Saturday, January 30, 2016

ማን ነው ተጠያቂው ? – ግርማ ካሳ

Ethio Prlama
Ethio Prlama
በፓርላማ ዉስጥ ካሉት ከ547ቱ የፓርላማ አባላት ዉስጥ ከትግራይ ክልል የሆኑት 38 ብቻ ናቸው። በኢሕአዴግ ፖሊት ቢሮና በኢሕአዴግ የማእከላዊ ኮሚቴ ዉስጥ ከሕወሃት የሆኑት አንድ አራትኛ ብቻ ናቸው። በሚኒስትሮች ምክር ቤት ዉስጥ ከትግራይ የተወከሉት የማውቃቸው ሶስት ብቻ ናቸው ( ዶር ቴዎድሮስ አዳኖም፣ ዶር ደብረ ጽዮን እና ማንነው ያ ስለጥንቆላ የሚያወራው ጌታቸው ረዳ)
ታዲያ እንዴት ነው ሕወሃት ብቻ፣ በአገሪቷ እየተፈጠረ ላለው ቀዉስ ተጣያቂ የሚሆነው ? የፓርላማው ቃለ ጉባኤ አባ ዱላ አይደሉም እንዴ ? ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወላይታው ሃይለማሪያም ደሳለኝ አይደሉም እንዴ ? አባ ዱላና አቶ ኃይለማሪያም በሕጉ መሰረት በአገሪቷ አንደኛ እና ሁለተኛ የሚባሉት ትላልቅ ስልጣናት ያላቸው አይደለም እንዴ ? (አንዱ የ executive branch ሌላው legislative branch መሪዎች)
አንዳንድ ሰዎች ህወሃት ደህንነቱን እና መከላከያውይን ተቆጣጥሯል ይላሉ። አዎን ልክ ነው። ግን አቶ ኃይለማሪያም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ናቸው። በማናቸውም ጊዜ የጦር ኃይሎች የ ኤታ ማጆር ሹም የሆኑትን ጀነራል ሶሞራን እና የደህንነቱን ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ በሕጉ መሰረት መሻር ይችላሉ። አባ ዱላም በፓርላማ አስጠርተው፣ እነ ሶሞራን እነ እነ ጌታቸውን ተጠያቂ ማድረግ ይችላሉ። ( oversight እንደሚላበው)
ወደ ክልል ሲኬድ ደግሞ የክልል አስተዳዳሪዎች በኦሮሚያ እነ ሙክታር፣ በአማራው ክልል እንደ ገዱ አናዳርጋቸው አይደሉም ወይ ?
እንግዲህ አስቡት፣ ብአዴን እና ኦህዴድ ከኢሕአዴግ ግንባር ወጥተው፣ የራሳቸው ግንባር ቢፈጥሩ ፣ በሕጉ መሰረት በፓርላማ ማጆሪቲ ስለሚኖራቸው ፣ አዲስ መንግስት ሊመሰርቱ ይችላሉ።
በኔ ግምት፣ የትግራይ ህዝብ ብቻ ነው ህወሃትን በቀጥታ ቢከስና ቢቃወም የሚያምርበት። ለምን ቢባል፣ በዚያ እየገዛ ያለው ህወሃት ስለሆነ ነው። በተቀረው ኢትዮጵያ ክልሎች ግን 100% ሊጠየቁ የሚገባው ከሕወሃት ዉጭ ያሉ የኢሕአዴግ ድርጅቶችና አጋር ደርጅቶች ናቸው ።
የሚካድ አይደለም። ህወሃት በብዙ ቦታዎች እጁ አለበት። ግን እጁ እንዲኖርበት የፈቀዱት ከሕወሃት ዉጭ ያሉ ደርጅቶች ናቸው። ለምሳሌ በሕወሃቶች የተሞላውና የ”አገር ደህንነትና የጸረ-ሽብር ግብረ ኃይል” ብሎ ራሱን የሚጠራ አሸባሪው ቡድን፣ በኦሮሚያ ግፍና ጭካኔ ሲፈጽም፣ የክልሉ ጨፌ አንድ አቋም ቢወስድ ኖሮ፣ እነ አቶ ሙክታር አቋም ቢወስዱ ኖሮ፣ አባ ዱላ በአስቸኳይ ፓርላማዉን ጠርተው እነ ሳሞራን አስጠርተው ቢጠይቁ ኖሮ፣ ይሄ ሁሉ ሰው ሰው አይሞትም ነበር። ሕዝቡ ያሳያዉን ድፍረት አንድ አስረኛ እንኳን የኦህዴድ ከፍተኛ አመራር አባላት ቢያሳዩ ኖሮ፣ ሌላው ይቅር በአስቸኳይ የአጋዚ ጦር ከኦሮሚያ ካልወጣ ከኢህአዴግ ግንብር እንወጣለን የሚል ማስጠንቀቂያ ቢሰጡ ኖሮ፣ ነገሮች አሁን ባለው መልኩ አይቀጥሉም ነበር።
- Source: satenaw

Saving Ethiopia from Bloodshed, By Owei Lakemfa

Flag_of_Ethiopia
Flag_of_Ethiopia
…the country can still avoid catastrophe by the government employing dialogue and making concessions. For instance, if it must go ahead with its Addis Ababa Master Plan, it needs to negotiate with the owners of the lands to be affected. Labeling the farmers and students leading those protests as terrorists and using that as a pretext to physically eliminate them is dangerous. Also, the Tigray-dominated government, nominally led by Prime Minister Hailemariam Desalgn (who is from Southern Ethiopia), need to relax the rules in the country and allow fundamental human rights to reign.
Ethiopia is primarily in the news this week, but not because it is hosting the on-going African Union (AU) Heads of State Summit. Rather, it is about two worrying developments. The advancing drought for which needed international funds are in short supply and an estimated 350,000 newborns being expected in drought-affected communities between March and August, 2016. The other reason is the renewed violent protests by the Oromo in which 140 souls have been dispatched by security forces to early graves.
The protests are not coming to me and other Ethiopia watchers as a surprise. I told myself in 2013, after a visit to the holiday resort town of Debre Zeyit, a picturesque haven with five crater lakes, that violent reaction was not far from the surface. At the resort, I got confused after realising that I was actually in Bishoftu, and the signboards were there to announce where I actually was. My confusion was cleared when I was educated that the two names were for one and the same town. The official name for many years, Debre Zeyit is Amharic, which is the official language of the country, while the inhabitants who are Oromo insist on the traditional name, Bishoftu. I dug deeper and found out that all the way from the resort to Addis Ababa, the capital, shops and businesses have two names; one written in the official language, and the other in Oromo. This was a show of Oromo nationalism. The Oromo, who constitute 40 percent of the Ethiopian population, feel marginalised, oppressed and repressed. They think their language and culture have been relegated to the background.
The immediate trigger of the protests is the government decision to implement an Addis Ababa Master Plan which would further expand the capital and develop the outlining farmlands near it into a business zone. But the Oromo who own these lands will have none of it. They see the plan as an attempt by other ethnic groups to seize more of their lands. The protesting Oromo have not forgotten that they were the original owners of the capital before they were conquered by the Christian Abyssinian Kingdom, which then moved its capital to Oromo land, and established Addis Ababa in 1886.
Feeling increasingly marginalised, the Oromo bided their time for the return to democratic rule under which they hoped to use their numerical strength to gain political power… In the 1995 and 2000 elections, the ruling party won easily amidst claims by the opposition that force, intimidation and rigging gave the winners victory.
To be sure, Ethiopia is a very complex country. For many years, the Amharic who are 30 percent of the population, ruled, first as a monarchy and later as a military junta under Colonel Mengistu Haile Mariam. The Tigrayans who constitute 15 percent were regarded as the warriors, while the Oromo felt left out. From the rule of Emperor Haile Selassie (said to be actually of Oromo parentage) to Mengistu, there was an armed rebellion by three component parts of the country. The Oromo had in 1973 founded the Oromo Liberation Front (OLF) with the objective of winning self-determination for their people. The Tigrayans founded the Tigrayan Peoples Liberation Front (TPLF) while the Eritreans founded the Eritrean Peoples Liberation Front (EPLF). The combined forces and pressure of the three groups were too much for the Mengistu regime, which gave way.
With that collapse, the Eritreans gained independence and became a separate country while the Tigray-dominated Ethiopian Peoples Revolutionary Democratic Front (EPRDF) led by Meles Zenawi Asres, pushed into the country and seized power. With that, the power equation in the country changed, with the Tigrayans becoming the new ruling group.
Feeling increasingly marginalised, the Oromo bided their time for the return to democratic rule under which they hoped to use their numerical strength to gain political power. There was also understandable disaffection amongst the Amharic. In the 1995 and 2000 elections, the ruling party won easily amidst claims by the opposition that force, intimidation and rigging gave the winners victory.
Freedom of expression and press freedom are observed more in the breach and many Ethiopians have left the country to do menial jobs, mainly in the Middle East where they have no labour rights. Many have also embarked on the perilous journey of crossing the Mediterranean Sea in overcrowded, makeshift boats to seek refuge in Europe.
However, the 2005 elections were different. The opposition, led by the Coalition for Unity and Democracy (CUD), made a very strong showing and believed it had won the elections. The CUD, for instance, won all the 23 seats in Addis Ababa and made good showing in the Oromo, Amharic and Southern areas. The official election results however gave a different narration; the ruling party had 327 seats, its allies, 40 seats, while the opposition seats increased from 12 in the previous elections to 174. The official results triggered street protests in November 2005 in which security forces allegedly gunned down hundreds of persons. The government followed up with the mass arrests of the opposition including the Mayor of Addis Ababa, local election observers and thirteen journalists. They were charged with treason which attracted the death penalty.
The Oromo claimed that between 2005 and 2008, 594 Oromo were extra-judicially executed while 43 disappeared. The renewed protests by the Oromo is therefore not unexpected. Similar protests in April and May, 2014 led to another round of killings.
But it must be emphasised that the challenge in Ethiopia is not primarily about the Oromo; there is marked depression in the country with many, including journalists, fleeing. Freedom of expression and press freedom are observed more in the breach and many Ethiopians have left the country to do menial jobs, mainly in the Middle East where they have no labour rights. Many have also embarked on the perilous journey of crossing the Mediterranean Sea in overcrowded, makeshift boats to seek refuge in Europe.
Now is the time to take a new direction.
But the country can still avoid catastrophe by the government employing dialogue and making concessions. For instance, if it must go ahead with its Addis Ababa Master Plan, it needs to negotiate with the owners of the lands to be affected. Labeling the farmers and students leading those protests as terrorists and using that as a pretext to physically eliminate them is dangerous. Also, the Tigray-dominated government, nominally led by Prime Minister Hailemariam Desalgn (who is from Southern Ethiopia), need to relax the rules in the country and allow fundamental human rights to reign. But if it insists on a continued clamping of the lid on Ethiopians, one day, the lid will blow off and Africa may experience another tragedy with a huge toll on human lives. Now is the time to take a new direction.
Source: Premium Times

በጋምቤላ ግጭት ብዙዎች ተጎድተዋል

በጋምቤላ በተቀሰቀሰ ግጭት ብዛት ያላቸው ሰዎች መገደላቸው ታውቋል ።በአኙዋክና ኑዌር ብሄረሰቦች መካከል ተፈጠረ በተባለው ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች በመሳሪያ፣በገጀራ ተጨፍጭፈውና መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እንዳሉም እሳት ተለቆባቸው መሞታቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ
የክልሉ የመንገድና ትራንስፖርት ምክትል ኃላፊ አቶ ጋዴት ጎኒ ይጠቀሙባት የነበረች መኪና በቦንብ በመጋየቷ ሹፌራቸውን ጨምሮ ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል

Friday, January 29, 2016

የህዝባችን እንባ ለማቆም ሁላችንም አምርረን እንታገል !


def-thumb

ኢትዮጵያ አገራችን ከፍተኛ የሆነ የህልውና ስጋት ተደቅኖባታል። ልጆቿ በያቅጣጫው ዋይታቸውን እያሰሙ ነው። የወያኔ የተበላሸ ስርዓት እና የስግብግብነት ተፈጥሮ ተደማምረው ህዝባችንን በቃላት ሊገለጽ በማይቻል ሰቆቃ ውስጥ ከተውታል። ህሊና ይዘው መፈጠራቸው ጥያቄ ውስጥ እስከሚገባ ድረስ፣ ቅልብ የወያኔ ገዳይ ወታደሮች በኦሮሞ እናቶችና ህጻናት ላይ የፈጸሙት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በረጅሙ ታሪካችን ያላየነውና ያልሰማነው ነው። ባለፉት መንግስታት ለነጻነታቸው የጮሁ ወጣቶች በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸው ታሪክ የመዘገበው ሃቅ ነው፣ ነገር ግን ህጻናትና ታዳጊዎች እጅግ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ግንባራቸውንና ደረታቸውን በጥይት እየተመቱ ሲወድቁ ስንመለከት ይህ በታሪካችን የመጀመሪያ ነው። አለም በፍጥነት እየተለወጠ ባለበት በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መወሰዱ ደግሞ የአገዛዙ ቁንጮዎችንና እነሱን ተከትለው ወደ ጥፋት አረንቋ የሚተሙትን ሁሉ ከሰው መፈጠራቸውን እንድንጠይቅ የሚያደርግ ነው። የኦሮሞ ህዝብ በአጋዚ ወታደሮችና በፌደራል ፖሊሶች በግፍ ለተነጠቀው ልጆቹ ድምጹን ከፍ አድርጎ አልቅሷል፤ ቁጭቱን በቻለው መንገድ ሁሉ ሊገልጸው ሞክሯል። ነገር ግን እስካሁኗ ሰአት ድረስ መገደሉ፣ መታሰሩ፣ መሰደዱ፣ መዋረዱ አለቆመም። አገዛዙ ለአንድ ቀን በስልጣን ላይ ውሎ እስካደረ ድረስ ይኸው ግፍ ይቀጥላል።
የወልቃይት ህዝብ እኛ እንደፈለግን እንጅ አንተ እንደፈለክ አትኖርም ተብሎ ተፈርዶበት ያለፉትን 25 ዓመታት በስቃይ አሳልፏል። አሁንም እንደገናእኛ እናውቅልሃለን እየተባለመከራውን እየበላ ነው። በአካባቢው ያንዣበበው የሞት ደመና እጅግ አደገኛ ነው። እየተረጨ ያለው መርዝ ካልቆመ፣ አካባቢው በአጭር ጊዜ የግጭት አውድማ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። ዘራፊው የህወሃት ቡድን ግጭትን ከማባበስ በተረፈ ችግሩን የማስቆም ፍላጎት አላሳዬም።
በዚሁ አካባቢ የአንድ አገር ሎጆችን ቅማንትና አማራ እያሉ እርስ በርስ ለመከፋፈልና ለማጋጨት ወያኔ እየዘራው ያለው ይጥፋት ዘር እስካሁን ከደረሰው እልቂት በላይ ሌላ እልቂት ይዞ እየመጣ ነው። የአገር ሰላምና ጸጥታ እናስከብራለን ብለው መሳሪያ የታጠቁ ሃይሎች በሁለቱም ወገን ግጭት ለመቀስቀስ ሲዶልቱ፣ ሲያቅራሩና ሲሸልሉ ውለው እያደሩ ነው። ከዚህ ሁሉ የእልቂት ጀርባ ያሉት ዜጎችን ካላጋጩ ውለው ማደር የማይችሉት የወያኔ መሪዎችና ግብረአበሮቹ ናቸው።
የደቡብ ህዝብም ልጆቹን በሞት እየተነጠቀ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ልጆቹም በየእስር ቤቱ ታጉረዋል፡፡ ዛሬ ወደ ኮንሶ፣ አርባምንጭ፣ ቁጫ፣ ሃመር ወዘተ ብንሄድ የምንሰማው ዋይታና ለቅሶ ነው።
የሶማሌው ወገናችን በልዩ ሃይል አባላት የዘረ ፍጅት እየተፈጸመበት ነው፤ አፋሩ ጋምቤላውና ቤንሻንጉሉ ከቀየው እየተፈናቀለ፣ መሬቱን እየተነጠቀ ለሞትና ለዘላለማዊ ድህነት ተዳርጓል።
ይሄ ሁሉ መከራና ግፍ ሳያንስ 20 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ህዝባችን በረሃብ እየተጠቃ መሆኑ በሰፊው እየተነገረ ነው። በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል በተፈጥሮ በሚሳበብ የአየር መዛባት ችግር ምክንያት ባለፈው የምርት ዘመን የተዘራው ሰብል እንዳለ ወድሞአል:: በዚህም የተነሳ በህዝባችን ላይ ያንዣበበው የረሃብ አደጋ እስከዛሬ ካየነው ሁሉ የከፋ እንደሚሆን አለማቀፍ ድርጅቶች እያስጠነቀቁ ነው። ላለፉት 10 አመታት በእጥፍ አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግቤያለሁ እያለ ህዝብ ሲያደነቁርና የለጋሽ አገሮችን ቀልብ ለመሳብ ሲባዝን የኖረው ወያኔ ግን በፈጠራ ታሪክ የገነባው ገጽታ እንዳይበላሽበት ረሀቡን ለመደበቅና የጉዳት መጠኑን ለማሳነስ ብዙ ርቀት ተጉዟል። ያም ሆኖ የችግሩ ግዝፈት እያየለ ሲመጣና ተጎጂዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ወደየ አጎራባች ከተሞች መሸሽ ሲጀምሩ ሳይወድ በግድ ለማመን ተገዷል። በሰሜን ወሎ፣ በትግራይ፣ በአማራ፣ በአፋር፣ በደቡብና በኦሮምያ በድርቁ ምክንያት በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ የሚገኙ እናቶችና ህጻናት ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢመጣም፣ ወያኔ ግን እንደ ኢኮኖሚው ሁሉ እዚህም ላይ የቁጥር ጨዋታ በመያዙ አሁንም ተገቢው እርዳታ ለህዝባችን በጊዜ እንዳይደርስ እየተከላከለ ለህዝብ መከራ ደንትቢስነቱንና ጨካኝነቱን እያሳየ ይገኛል።
ወያኔ በህዝባችን ላይ የደገሰው የሞት ድግስ በዚህ ብቻ አያበቃም። የኑሮ ውድነቱ ጣሪያ በመንካቱ ህዝቡ እያንዳንዷን ቀን የሚያሳልፈው በጣርና በጭንቅ ነው፤ ከጥቂት የወያኔ ባለስልጣናትና ሸሪኮቻቸው ውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ኑሮው ሲኦል ሆኖበታል። ችግሩና መከራው እየከፋ ሲሄድ እንጅ እየቀነሰ ሲሄድ አይታይም። በሚብለጨለጩና የህዝቡን መሰረታዊ የፍጆታ ችግር በማይቀርፉ ስራዎች ላይ በማትኮር ህዝብን በልማት ስም ለመሸንገል ሙከራ ቢደረግም፣ አልተሳካም። ከኑሮ ውድነት በተጨማሪ ስራ አጥነቱ፣ አፈናው ስደቱ እስርና እንግልቱ፤ ሙስናው፣ የፍትህ እጦቱ ወዘተ የአገራችን ህዝብ ኑሮውን በጉስቁል እንዲገፋ አድርጎታል።
አርበኞች ግንቦት 7 አገራችንና ህዝባችን ከዚህ ሁሉ መከራና ስቃይ መውጣት የሚችለው አገዛዙ የዘረጋው የተበላሸ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲዎች ሲለወጡና ከህዝብ፡በህዝብ ለህዝብ የሚቆም የመንግሥት ሥርዓት በአገራችን እውን መሆን ሲችል ብቻ ነው ብሎ ያምናል:: የወያኔ የሥልጣን ዕድሜ በተራዘመ ቁጥር በህዝባችን ላይ የሚደርሰው በደልና ሰቆቃም እንዲሁ እየተራዘመ ይሄዳል:: ህዝባችን ከሚደርስበት ለቅሶና መከራ እንዲገላገል ሁላችንም በያለንበት አምርረን እንታገል::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
አርበኞች ግንቦት7