Saturday, July 27, 2013

ወያኔ መጅሊሱ ህዝቡን እንዲቆጣጠርለት ይፈልጋል

     ወያኔ መጅሊሱ ህዝቡን እንዲቆጣጠርለት ይፈልጋል



"ወያኔ ይህ ሁሉ ሚሊዮን ሙስሊም የሚቃወመውንና ‹‹አይወክለኝም!›› የሚለውን 

መጅሊስ ይዞ ምን ሊያደርግ እንዳሰበ ለብዙዎች ግራ ነው። ከዚህ ሁሉ ህዝብ ጋር 

የተጣላና የሚጠላ መጅሊስ እቅዶቹን የሚያስፈጽመው እንዴት አድርጎ ይሆን? ወያኔ 

መጅሊሱ ህዝቡን እንዲቆጣጠርለት ይፈልጋል፤ ኹጥባ እንኳ ከመጅሊሱ እጅ 

እንዳይወጣ መፈለጋቸውን ግልጽ አድርገዋል። ሚሊዮኖች እየተቃወሙት ግን 


ሙስሊሙን የማስቆጣት እንጂ የመቆጣጠር ስራ ሊሰራ እንደማይችል ግልጽ ነው። 

በአጭሩ አቅም የለውም፤ ህዝብ አንቅሮ  ተፍቶታልና! ታዲያ ወያኔ እንዲህ አይነቱን 

አቅመ ቢስ መጅሊስ ከሚስቀምጥ ህዝቡ በትክክል የሚያምናቸውን መሪዎች መርጦ 

ከነሱ ጋር መደራደር  አይሻለውም ኖሯልን? በአፈሙዝ ታጅቦ የመጣው የአህባሽ 

አመለካከት በህዝቡ  አንቅሮ ተተፍቷል። በሁለት እግሩ ተደላድሎ ሊቆም 

የሚችልበትም እድል የለውም። 


የሚሊዮኖች ጆሮ የሚጠየፈውን ነገር በግድ ልጫን ቢባልም ህዝቡ በግልጽ 

‹‹እምቢ!›› ብሏል። ሃይማኖት በሰዎች ልብ ውስጥ የሚኖር ከሆነ እኛ 

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አህባሽን በልባችን ቦታ ነፍገነዋል። ታዲያ ልባችን ዝግ 

ከሆነ የትኛው ቦታ ላይ ይሆን መቅደሱን የሚያንጹለት?"

No comments: