አንጋው ተገኝ በበኩሉ ‹‹በማዕከላዊ 6 ወር ጨለማ ቤት ስለቆየሁ አይኔን ታምሜያለሁ፡፡ ለአይኔ መነፀር እንደሚያስፈልግ ቢታወቅም ህክምና እንዳላገኝ ተከልክያለሁ፡፡›› ሲል ቅሬታውን አቅርቧል፡፡
አቃቤ ህግ የተለየ መብት እንደተሰጠው፣ ካለ አግባብ ጥያቄዎችን እንደሚያቀርብና ምስክሮችንም በጊዜው ማቅረብ እንዳልቻለ በተደጋጋሚ አቤቱታ ያቀረቡት የተከሳሽ ጠበቃ ‹‹አቃቤ ህግ ችሎቱን እየመራው ነው›› ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡ በመጨረሻም የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት የአቃቤ ህግን ቀሪ 6 ምስክሮች ለመስማት ለህዳር 13/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የኢትዮጵያ አገር አንድ በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄን ምስረታ በማስመልከት የወጣ ድርጅታዊ መግለጫ

Birhanu
(ማክሰኞ ጳጉሜ 3 2007 ዓ.ም)
የኢትዮጵያ ህዝብ የአገሩን ሉአላዊነት እና አንድነት አስከብሮ የኖረ ብቻ ሳይሆን አፍሪካዊያን ወንድሞቹና እህቶቹ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ እንዲወጡ የራሱን አስተዋፅኦ ያደረገ ጀግና ህዝብ ነው፡፡ ሆኖም ይህ ጀግኛ ህዝብ ከአብራኩ በወጡ ገዥዎች ነፃነቱ ተገፎ፣ መብቶቹ ተረግጠው የመከራ ኑሮ እየገፋ አያሌ ዘመናት ኖሯል፡፡ ይህ የመከራና የሰቆቃ ኑሮ ዛሬም አላበቃም፣ እንዲያውም “ከጭቆና ነፃ አወጣንህ” እያሉ የሚሳለቁበት ግፈኛ ገዥዎች የጫኑበትን የስቃይ ቀንምበር ተሸክሞ የውርደት ኑሮ እየኖረ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ የአገር ውስጥ ገዥ መደቦች የጫኑበትን የስቃይና የመከራ ቀንበር ሰባብሮ ለመጣል፣ ፍትህ፣ ሰላምና እኩልነት የሰፈነበት ኑሮ ለመኖር ዓመታት የፈጀ ከፍተኛ መስዋዕትነት የተከፈለበት ትግል አድርጓል፡፡ እስካሁን ትግሉን በአሸናፊነት ተወጥቶ የናፈቀውን ፍትህ፣ ሰላምና ብልፅግና ማግኘት አልቻለም፡፡ ለዚህ በርካታ ምክንያቶች ያሉት ቢሆንም ዋናው ምክንያት ህዝባዊ ትግሉን በተባበረና በተቀናጀ መልክ መስራት አለመቻሉ ነው፡፡ ይህ ስር የሰደደ ያለመተባበር ችግር በህወሓት/ኢህአዴግ ዘመን ተባብሷል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ሆን ብሎ የፈጠረው የመለያየት እና የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ ለጋራ ድል አብሮ መታገልን በጭራሽ አስቸጋሪ ጉዳይ አድርጎት ቆይቷል፡፡
ዛሬ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል፡፡ በጋራ አብሮ በመታገል የሚገኘው ዘርፈ ብዙ ጥቅም የገባቸውና ካለፈው ተደጋጋሚ የታሪክ ስህተት የተማሩ፣ በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲመሰረት በምድር ላይ በመንቀሳቀስ ላይ ያሉ አራት ድርጅቶች በጥምረጥ ተሳስረው በጋራ ለመታገል ወስነዋል፡፡ እነዚህ አራቱ ድርጅቶች ለብዙ አመታት የአብሮ መታገል ፍላጎት እንቅፋት የሆነውን የገዢ መደቦች የከፋፍለህ ግዛው ሴራ በጣጥሰዋል፡፡ ይህ ዛሬ በጥምረት የተጀመረው ትብብር እያደገ ሄዶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ውህደት እንዲያድግ ይደረጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ንቅናቄው ከሌሎች ለዴሞክራሲ ስርዓት መመስረት ከሚታገሉ ኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች ጋር ተጣምሮ ለመስራት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይገፋበታል፡፡
በዚህም መሰረት፣
1ኛ) የአፋር ድርጅቶች የጋራ ንቅናቄ
2ኛ) የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣
3ኛ) የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ እና
4ኛ) አርበኞች ግንቦት 7 ለአድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ፣
የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ (በአጭሩ “የአገር አድን ንቅናቄ”) የሚባል ድርጅት ዛሬ በአዲስ ዓመት መባቻ ጳጉሜ 3 ቀን 2007 ዓ.ም ፈጥረዋል፡፡ የንቅናቄውን ምክርቤት፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴና የተለያዩ መምሪያዎችን ከማቋቋሙም በላይ ዶክተር ብርሃኑ ነጋን ሊ/መንበር፣ ታጋይ ሞላ አስገዶምን ም/ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡
የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ ከአራቱ አባል ድርጅቶች የተውጣጣ አገር አድን ሰራዊት አቋቁሟል፡፡ይህ አገር አድን ሰራዊት በሚያደርጋቸው የትግል እንቅስቃሴዎች ሁሉ የአራቱ አባል ድርጅቶች ሰራዊቶች አባላት ሁሌም ከጎኑ አብረው በመሰለፍ ይታገላሉ፡፡
ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት ከህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ በሰላማዊ መንገድ ለመገላገል የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፣ ሁኖም ለእነዚህ ጥረቶች ከአገዛዙ የተገኘው ምላሽ እስር፣ ስደት፣ ውርደትና ሞት ብቻ ነው፡፡ ይህ በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይወድ የህዝባዊ አመፅ አማራጭን እዲቀበል ተገዷል፡፡ በዚህም ምክንያት አሁንም ለሰላም የዘረጋውን እጅ ሳያጥፍ የህወሓት/ኢህአዴግን አገዛዝ በህዝባዊ አመፅ ለማስወገድ እንቅስቃሴውን ጀምሯል፡፡
በጋራ የሚደረገው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በትግሉ ሜዳ ከሚደረገው ሕዝባዊ አመጽ በተጨማሪ የፖለቲካ፣የዲፕሎማሲና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፎችን ያካተተ ይሆናል፡፡ ይህ አዲስ ጅምር የህወሓት/ኢህአዴግን አገዛዝ ዕድሜ ለማሳጠር በሚደረገው ሕዝባዊ ትግል ውስጥ የመጀመሪያውና ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን በዚህ አዲስ ጅምር ውስጥ አገር አድን ሰራዊቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉያ ውስጥ እየገባ፣ ዕዝብን እያነቃና እያደራጀ ወገኑ ከሆነው ሕዝብ ጋር የሚያደርገው የትግል እንቅስቃሴ በመጪው አዲስ ዓመት በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል፡፡
የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ አገር አድን ሰራዊት መመስረቱን በዚህ መግለጫ ሲያሳውቅ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎኑ እንዲቆም ያደርጋል፡፡እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሰብዓዊ መብቶቹና ነፃነቱ ተከብረው በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም ሰርቶ መኖር የዜግነት መብቱ እንጂ የገዢዎች ችሮታ አለመሆኑን ማስመስከር አለበት፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያንን ለእስራት፤ለስደትና ለሞት የዳረገን የውርደት ኑሮ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ማብቃት አለበት፡፡
ይህንን ብሩህ ዓላማ እውን የሚያደረግ ሁለንተናዊ የአገር አድን ትግል ተጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያ ገበሬ ሆይ !
መሬት የህዝብ ነው እየተባልክ ህወሓት/ኢህአዴግ ሲያሰኘው አንተንና ቤተሰብህን ከመሬትህ እያፈናቀለና መሬቱን ለባእዳን እየሸጠ፤ አለዚያም በገዛ መሬትህ ላይ እንደ ገባር ተቆጥረህ አገሪቱ የዝናብ እጥረት ባጋጠማት ቁጥር የዕርዳታ ሰጭዎችን እጅ ተመልካች ሆነሃል፡፡
ዛሬ ልጆችህ በአገር አድን እንቅስቃሴ ዙሪያ ተሰባስበው ከዚህ የውርደት ኑሮ ነፃ ሊያወጡህ ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ይህ ትግል አንተ በምትኖርበት አካባቢ፣በአንተ ድጋፍና አንተም ተሳትፈህበት የሚደረግ ትግል ነው፡፡ ስለዚህ ልጆችህ ከህወሓት/ኢህአዴግ ጋር በሚያደርጉት ትንንቅ መሸሸጊያ ጫካቸው አንተ ነህ፡፡ ውሃ ሲጠማቸው ውሃ እያጠጣህ፤ ሲርባቸው ቤት ያፈራውን እያበላህ፤ ይህንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚደረግ የመብት፣ የነፃነትና የእኩልነት ትግል ከልጆችህ ጋር አብረህ እድትታገል በአገር አድን እንቅስቃሴ ዙሪያ የተሰባሰቡ ልጆችህ አገራዊ ጥሪ ያቀርቡልሃል፡፡
የኢትዮጵያ ወጣት ሆይ!
“የወደፊቷ ኢትዮጵያ ተረካቢ ነህ” እየተባለ በተደጋጋሚ እየተነገረህ ነው፡፡ አንተ በራስህ ዓይን እደምትመለከተው የዛሬዋም ኢትዮጵያ ለአገርና ለህዝብ ደንታ በሌላቸው ሰዎች እጅ ገብታ እፈረሰች ነው፡፡ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ከህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ነፃ ካልወጣች የነገዋ ኢትዮጵያ አትኖርም፡፡ የነገዋን ኢትዮጵያ የመገንባት ባአንተ በወጣቱ ጀርባ ላይ የወደቀ ኃላፊነት ነው፡፡ ይህ ስራ የሚጀምረው ህወሓት/ኢህአዴግን ከስልጣን በማባረር ነው፡፡ የስደት ኑሮ አብቅቶ በገዛ አገርህ ውስጥ ባሰኘህ ቦታ ያሰኘህን ስራ እየሰራህ የክብር ኑሮ የምትኖርበትን ጊዜ አንተው ራስህ ታግለህ ማምጣት አለብህ፡፡ ስለዚህ ዛሬ ራሳቸው አደራጅተው ከህወሓት/ኢህአዴግ ጋር ከሚፋለመው የአገር አድን ሰራዊት ጋር ዛሬውኑ ተቀላቀል፤ ይህንን ማድረግ የማትችል ደግሞ በምትኖርበት ቦታ ከምታምናቸው ጓደኞችህ ጋር ሆነህ ራስህን እያደራጀህና የመረጃ ማሰባሰብ ስራዎችን እየሰራህ በየአካባቢህ የሚገኘውን የህዝባዊ እቢተኝነት ቡድን ተቀላቀል፡፡
በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የምትታገሉ ድርጅቶች ሆይ !
ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ተገንብቶ ማየት የሚሹ የተለያዩ ድርጅቶች ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን ከመያዙ በፊትና ሥልጣን ከያዘም በኋላ በርካታ ዓመታት የፈጀ እልህ አስጨራሽ ትግል አካሂደዋል፤ዛሬም እያካሄዱ ነው፡፡ ይህ በተናጠል እየተካሄደ ያለው ትግል በመካከላችን የልዩነትና ያለመተማመን አጥር ሰርቶ ስላራራቀን ህወሓት/ኢህአዴግን ማሸነፍ ቀርቶ ጠንካራ ጡንቻ እንድናሳርፍበት እንኳን አላስቻለንም፡፡ ይልቁንም የምንታገልለት ህዝብ በየቀኑ ይታሰራል፤ ሰቆቃ ይደርስበታል፤ ይገደላል፡፡ ከዚህ ሁሉ ያመለጠው ደግሞ አገሩን ለቅቆ ይሰደዳል፡፡ በመካከላችን ያሉትን መለስተኛ ልዩነቶች ለህዝብ አቅርበን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት እስከተማመን ድረስ የአሁኑ ትግላችን ይህንኑ ለማድረግ ነውና ለዚህ እንቅፋት የሆነብንን የህወሓት/ኢህአዴግ ሥርዓት አብረን የማንታገልበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ስለሆነም ሁላችንም ፍሬያማ ለሆነ ትብብር ራሳችንን እናዘጋጅ፤እንተጋገዝ፡፡
የኢትዮጵያ ምሁር ሆይ !
አገራችን ኢትዮጵያ ሁለት እጆቿን ዘርግታ ከምንግዜውም በላይ ያንተን የምሁር ልጆቿን የነቃ የትግል ተሳትፎ የምትፈልግበት ጊዜ አሁን ነው፡፡የኢትዮጵያ ምሁር ለኢትዮጵያ ሕዝብ መብትና ነፃነት መከበር ከፍተኛ አስታውጽኦ አድርጓል፤ ግን ይህ በአብዛኛው በተናጠል አንዳዴም ድርጅታዊ መልክ ይዞ የተካሄደው ትግል የኢትዮጵያን ሕዝብ መብትና ነፃነት ማስከበር አልቻለም፡፡ በዚህ ተስፋ ቆርጠህ ከዳር ቆመህ የአገርህን ውርደት ዝም ብለህ እያየህ ከነበርክ ይህ ከዳር ሆኖ የመመልከቻ ጊዜ አሁን አብቅቷል፡፡ ስለዚህ አገር ውስጥና አገር ውጭ የምትኖረው ኢትዮጵያዊ ከወንድሞችህና እህቶችህ ጋር በመሆን ይህን የተቀጣጠለ ሕዝባዊ ትግል ተቀላቅለህ ዝንት ዓለም ስተመኝው የነበረውን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመመስረት ድርሻህን እንድታበረክት አገራዊ ጥሪ ቀርቦልሃል፡፡
የህወሓት/ኢህአዴግ አባላት ሆይ!
አንዳንዶቻችሁ ከልባችሁ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የምትታገሉ መስሏችሁ፤ ከፊሎቻችሁ ደግሞ በሁኔታዎች ተገድዳችሁ፤ ሌሎቻችሁ ደግሞ አማራጭ አጥታችሁ ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት ከለየለት የአገር ጠላት ድርጅት ጋር ተስልፋችሁ እናት አገራችሁን ስትበደሉ ቆይታችኋል፡፡ ብዙዎቻችሁ የሕዝብ ስቃይና መከራ ተሰምቷችሁ የበደላችሁትን ሕዝብ ለመካስ አመች ጊዜ እየጠበቃችሁ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ደስ ይበላችሁ! የምትጠብቁት ጊዜ ደርሷል፡፡ መጭው እውነተኛ ዴሞክራሳዊ ስርዓት እናንተንም ነፃ የሚያወጣ ስርዓት ነውና ሁላችሁም በያላችሁበት ትግሉን ተቀላቀሉ፤መቀላቀል የማትችሉ ደግሞ መረጃ በማቀበልና ስርዓቱን ከውስጥ ሆናችሁ በማፍረስ ሕዝባዊውን ትግል ደግፉ ከህሊና እና ከታሪክ ተጠያቂነት ራሳችሁን ታደጉ፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሆይ !
ያንተ ኃላፊነት የአገረህን ዳር ድንበር ከጠላት መጠበቅ ሆኖ ሳለ ህወሓት/ኢህአዴግ በአገርህ አንድነት ላይ የሚሸርባችው ሴራዎች አስፈፃሚ አድርጎህ ጭራሽ ደህንነቱን ለመጠበቅና ለመንከባከብ ቃል ከገገባለት ሕዝብ ላይ መሳሪያህን እንድታነሳ እያደረገህ ነው፡፡ አንተ የወጣኸው ከኢትዮጵያ ሕዝብ አብራክ ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ወልዶ ባሳደገህ ወገነህ ላይ “ተኩስ” የሚል ፀረ-ሕዝብ ትዕዛዝ ሲሰጥ በፍጹም አትቀበል፣ ይልቁንም በጠላትህ ህወሓት/ኢህአዴግ ሰርዓት ላይ አዙር ወይም መሳሪያህን እየያዝክ ወገኖችህን ተቀላቀል፡፡ እኛ ወገኖችህ ለነፃነት የምናደርገው ትግል በዘረፋና በሙስና ከከበሩ ዘራፊ ወታደራዊ መሪዎች ነን ባይ ሽፍቶች ጋር ነው እንጂ በፍጹም ካንተ ከወገናችን ጋር አይደለም፡፡ የእኛ ትግል አንተ የአገርህን ዳር ድንበር ለመጠበቅ የሚያስችልህን ብቃት ለመፍጠርና እውነተኛ የሕዝብ ሰራዊት እንድትሆን ለማድረግ ነው እንጂ አንተን ወገናችንን ለመበታተን የመጣን ጠላቶች ወይም አንተን በመግደል የምንደሰት አይደለንም፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ!
አንድን ጨቋኝ አምባገነን ስርዓት ታግለህ በደመሰስክ ማግስት ከቀድሞው የባሰ የሚረግጥህና የሚጨቁንህ ስርዓት በላይህ ላይ እየተጫነ ተቆጥረው የማያልቁ የስድት፣ የሰቆቃና የውርደት ዓመታት ዓሳልፈሃል፡፡ አባቶችህ በደማቸው አስከብረው ያስረከቡህ የአገር አንድነት ላልቷል፤ አንተ ታግለህ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ያወጣሃቸው አገሮች በዕድገት ወደ ኋላ ጥለውህ ሄደዋል፤ የወለድካቸው ልጆችህ እስር ቤት ውስጥ ናቸው አልያም አንተንና አገራችውን ጥለው ተሰደዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! “አምላኬ! አምላኬ! ይህ የመከራና የውርደት ዘመን መቼ ይሆን የሚያበቃው?” እያልክ ሰማይ ሰማዩን እየተመለከትክ ፈጣሪህን ጠይቀሃል፤ ለምነሃልም፡፡ ፈጣሪ አልረሳህም፡፡ የወለድካቸው ልጆችህ ተሰባስበውና ተደራጅተው የናፈቀህን የሰላምና የነፃነት ኑሮ የምታገኝበትን ቀን ለማቅረብ በአገር አድን ሰራዊትነት ተደራጅተው እየተፋለሙ ነው፡፡ የአገር አድን የጋራ ንቅናቄ ዓላማ አገራችን ኢትዮጵያ ፍትህ፣ ሰላምና እኩልነት የሰፈኑባት አገር እንድትሆን ነውና የምትችል በአካል ትግሉ ሜዳ ተገኝተህ በጉልበትህ፤ ይህን ማድረግ የማትችለው ደግሞ በገንዘብህ፣ በእውቀትህና ለዚህ ከጠላትጋር ለሚደረገው ትንንቅ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለወገን ኃይሎች በማቀበል ትግሉን ተቀላቀል፡፡
አንድነት ኃይል ነው!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
Source: Zehabesha

Tuesday, September 8, 2015

አራት የተቃዋሚ ድርጅቶች ጥምረት መመስረታቸውን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች ቀረቡ

ጷግሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስልጣን ላይ ያለውን የኢህአዴግ አገዛዝ በሃይል ለማስወገድ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች " አገር አድን ሰራዊት" ማቋቋማቸውን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየቀረቡ ነው። የአፋር ድርጅት የጋራ ንቅናቄ፣ የትግራይ ህዝብ የጋራ ንቅናቄ፣ የአማራ ዲሞክራሲ ሃይሎች ንቅናቄ እና አርበኞች ገንቦት 7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ በጋራ የአገር አድን ንቅናቄ የሚባል ድርጅት መመስረታቸውን ጳጉሜ 3 ቀን 2007 ዓም ያስታወቁ ሲሆን፣ ንቅናቄው የራሱ ስራ አስፈጻሚና የተለያዩ መምሪያዎች ይኖሩታል ተብሎአል። አዲሱ ንቅናቄ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋን በሊቀመንበርነትና አቶ ሞላ አስገዶምን በምክትል ሊቀመንበርነት መርጧል። ከእነዚህ አባል ደርጅቶች የተውጣጣ አገር አድን ሰራዊት መቋቋሙም ተገልጿል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይወድ በግድ በህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ የሃይልን አማራጭ እንዲቀበል በመገደዱ፣ አገዛዙን ለማስወገድ የጋራ እንቅስቃሴው ተጀምሯል ሲል መግለጫው ያክላል። ንቅናቄው ከሌሎች ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት ከሚታገሉ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ጋር ተጣምሮ ለመስራት ጥረቱን እንደሚቀጥልም ገልጿል። መግለጫውን ተክትሎ ጥምረቱን በአወንታዊ መልኩ የተቀበሉ በርካታ አስተያቶች ለኢሳት በኤሜል መልእክት ደርሰዋል። አንዳንድ ሰዎች ተጨማሪ ማብራሪያ የሚሹ ጥያቄዎችንም ልከዋል። ዜናው አዲስ መነቃቃት የፈጠረና የገዢውን ፓርቲ እድሜ ለማሳጠር ወሳኝ ምእራፍ መሆኑን የሚገልጹ በርካታ አስተያየቶች ሲቀርቡ፣ ኦነግና አብነግ ለምን አልተካተቱም የሚሉ ጥያቄዎችም ቀርበዋል። አንድ አስተያየት ሰጪ " ወያኔ የተባለ ሃገርን ከፋፋይ የፖለቲካ ነቀርሳ ነቅሎ ለመጣልና ለማሸነፍ ለሚደረግ ትግል አቅም የተፈጠረበትን የፖለቲካ ድርጅቶች የአንድነት ዓላማ ትብብር ዜና ከመስማት የበለጠ የሚያስደስት የታሪክ አጋጣሚ ለማከፈል ከመታደል የበለጠ አስደሳች ነገር ሊኖር አይችልም!!! ብራቦቦቦቦቦቦ ለፕ/ር ብርሃኑ ነጋና ለሌሎች ሃገር ወዳድ ፖለቲከኞች!!!!! ቪቫ ለመረጃ ምንጫችን ኢሳት" የሚል መልእክት ሲልክ፣ ሌላው የስርዓቱ ደጋፊ ነኝ ያለ ሰው ደግሞ " ተልባ ቢንጫጫ ባንድ ሙቀጫ እንዲሉ በገባችሁበት ገብተን እንደመስሳችሁዋለን" ብሎአል። "የኦሮሞ ፖለቲከኞች በጥምረቱ አለመካፈላቸው አሳዝኖኛል፣ ለወደፊቱም ተጣምረው ይታገላሉ" የሚል ተስፋ አለኝ ሲል ዱኪ የተባለ አስተያየት ሰጪ ጽፏል። የህወሃት ደጋፊ የሆኑ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ገዢው ፓርቲ " ሳይቀጠል በቅጠል" የሚል ብሂል በመጥቀስ ኢህአዴግ እርምጃ እንዲወስድ እየጠየቁ ነው። ካለፉት ሶስት ወራት ጀምሮ አርበኞች ግንቦት7ትን ለመቀላቀል ጥያቄ የሚያቀርበው ወጣት ቁጥር እንዲሁም ድርጅቱን ለመርዳት የባንክ አካውንት የሚጠይቀው በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የድርጅቱ አመራሮች ይናገራሉ። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ዜጎች ትግሉን በአካል እንቀላቀል የሚል ጥያቄ ከማቅረብ ውጭ፣ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መረጃዎችን እየጠየቁ በመሆኑ ድርጀቱ በቅርቡ መረጃ እንደሚሰጥ አመራሮች ይገልጻሉ። ገዢው ፓርቲ ጥምረቱ ስላወጣው መግለጫ ምንም ያለው ነገር የለም። ይሁን እንጅ የኤርትራ መንግስት በህወሃት በኩል የጦርነት ነጋሪት እየተጎሰመ መሆኑን የሚገልጽ ማስጠንቀቂያ አዘል መግለጫ አውጥቷል። በኤርትራ በኩል ይህ ነው የሚባል ወታደራዊ ዝግጅት ወይም ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደማይታይ የኤርትራ ምንጮች ይገልጻሉ።

Source: ethsat