Friday, August 28, 2015

በፍቃዱ ኃይሉ (ከቂሊንጦ እስር ቤት)



በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ አውሮፓውያን አፍሪካን ለመቀራመት ተሰብስበው ወሰኑ፡፡ ኃያላኑ መንግስታት የየድርሻቸውን ሲወስዱ የኢትዮጵያን አካባቢዎች ለመውረር የሞከረው የጣሊያን መንግስት ነበር፡፡ አውሮፓውያን ወራሪዎች ‹‹ዓላማችን አፍሪካውያንን ከእንቅልፋቸው ቀስቅሶ ማሰልጠን ነው›› ቢሉም እየዋሹ ነበር፡፡ ዋነኛ ዓላማቸው የአፍሪካን ሀብት ለፋብሪካዎቻቸው ጥሬ ዕቃ ማድረግ ነበር፡፡ ሆኖም እግረ መንገዳቸውን አፍሪካውያንን ሀይማኖታቸውን እያስለወጡ ከራሳቸው ጋር ያመሳስሉታል፡፡ ቋንቋ፣ ወግ እና ልማዶችን በማጥናት ዘመናዊ በሚሉት በራሳቸው ቋንቋ፣ ወግ እና ልማድ ይተኩታል፡፡ አፍሪካውያንን ማሰልጠን የሚሉት ይህንን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ከቅኝ ግዛት በኋላ ብዙ አፍሪካውያን የራሳቸውን ቋንቋ፣ ባህል እና ስርዓት ሙሉ ለሙሉ አጥተው በአውሮፓውያን ገዥዎቻቸው ባህል እና ስርዓት እየተዳደሩ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ግን በአንጻሩ ይህንን ወረራ በኅብረት መመከት በመቻሏ ምንም እንኳን ከአውሮፓ ተጽዕኖ ባትተርፍም የተለየ (የራሷን) ባህል እና ወጎችን እንደያዘች አለች፡፡
ኢትዮጵያ የአውሮፓ ወራሪዎችን መመከት የቻለችው ህዝቦቿ በመተባበራቸው ነው፡፡ የጣልያን ሰራዊት አድዋ ላይ ድል ካደረጉት የጦር መሪዎች መካከል ባልቻ ሳፎ (በፈረስ ስማቸው አባ ነፍሶ) ሳይጠቀሱ የማይታለፉ የኦሮሞ ልጅ ናቸው፡፡ ከምንም ተነስተው የጦር ሚንስትር እስከመሆን የደረሱት ሀብተጊዎርጊስ ዲነግዴ (አባ መላ) ለዚህ ደረጃ የበቁት በአድዋ ባሳዩት ጀግንነት እና መለኝነት ነበር፡፡ እርሳቸውም የኦሮሞ ልጅ ናቸው፡፡ ጣልያን ድል ሆኖ መመለሱ ቆጭቶት ከ40 አመታት በኋላ ሲመለስም ወረራውን በመመከት ረገድ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ኦሮሞዎች ተሰልፈው ነበር፡፡ ከነዚህም መካከል የማይዘነጉት እነ ገረሱ ዱኪ እና ጃጋማ ኬሎ ይገኙበታል፡፡ ጀግናው ጃጋማ ኬሎ ፍቀረማርቆስ ደስታ በጻፈላቸው ታሪካቸው ውስጥ ‹‹ኦሮሞ የኢትዮጵያ ግንድ ነው›› ሲሉ ነግረውታል፡፡ እውነታቸውን ነው፡፡ 
የኦሮሞ ህዝብ በብዛት ትልቁ ኢትዮጵያዊ ብሄረሰብ ነው፡፡ የኦሮሞ ታሪክ ከተጻፈው በላይ ትልቅ ነው፡፡ የኦሮሞ ጎሳዎች ይተዳደሩበት የነበረው የገዳ ስርዓት ዴሞክራሲ ለኦሮሞ ህዝብ ባህሉ ነው ያስብላል፡፡ በኦሮሞ ባህል የሰዎች አደረጃጀት የበላይና የበታች የሚለው ብዙም ተቀባይነት የለውም፡፡ በየትኛውም የገዳ ስርዓት የስልጣን እርከን ላይ ያለን ሰው የትኛውም ተራ ሰው መተቸት እንዲችል የኦሮሞ ባህል ይፈቅድለታል፡፡ ይህ ዓይነቱ ባህል የህዝብ መሪዎች ከህዝብ ትችት እንዳያመልጡ የሚያደርግ ስለሆነ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ያስፈልገናል፡፡
የኦሮሞ ህዝብ፣ ምንም እንኳን የብዛቱን ያህል ተጠቃሚ ባይሆንም የኦሮሞ ልጆች በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የስልጣን ተቀናቃኝ ሆነው አልፈዋል፡፡ አንዳንድ ባለታሪኮች ‹ዘመነ መሳፍንት› የሚሉት የኢትዮጵያ ክፍለ ታሪክ በየጁ ኦሮሞዎች ኢትዮጵያ የተመራችበት ዘመን ነው ይላሉ፡፡ ያኔ መናገሻ የነበረችው ጎንደር ከተማ የስራ ቋንቋዋ ኦሮምኛ ሆኖ ነበር፡፡ በሌላ ጊዜ ደግሞ ንግስናውን ያገኙት የአማራ እና የትግሬ ገዢዎች ከኦሮሞ ጦረኞች ጋር ተስማምቶ ለማደር በጋብቻ መተሳሰርን መርጠዋል፡፡ ለምሳሌ ቴዎድሮስ ልባቸው እስኪጠፋ ያፈቅሯት የነበረችው ሚስታቸው የወሎው ኦሮሞ ራስ አሊ ልጅ ተዋበች ነበረች፡፡ አጤ ምኒልክ ያገቡት ‹‹የኢትዮጵያ ብርሃን›› የምትባለውን ዜደኛ የየጁ ኦሮሞ ሴት ጣይቱ ብጡልን ነበር፡፡ …ኦሮሞዎች ኢትዮጵያን በቀጥታ ባልገዙበት ዘመን በተዘዋዋሪ አዝዘውባታል፡፡
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንዳለመታደል ሆኖ ህዝቡ ተመችቶት አልኖረም፡፡ የኦሮሞ ህዝብም የዚሁ ገፈት ቀማሽ ነበር፡፡ መሪዎች በተገላበጡ ቁጥር ለራሳቸው ሲሉ ድሃውን ገበሬ ሲያንገላቱ ኖረዋል፡፡ ነገስታቱ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ከጎናቸው ያልተሰለፈውን ሁሉ በኃይል ያጠቁ ነበር፡፡ ገበሬው ያመረተውን ቆርሶ የማካፈል ግዴታ ነበረበት፡፡ ግብር የበዛባቸው ገበሬዎች ከመማረራቸው የተነሳ የእህል ክምራቸውን የንጉስ ወታደሮች ሊወስዱባቸው ሲመጡ እህሉ ላይ እሳት ለኩሰውበት ይሸሹ ነበር፡፡ ነገስታት በመጡ፣ ነገስታት በሄዱ ቁጥር ድሃው ህዝብ እረፍት ሳያገኝ ኖሯል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ከጥቂቶቹ የስልጣን ተቀናቃኞች በስተቀር ቀሪው ያሳለፈው ታሪክ የፈተና ነበር፡፡ ሆኖም ግን ጭቆናው ዴሞክራሲያዊ (ህዝባዊ) ያልሆኑ መንግስታት ባሉበት ቦታ ሁሉ ብዙሃኑ ላይ የሚጫን ቀንበር ነው፡፡
የኦሮሞ ህዝብ በታሪኩ ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎች ከደቡብ ወደ ሰሜን በመስፋፋት ያልሰፈረበት የኢትዮጵያ ግዛት የለም፡፡ ከሁሉም ህዝብ ጋር ተቀላቅሏል፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች የራሱን ባህልና ቋንቋ ሲያወርስ በሌሎች ቦታዎች ደግሞ ከተስፋፋባቸው አካባቢዎቹ የቀድሞዎችን ነዋሪዎች ባህልና ቋንቋ እንዲሁም ሀይማኖት ወርሷል፡፡ ‹‹ግማሽ ሲዳማ››፣ ‹‹ግማሽ ጉራጌ›› የሲዳማንና የጉራጌን ባህል የወረሱ ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ የወሎ ኦሮሞዎች አማርኛ ቋንቋ እና እስልምና ሀይማኖት ወርሰዋል፡፡ ራያ እና አዘቦዎች ትግርኛ ቋንቋና ክርስትናን ወርሰዋል፡፡ … በዚህ መንገድ ኦሮሞዎች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ተሳስረዋል፡፡ ሶሾሎጂስቱ ዶናልድ ሌቪን የኦሮሞዎች እንዲህ ከሌሎች የመዋሃድ ችሎታ ትልቋን ኢትዮጵያ ፈጥሯል ይላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝቦች አሁንም ከገዥው ጭቆና አልተላቀቁም፡፡ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ልክ እንደ ትላንቷ ኢትዮጵያ የመብት ጥያቄ ያነሱ ልጆች በኃይል ይጨፈለቃሉ፡፡ ይህንን ጭቆና ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች በየራሳቸው መንገድ እየታገሉት ነው፡፡ ይሁን እንጂ በተባበረ ክንድ መታገል ባለመቻላቸው ጭቆናው ሊቆም አልቻለም፡፡ ብዙ የኦሮሞ ልጆች መፍትሄው የኦሮሚያ መገንጠል እንደሆነ ሊያምኑ ይችላሉ፡፡ ኦነግ በቀድሞው ብርታቱ ባይኖርም መንፈሱ አለ፡፡ ብዙዎች የኦነግ መንፈስ የሚሉት ይህንን ‹‹እንገነጠላለን›› የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ ብዙዎች የተሰውለት፣ ብዙዎች የታሰሩለት፣ ብዙዎች የተሰደዱለት ጥያቄ ይሄው ቢሆንም እስካሁን ለውጥ አላመጣም፡፡ በእኔ እምነት ጥያቄው ለውጥ ያላመጣው በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡ አንደኛ ትልቋን ኢትዮጵያ የመሰረተው የኢትዮጵያ ግንድ (የኦሮሞ ህዝብ) እንደቅርንጫፍ እገነጠላለሁ ማለቱ ነበር፡፡ ሁለተኛ ጠላታችን የሆነውን ጭቆና ማሸነፍ የምንችለው በመተባበር እንጂ በመለያየት ባለመሆኑ ነው፡፡
የጣልያን ወረራን ያሸነፍነው በተባበረ ክንዳችን እንጂ በተነጣጠለ ኃይል አይደለም፡፡ አሜሪካ ዓለምን የምትመራው ክፍለ ሀገሮቿ ተባብረው አንድነት ስለቆሙ ነው፡፡ አውሮፓውያን የአውሮፓ ህብረትን የመሰረቱት የአሜሪካን ኃያልነት በህብረት ለመቋቋም ነው፡፡ አፍሪካም ወደ ህብረት እየሄደች ነው፡፡ በህብረታችን ታሪካዊ ጠላታችን ጭቆናን ማሸነፍ ይቻላል፡፡ መገነጣጠል ግን ይብሱን ያደክመን ይሆናል እንጂ አይበጀንም፡፡ የኤርትራ መገንጠል ለኤርትራ ህዝብ ነጻነት አላስገኘም፡፡ የደቡብ ሱዳን መገንጠል ለደቡብ ሱዳናውያን ሰላም አላመጣላቸውም፡፡ የሶማሊያ አንድ ብሄር መሆንና አንድ ሀይማኖት መከተል ከመበጣበጥ አላዳናቸውም፡፡ መዋጋት ያለብን ጭቆናን እንጂ ህብረታችንን አይደለም፡፡
ኦሮሚያን እንገነጥላለን የሚለው ጥያቄ ታላቋ ኢትዮጵያን ለመሰረተው የኦሮሞ ህዝብ ስድብ ነው፡፡ ሽንፈት ነው፡፡ ትግሉ መሆን ያለበት ጠንካራና ነጻ ኢትዮጵያን ለማረጋገጥ ነው፡፡ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ለዚህ ዓላማ (ሌሎች ፖለቲከኞች ባይመቿቸው እንኳ) የዴሞክራሲ ባህላቸውን ተጠቅመው ሊታገሉት ይገባል እንጂ የገነቧትን ትልቋን ኢትዮጵያ ጥለው እንገነጠላለን ማለት የለባቸውም እላለሁ፡፡ የታላቅነት ምስጢሩ ህብረት እንጂ ነጠላነት አይደለም፡፡ በህብረት እናሸንፋለን!

የኢትዮጵያ ‹የፀረ-ሽብርተኝነት› ሕግ ሲዘከር

በዞን ዘጠኝ
ነሃሴ 22 – 2007

ምክር ቤቱ ከሌሎች ጊዜያት የሚለየው በዛ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን የያዘ በመሆኑ ነው - የአወዛጋቢው ምርጫ 97 ውጤት የሆነው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፡፡እናም ለዚህ ምክር ቤት ሲቀርቡ የነበሩ ብዙ ሕጎች በሚቀርቡበት ወቅት ውዝግብ ማስከተላቸው አልቀረም ነበር፡፡ ገዢው ፓርቲ ‹ሕጎቹ ዴሞክራሲን እና ልማትን የሚያሳልጡ ናቸው› እያለ ሲዘምር፤ በምክር ቤት የሚገኙ የተቃዋሚ አባላት ደግሞ ‹ሕጎቹ የገዢውን ፓርቲ ስልጣን ለማራዘም ዜጎችን ለማጥቃት የተዘጋጁ መሳሪያዎች ናቸው› በማለት በተገደበች ደቂቃቸው ይሟገቱ ነበር፡፡
የዚህ ማስታዎሻ መነሻ የሆነው ጉዳይም የተከሰተው አወዛጋቢው ምክር ቤት የአራተኛ ዓመት ስራውን ለማጠናቀቅ አምስት ቀናት ብቻ ሲቀሩት በሰኔ 25/2001 ነው፡፡ በዕለቱ ምክር ቤቱ ከተመሰረተበት 1987 ጀምሮ ካፀደቃቸው ስድስት መቶ ሃምሳ አንድ አዋጆች ጠንካራውን እና እጅግ አወዛጋቢ የሆነውን ሕግ ለማፅደቅ ኮረም ተሟልቶ ስራውን ጀመረ፡፡ ብዙም ሳይቆይ በተለመደው መልኩ በዘጠና አንድ ተቃውሞ፣ በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ እና በሁለት መቶ ሰማኒያ ስድስት የድጋፍ ድምፅ አዋጅ ቁጥር 652/2001ን ‹የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ› በሚል ርዕስ አፀደቀ! ነገር ግን አዋጁ ተግባራዊ የሚሆነው በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ሲወጣ (አዋጅ ቁጥር 3/1987 እንደሚደነግገው) በመሆኑ ወደ ተግባር ለመሻጋገርሁለት ወራት ገደማ ፈጅቶበት በነሃሴ 22/2001 በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ በመውጣት ስራውን ጀመረ!
እንግዲህ በዋናነት ስራውን ከምርጫ2002 ማግስት ጀምሮ ያደረገው ይህ አዋጅ በነጋሪት ጋዜጣ ወጥቶ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ዛሬ ነሃሴ 22/2007 ድፍን ስድስትዓመት ሞላው፡፡ አዋጁ በተለያዩ ዓለማቀፍ የመብት ተቋማት እና ምዕራባዊ መንግስታት እጅግ ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰበት ይገኛል፡፡‹አዋጁ ከሕገ-መንግስቱ አንቀፆች ጋር ይጋጫል› ብለው ምሁራን እየተቹት ይገኛል፡፡ አዋጁ ‹ሽብርተኝነት›፣ ‹ጋዜጠኝነት›፣ ‹ተቃዋሚነት›፣‹ፋኖነት›፣ ‹ጦማሪነት› … የተባሉ ጉዳዮችን አንድ በማድረግ ሁሉንም በመደዳ እያጠቃ ይገኛል፡፡ በመንግስታዊ የመገናኛ ብዙሃንአዋጁን ‹ለመከላከል› ከየትኛውም ሕግ በላይ በዛ ያሉ ዶክመንታሪዎች ተሰርተውለታል (ለምሳሌ አዲስ ግንባር፤ ጀሃዳዊ ሃረካት፤ አዲስ አበባን እንደ ባግዳድ…)፣ አዋጁ ለፀጥታ ተቋማት (ለደህንነትና ለፖሊስ) ሰፊ መብት የሚሰጥ በመሆኑ አዋጁን መሰረት በማድረግ የሚያዙሰዎች እጅግ ከፍተኛ ማሰቃየትና ድብደባ (CITDs) እየደረሰባቸው ይገኛል፤ አዋጁን ለማስፈፀም በሚል ከአዋጁ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ብቻ ለማዬት ‹ልዩ የወንጀል ችሎት› ተቋቁሞለታል (የቀድሞው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የአሁኑ19ኛ ወንጀል ችሎት)፤ አዋጁ ይሻሻል/ይሰረዝ ዘንድ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጥ የሕዝብ ፊርማ ተሰባስቦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ጨምሮ ለተለያዩ የመንግስት አካላት ቀርቧል (እስከ አሁን ድረስ ምላሽ ባያገኝም)፤ አዋጁ ከመቶ በላይ የሚሆኑትን የኢፌደሪ የወንጀልሕግ አንቀፆች (ከአንቀፅ 238 – 353) በተግባር ‹ጥቅም አልባ› አድርጓቸዋል … በአጠቃላይ የኢፌደሪ መንግስት ከተቋቋመበት1987 ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2007 ድረስ ባሉት ሃያ ዓመታት ውስጥ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካፀደቃቸው ወደ ዘጠኝ መቶ የሚጠጉአዋጆች ውስጥ እንደ አዋጅ ቁጥር 652/2001 አስፈሪ አዋጅ አለ ማለት ይከብዳል፡፡
አዋጁ ያልነካው/የማይነካው የስራዘርፍም ሆነ ግለሰብ የለም፡፡
1.     ሕዛባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በተመሰረተ በ10ኛው ወር (ጥቅምት 1968) ፓርቲውን ተቀላቅለው ደርግን ለመጣልየተደረገውን ትግል ዳር ያደረሱት የስልሳ ዓመቱ አቶ አማረ ተወልደ ዛሬ ‹አሸባሪ› ተብለው የአዋጁ ሰለባ በመሆን በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

2.     በምርጫ 1997 ቅንጅትን በመወከል(የኢዴፓ-መድህን አባል የነበረ) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ተወዳድረው በማሸነፍ የምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ አግባው ሰጠኝ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ በፀደቀበት ወቅት አዋጁን አምርረው የተቃወሙ እና የተቃውሞ ድምፅ የሰጡ ሲሆን፤ ለዛ ተቃውሟቸው ምላሽ ይመስላል ዛሬ በአዋጁ መሰረት ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡


3.     የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ጋሕዴን) አባል በመሆን የጋምቤላ ክልል የክልል ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ በኳች ማሞ ደርግን ለመጣል በተደረገው ትግል ውስጥ ተሳታፊ የነበረው እና በአሁኑ ወቅት በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋሕነን) አባል ነህ ተብለው ያለመከሰስ መብታቸው እንኳን ሳይነሳ በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ መሰረት ተከሰው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡


4.     የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባርን (ኦነግ) በ1978 በመቀላቀል እስከ 1985 ድረስ አብሮ በመቀጠል ደርግን የጣሉት እና በ1985 ደግሞ ተሃድሶ በመግባት ወደ ግብርና ሙያጨው የተመለሱት የሃምሳ ሁለት ዓመቱ ዳንኤል አኩማ አሁን በአዋጁ መሰረት ‹የኦነግ አባል ነህ› ተብለው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

5.     ወጣቱ ሃዊ ደላን የፎቶ ሾፕ ጥበብን የተካነ ሲሆን ‹We are Soldiers of the World› የተባለውን የሲሊቬስተር ስታሎንን የፊልም ፖስተር በመውሰድ ራሱን ከኦሳማ ቢንላደን ጋር አስቀምጦ ፎቶውን ኤዲት በማድረግ ፌስቡክ ላይ በመለጠፍ ከጓደኞቹ ጋር ለመቀላለድ ቢሞክርም ይህ ድርጊቱ ግን ከፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ሊያመልጥ አልቻለም፡፡ ሃዊ በአሁኑ ወቅት ‹እኛ የአለም ወታደሮች ነን (We are Soldiers of the World) በማለት በፌስቡክ ዜጎችን ለሽብር ቀስቅሰሃል› ተብሎ በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ አንቀፅ 6 መሰረት ተከሶ በእስር ላይ ይገኛል፤ ጉዳዩም ከባድ ነው በሚል በዝግ ችሎት እየታየ ይገኛል፡፡

6.     የሰባ አምስት ዓመቱ ሽማግሌ ፒሊማንኩዎት የሃያ ስድስት ልጆች አባት ሲሆኑ ስራቸውም በዚህ እድሜያቸው የጋምቤላ ክልል ልዩ ሃይል ምክትል ሃላፊነት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ‹የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄን (ጋሕነን) የተባለ የሽብርተኛ ድርጅትን ትረዳለህ› ተብለው በአዋጁ መሰረት ተከሰው በእስርላይ ይገኛሉ፡፡


7.     የአስራ ስድስት ዓመቱ አብዱ ሃሚዝ በአስራ አንድ ዓመቱ ሱዳን በቆሎ ቆረጣ ስራ በወጣበት በቤሕነን (የቢኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ) ወታደሮች ተጠልፎ ወደ ኤርትራ በመሄድ ኤርትራ ከአምስት ዓመታት በላይ ቆይቶ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ሲሞክር ተያዞ (በዓለማቀፍ ሕግ Child Soldier ቢሆንም)በአዋጁ አንቀፅ 7 (1) መሰረት ተከሶ የአራት ዓመት ፍርድ ተፈርዶበት አሁን በእስር ላይ ይገኛል፡፡ …
እነዚህ ለምሳሌ ያህል ያነሳናቸውጉዳዮች በሚዲያ ከሚዘገቡት የፖለቲከኞች፣ ፀሃፊዎችና ጋዜጠኞች ጉዳይ ባለፈ የምናገኛቸው እና ሕጉ እንዴት እየተገበረ ያለ እንደሆነለማሳየት ያህል ይረዱናል በሚል ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ምሳሌዎች በጣም ትንሽ ሲሆኑ፤ ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ ሕጉ እጅግ ብዙ ዜጎችን ሰለባ አድርጓል፡፡ በዛሬው ዕለትም የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ ሰለባያደረጋቸውን ግለሰቦች ስም ዝርዝር (ሙሉ ዝርዝሩ አልቀረበም)፣ ተያይዘው የተከሰሱበት ድርጅት/ቡድን እና የተከሰሱበትን የአዋጁንአንቀፆች በማስቀመጥ ስለሰለባዎቹ እንነጋገር ዘንድ እንዲህ አቅርበናቸዋል፡፡





የተለያዩ ‹የሽብር ቡድኖችን አቋቁማችኋል›በሚል በፀረ-ሽብርተኘነት አዋጁ መሰረት የተከሰሱ ሙስሊም ግለሰቦች፡


·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 122/05 ‹የመፍትሔአፈላላጊ ኮሚቴ› የሚል ‹የሽብርተኛ ድርጅት› በማቋቋም በሚል ክስ፡

1.     አቡበከር አህመድ ሙሐመድ
2.     አህመዲን ጀበል
3.     መከተ ሙሄ መኮንን
4.     ካሚል ሸምሱ ሲራጅ
5.     በድሩ ሁሴን ኑርሁሴን
6.     ያሲን ኑሩ ኢሳ
7.     ሳቢር ይርጉ ማንደፍሮ
8.     መሀመድ አባተ ተሰማ
9.     አህመድ ሙስጠፋ ሀቢብ
10.   ሙራድ ሽኩር ጀማል
11.     አቡበከር አለሙ ሙሔ (ጋዜጠኛ)
12.   ኑሩ ቱርኪ ኑሩ
13.   ባህሩ ዑመር ሽኩር
14.   ሙኒር ሁሴን ሀሰን
15.   ሰዒድ አሊ ጀውሀር
16.   ዩሱፍ ጌታቸው  (ጋዜጠኛ)
17.   ሙባረክ አደም ጌቱ
18.   ካሊድ ኢብራሒም ባልቻ
19.   አብዱረዛቅ አክመል ሀሰን
20. አሊ መኪ በድሩ
21.   አብሩዱራህማን ኡስማን ከሊል
22.   ሐሰን አሊ ሹራብ
23.   ሱልጣን ሐጂ አማን
24. ጀማል ያሲን ራጁ
25.   ጣሂር አብዱልከድር
26. ሐሰን አቢ ሰይድ
27.   ሐጂ ኢብራሂም ቶይፋ
28. ሀቢባ ሙሐመድ
29. ከማል ሐጂ ገለቱ ማሜ
3 (1, 2, 4 እና 6)፣ አንቀፅ 4 እና 7 (1)




·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 225/06 ‹የመፍትሔአፈላላጊ ኮሚቴ› የተባለ ‹የሽብርተኛ ድርጅት› ጋር ግንኙነት በማድረግ በሚል ክስ፡

1.     ኤልያስ ከድር ሽኩር
2.     ሙባረክ ከድር ሀሰን
3.     ቶፊቅ መሀመድ ዑመር
4.     ፈይሰል አርጋው ኡመር
5.     አብዱልመጅድ አብዱልከሪም
6.     እስማኤል ሙስጠፋ ሀሰን
7.     ሬድዋን አብደላ አህመድ
8.     አንዋር ሱልጣን መሀመድ
9.     አብዱላዚዝ ፋቱደን በድሩደን
10.   ዳፋር ዲጋ ሀሰን
11.     ፋሩቅ ሰዒድ አብዶ
12.   መሪማ ሀያቱ ዑመር
13.   መሀመድ ዓሊ ሀሰን
14.   መሀመድ አይለየን ገማ
15.   አቡበክር ሰልማን ሙሳ
16.   ሙዓዝ ሙደስር አወል
አንቀፅ 7(1)

·        የ/ፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 216/06 ‹የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ› የተባለ ‹የሽብርተኛ ድርጅት› ጋር ግንኙነት በማድረግ በሚልክስ፡

1.     አብዱልአዚዝ ጀማል አብዱ
2.     ጅብሪል ይመር አበጋዝ
3.     ስዑድ ሙሳ ሁሴን
4.     ሀያት አህመድ ረዲ
5.     ሳላሀዲን ሙሀመድ አህመድ
አንቀፅ 7(1)


·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 666/07 ‹የመፍትሔአፈላላጊ ኮሚቴ› የተባለ ‹የሽብርተኛ ድርጅት› ጋር ግንኙነት በማድረግ በሚል ክስ፡

1.     ከድር መሃመድ ዩሱፍ
2.     ነዚፍ ተማም ሙስጠፋ
3.     ኽሊድ መሃመድ አህመድ
4.     ፉአድ አብዱልቃድር አሊ
5.     ኢብራሂም ከማል ኢሳ
6.     አብዱጀባር አብዱላ ኢብራሂም
7.     ሁሴን አህመድ አባደጋ
8.     ሃሚድ መሃመድ ሻፊ
9.     ቶፊቅ ሚስባህ ያሲን
10.   ዑስማን አብዲ መሃመድ
11.     መሃመድ ኑሪ ተሰሙ
12.   አብዱልሃፊዝ ሻፊ ሙቅተባ
13.   ዳርሰማ ሶሪ ባንቀሽ
14.   ፍፁም ቸርነት ኃ/ማሪያም
15.   ሀሩን ሃይረዱን ሃቢብ
16.   ሸህቡዱን ኑረዲን
17.   አያተልከብራ ነስረዲን
18.   ሃሺም አብደላ አወል
19.   ሙጂብ አሚኖ ሰኢድ
20. መሃመድ ከማል አባመልካ
አንቀፅ 7(1)

·        የ/ፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 164/06

1.     አህመድ ኢድሪስ ገበየሁ
2.     አንዋር ኡመር ሰዒድ
3.     ሷሊህ መሀመድ አብዱ
4.     አደም አራጋው አህመድ
5.     አብዱራህማን እሸቱ መሀመድ
6.     ኢብራሒም ሙሔ ይማም
7.     ዑመር ሁሴን አህመድ
8.     ይመር ሁሴን ሞላ
9.     ሙባረክ ይመር አየለ
10.   እስማኤል ሀሰን ይመር
11.     ከማል ሁሴን አህመድ
12.   አብዱ ሀሰን መሀመድ
13.   አህመድ ጀማል ሰይድ
14.   ሙሀመድ ዩሱፍ መሀመድ
አንቀፅ 3 (1 እና 2)

·        ‹አል -ኻዋሪጅ› የተባለ ‹የሽብርተኝነትድርጅት› በማቋቋም በሚል ክስ፡

1.     ጃፋር መሀመድ አባረዳ
2.     መሀመድኑር ግዛው ሀ/ሚካኤል
3.     ሀጂ ሙሀመድ ሳኒ አባዋጂ
4.     ሙህዲን ጀሚል ያሲን
5.     አህመድ አባቢያ አባሪጉ
6.     አንዋር ትጃኔ አባጨብሳ
7.     ሼህ ጀሚል አባጨብሳ አባጎዱ
አንቀፅ 7(1)

·        ‹ፉርቀቱ ልናጀያ ሙስሊም ጀምዓ›የተባለ ‹የሽብርተኝነት ድርጅት› በማቋቋም በሚል ክስ፡

1.     ዙቤር ቢቂላ አባወጃ
2.     ተወከልዬ ግርማዬ ቡልቻ
3.     አወል አበፈጫ አባጨብሳ
አንቀፅ 3(1)(2) እና (4)

·        ‹ፈርቀቱ ልናጀያ ሙስሊም ጀምዓ›የተባለ ‹የሽብርተኝነት ድርጅት› በማቋቋም በሚል ክስ፡

1.     በድሩ አባቦር
2.     መሃመድ አሚን
3.     አወል አባሜጫ
4.     አብዱልአዚዝ አባዝናብ
5.     ጣሂር አባኑራ
6.     ሳቢት ከድር
7.     አወል ሱልጣን
8.     መሃመድ አባጋሮ
9.     አብዱ ሁሴን

አንቀፅ 7 (1) እና (2)

·        ‹አል ሸባብ› የተባለ ‹የሽብርተኛድርጅት› አባል በመሆን በሚል ክስ፡

1.     ሃሰን ጃርሶ ቆቶላ (ኬኒያዊ)
2.     መሃመድ ቃሲም
3.     ዑመር ሙሳ
4.     አብዲሽኩር ዳውድ
5.     በሽር ሃጅ
6.     ዩሱፍ ሃሰን
7.     መሐመድ ሳፊ
8.     ሙስጠፋ ዑመር
9.     አብድራህማን ሁሴን
10.   አብዱል ለጢፍ
11.     ከድር ሙስጠፋ
አንቀፅ 4 እና አንቀፅ 7 (1)

·        ‹አል ሸባብ› የተባለ ‹የሽብርተኛድርጅት› አባል በመሆን እና ሌሎች የሀገር ውስጥ የጅሃድ ቡድኖችን በማቋቋም በሚል ክስ፡

1.     አማን አሰፋ
2.     ኑሪ ሙዘይን አህመድ
3.     ሰለሞን ከበደ (ጋዜጠኛ)
4.     አብዱል ፈታህ ሸሪፍ
5.     ኑረዲን ሙሃመድ አብደላ
6.     ሙፍቲ ሙሃመድ
7.     አንዋር አደም (አሜሪካዊ)
8.     ጀማል ሀሰን አህመድ
9.     ኢብራሂም አብዱ
10.   አህመድ ማሞ
11.     ሙሃመድ አብዱልቃድር
12.   ሙሃመድ ኑር አብደላ
13.   ሰለሃዲን ሰኢድ የሱፍ
14.   ሳዳም አብዱረህማን
15.   ሁሴን ሮባ
16.   አብዱረዛቅ ሸህ አህመድ
17.   እንድሪስ አልይ
18.   እድሪስ አህመድ
19.   ኢብራሂም ኪያ
20. ሙሃመድ አህመድ
21.   አጋሱ ሁሴን
22.   የዚድ ጀማል
23.   ኢብራሂም የሱፍ
24. ጃእፈር
25.   አብዱ አሊ
26. አብዱረህማን ቢላል
27.   ሙሃመድ አህመድ

አንቀፅ 3 (1) (2) እና አንቀፅ 7 (1)




‹የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር› (ኦነግ)አባላት ናችሁ ተብለው በአዋጁ የተከሰሱ ግለሰቦች፡

·        በፌ/ዓ/ሕግ/መ/ቁ 376/06

1.     ጀልዴሳ ዋቆ ጃርሶ
2.     ገልገሎ ጉዮ ቦሩ
3.     ዋርዮ ጣጤሳ ጉዮ
አንቀፅ 3 (1 እና2) እና 7 (1)

·        በእነ አብዲ ከማል የክስ መዝገብ

1.     አብዲ ከማል የሱፍ
2.     ቶፊቅ ረሽድ ዩያ
አንቀፅ 7 (1)

·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 106/07

1.     ዳንኤል አኩማ ፉፋ
2.     አስፋው ልሳና ናደው
አንቀፅ 3(1) እና (4)

·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 35/07

1.     አበበ ኡርጌሣ ፎከንሣ
2.     መገርሣ ወርቈ ፋይሳ
3.     አዱኛ ኬሳ አደሩ
4.     ቢሉሱማ ደመና ስዩም
5.     ተሻለ በቀለ ገርባ
6.     ሌንጅሳ አለማየሁ
አንቀፅ 7(1)፣ 3 (1) (4) እና (6)




‹የዴሞክራሲ ምንቅስቃስ ሕዝቢ ትግራይ›(ዴምሕት) አባላት ናችሁ ተብለው በአዋጁ የተከሰሱ ግለሰቦች፡

·        በእነታሪኩ በላይ ፍስሃ የክስ መዝገብ

1.     ታሪኩ በላይ ፍስሀ
2.     አማረ ተወልደ መነህ
አንቀፅ 7(1)

የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ(ቤሕነን) አባላት ናችሁ ተብለው በአዋጁ የተከሰሱ ግለሰቦች፡

·        በእነ አብዱልከሪም አብዱሰመድ የክስ መዝገብ

1.     አብዱልከሪም አብዱሰመድ አብዱልቃድር
2.     ሀዋጃ ሚነላ አጉር
3.     ኢሳቅ ኢብራሒም ዓሊ (ዕድሜ 17)
4.     አጄላ ጃባላ ንምር
5.     አብዱ ሀሚዝ ፈረንሳ (ዕድሜ 16)
6.     ፋተልሙላ አጣሂር አከሶ
አንቀፅ 7 (1)

·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 168/07

1.     አብዱልወሀብ መሃዲ ኢሳ
2.     አብዱረህማን ናስር አህመድ
3.     ኩርፊል ጀማ ናስር
4.     ያሲር ጀበል ነጉራ
5.     ኢማያ አብዱረዛቅ አብዱላሀ
6.     ደፋኢል መሀመድ አብዱልሃሰን
7.     አደም በዳዊ ባባክር
8.     ሙደወኪል ከሚል ሙባረክ

አንቀፅ 3(1) እና (2)


‹የግንቦት ሰባት ለፍትህና ለነፃነትድርጅት› እና ‹የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር› አባላት ናችሁ ተብለው በአዋጁ የተከሰሱ ግለሰቦች፡

·        በእነ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞየክስ መዝገብ

1.     ጄነራል ተፈራ ማሞ
2.     ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
3.     አንዳርጋቸው ፅጌ
4.     መስፍን አማን
5.     ሙሉነህ እዩኤል
6.     መላኩ ተፈራ
7.     አሳምነው ፅጌ
8.     ሌ/ኮ ደምሰው አንተነህ
9.     ሻለቃ መኮንን ወርቁ
10.   አበረ አሰፋ
11.     ሌ/ኮ ዓለሙ ጌትነት
12.   ሌ/ኮ ሠለሞን አሻግሬ
13.   ሌ/ኮ ጌታቸው ብርሌ
14.   ሻምበል ተመስገን ባይለየኝ
15.   ሌ/ኮ ፋንታሁን ሙሃባ
16.   ሻለቃ መሰከረ ካሣ
17.   ሻምበል ምስጋናው ተሰማ
18.   ክፍሌ ስንሻው
19.   የሽዋስ መንገሻ
20. መንግሥቱ አበበ
21.   እማዋይሽ ዓለሙ
22.   ጎሽይራድ ፀጋው
23.   ሳጅን አመራር ባያብል
24. ምክትል ሳጅን ጎበና በላይ
25.   ረዳት ሳጅን ይበልጣል ብርሃኑ
26. ምክትል ሳጅን የሺዋስ ምትኩ
27.   ውድነህ ተመስገን
28. ጌቱ ወርቁ
29. ፅጌ ኃብተማርያም (ዕድሜ80 ዓመት)
30. ሌተናል ኮሎኔል አለበል አማረ
31.    ያረጋል ይማም
32.    ዳንኤል (ዳን)
33.    አወቀ አፈወርቅ
34.  ኤፍሬም ማንዴቦ
35.    ዳንኤል አሰፋ
36.  ቸኮል ጌታሁን
37.    ፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)
38.  ደረጀ ሀብተወልድ (ጋዜጠኛ)
39.  አዱኛ ዓለማየሁ
40. አደፍርስ አሳምነው
አንቀፅ 3 እና 4

·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 00180/04
1.     አንዱዓለም አራጌ ዋለ
2.    ናትናኤል መኮንን ገ/ኪዳን
3.    ዮሃንስ ተረፈ ከበደ
4.    ሻምበል የሽዋስ ይሁንዓለም
5.    ክንፈሚካኤል ደበበ በረደድ(አበበ ቀስቶ)
6.    ምትኩ ዳምጠው ውርቁ
7.    እስክንድር ነጋ ፈንታ (ጋዜጠኛ)
8.    አንዱዓለም አያሌው ገላው
9.    አንዳርጋቸው ፅጌ
10.  ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንገር
11.    ውቤ ሮቤ
12.   ኤፍሬም ማዴቦ
13.   መስፍን አማን
14.  ዘለሌ ፀጋስላሴ
15.   ፋሲል የኔአለም (ጋዜጠኛ)
16.  አበበ በለው (ጋዜጠኛ)
17.   አበበ ገላው (ጋዜጠኛ)
18.  ንአምን ዘለቀ
19.  ኤልያስ ሞላ
20. ደሳለኝ አራጌ ዋለ
21.   ኮ/ሌ አለበል አማረ
22.  ኦባንግ ሜቶ፣
23.  መስፍን ነጋሽ (ጋዜጠኛ)
24. ዓብይ ተ/ማሪያም (ጋዜጠኛ)
አንቀፅ 3 (1) (2)(4) እና አንቀፅ 5 (1)

·        የፌ/ዓ/ህ/መ/ቁ 071/06  

1.     ማስረሻ ታፈረ ወ/ገብርኤል
2.     ሻለቃ አለምነው አየለ ነጋሽ
3.     ብርቁ አዲሱ ውቡ
4.     ታደሰ መንግስቱ በላይ
5.     የፀዳው ካሴ አሉላ
6.     አወቀ ደስታው ምህረቴ
7.     መሀመድ ግዛቸው ፋንታው
8.     ቴዎድሮስ ሀይሌ
9.     ታደሰ በለጠ
10.   ታደሰ ባዩ ገበየሁ
አንቀፅ 7(1)

·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 382/06

1.     መ/አ/ ጌታቸው መኮንን
2.     በላይነህ ሲሳይ ኮከቤ
3.     አለባቸው ማሞ መለሰ
4.     አወቀ ሞጃ ሆዴፈንታ
5.     ዘሪሁን በኔ ታረፋ
6.     ወርቅዬ ምስጋና ዋሴ
7.     አመረ መስፍን መለሰ
8.     ተስፋዬ ታሪኩ በዛብህ
9.     ቢሆነኝ አለነ ማረው
10.   ታፈረ ፋንታሁን አጉመሌ
11.     ፈጃ ሙሉ ዘገየ
12.   አትርሳው አስቻለው ተካ
13.   እንግዲያው ዋጀራ ወርቁ
14.   አንጋው ተገኝ አርጋው
15.   አግባው ሰጠኝ በሪሁን
16.   አባይ ዘውዴ በቀለ
አንቀፅ 7(1)

·        በእነ ዘመኑ ካሴ በእውቄ የክስ መዝገብ

1.     ዘመኑ ካሴ በእውቄ
2.     አሸናፊ አካሉ አበራ
3.     ደህናሁን ቤዛ ስመኝ
4.     ምንዳዬ ጥላሁን ለማ
5.     አንሙት የኔዋስ አለኸኝ
6.     ደሳለኝ አሰፋ ወንድማገኝ
7.     ም/ኢ/ር ሙልየ ማናየ ረታ
8.     ጠጋው ካሳ እንየው
9.     ይህዓለም አካሉ አበራ
አንቀፅ 4፣ 5 እና 8



·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 033/06

1.     ፀጋው አለሙ ተካ
2.     ዋሲሁን ንጉሱ ገብሬ
3.     ጎዳዳው ፈረደ ማሞ
4.     ማማይ ታከለ በየነ
5.     ተገኝ ሲሳይ መንገሻ
አንቀፅ 7 (1)

·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 174/06

1.     አስማማው ደሴ ጣሰው
2.     መብራታይ ይርጋ ተስፋዬ
አንቀፅ 7 (1)

·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 344/07

1.     መ/አ ማስረሻ ሰጤ ብሬ
2.     መ/አ ብሩክ አናዬ በሪ
3.     መ/አ ዳንኤል ግርማ ካሳ
4.     መ/አ ገዛኽኝ ድረስ ብዙነህ
5.     ተስፋዬ እሸቴ ውበት
6.     ሰይፉ ግርማ ተሰማ
አንቀፅ 7(1)

·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 26/07

1.     ብርሃኑ ተክለያሬድ አሰፋ
2.     እየሩሳሌም ተስፋው እንየው
3.     ፍቅረማሪያም አስማማው ዋለልኝ
4.     ደሴ ካህሳይ ቃልዬ

አንቀፅ 7(1)


·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 582/07

1.     ዘመነ ምህረት ታከለ
2.     ጌትነት ደርሶ አዱኛ
3.     መሰለ መሸሻ አናጋው
አንቀፅ 4 እና 7 (1)
                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                         
·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 324/07

1.     አምሳሉ መስታየት ፀሃይ
2.     ኢሳያስ ማሩ ዓለሙ
3.     ጀጃው አለማየሁ ተፈራ
4.     ወርቁ ዳኘው ተዘራ
5.     አሳመረው አሰፋ እጅጉ
6.     አብነት ደሳለኝ ጫኔ
አንቀፅ 7(1)

·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 300/07

1.     ተረፈ ይታይህ ቢተው
2.     ሙሉጌታ ደምሴ አበበ
3.     ዘላለም እጅጉ ካሳ
4.     ታድለው ፈረደ
አንቀፅ 7(1)

·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 299/07

1.     ሃሰን ዳውድ
አንቀፅ 7(1)

·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 480/07

1.     ለምለሙ በሽሬው በላይ
2.     ት/ሚካኤል ት/ስላሴ ማለዳ
3.     አብዬ ተስፋ ልፎ
4.     እሸቴ ግርማይ በዜ
5.     ሃብታሙ ተረፈ ሙሉነህ
6.     አታሎ ደሳለኝ መኮንን
7.     ዶክተር ባየው አበራ
8.     መልካሙ ታደሰ ነገሰ
9.     ኃ/ማሪያም ገነት ተሾመ
አንቀፅ 7(1 እና 2)

·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 456/07

1.     ዘላለም ወርቅአገኘው (ጦማሪ)
2.     ሃብታሙ አያሌው
3.     ዳንኤል ሽበሺ
4.     አብርሃ ደስታ
5.     የሽዋስ አሰፋ
6.     ዮናታን ወልዴ
7.     አብርሃም ሰለሞን
8.     ሰለሞን ግርማ
9.     ባህሩ ደጉ
10.   ተስፋዬ ተፈሪ

አንቀፅ 4 እና 7 (1)

‹የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር› (ኦብነግ) አባል እና ተሳታፊ በመሆን በሚል ክስ፡

·        በእነማርቲን ሽብ የክስ መዝገብ

1.     ማርቲን ካርል ሽብዬ (ሲዊድናዊ)
2.     ጁሃን ከርል ፐርሰን (ሲዊድናዊ)
3.     አብዲወሊ መሐሙድ እስማኤል
4.     ከሊፍ አሊ ዳሂር

አንቀፅ 3 (1) (2) አንቀፅ 4 እና አንቀፅ 7 (1)


‹የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ› (ጋሕነን) የተባለ የሽብርተኛ ድርጅት› አባል በመሆን የሽብርተኝነት ድርጊትመፈፀም በሚል ክስ፡

·        በእነኡመድ ኡከት ኡመድ የክስ መዝገብ

1.     ኡመድ ኡከት ኡመድ
2.     ኡጁሉ ገመቹ
3.     ፖል ኡመድ
4.     ኡመድ አዴል
5.     ኡጅሉ ባብ
6.     ኡባንግ ኪሩ
7.     ኡራንግ ኡቻን
8.     ኪሩ ኡመድ
9.     አካይ ኦፒዮ
10.   ዋና ሳጅን ኦኬሎ አዋኘንግ ኡሎንግ
11.     ኡመድ ኡኮቾ
12.   አዱኛ ኡማን
አንቀፅ 3 (1) (2) እና (4)

·        በፌ/ዓ/ህ/መ/ቁ 322/06

1.     ኡቺሚ አፐይ ኡቻላ
2.     ኡማን ኡድሉ ቻም
3.     ኡቻን ኡድላ ኦፒዮ
4.     ኡመድ ኡጁሉ ኡማን
5.     ኝበዲ ኡባንግ ኡጃቶ
6.     ኦፒዮ ቹር ኡባንግ
7.     ኡመድ ኡቶ ኡማን
8.     ኡፐዶካ ኡቱን ኝግየው
9.     ታደሰ ኡዱጊ ቲፋ
10.   ኡማን ኡካይ ኡኩችና
11.     ኦኬሎ ኡበር ኡቻን
አንቀፅ 3 (1፣ 2 እና 3)

·        የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ/ 29/07

1.     ፒሊማን ኩዎት አግድ አዷቶ
2.     በኳች ማሞ ኡቶይ
3.     እኛንግ አጃልቡራ
4.     አዱሉ አኮላ
5.     አቶኦ ኡኮላ
6.     ኡጁራ አዋር
7.     ኡመድ ባች ኡዱኣ
8.     ፓቦች ኡመድ ኡባንግ
9.     ኡጁሉ ታታ ኡመድ
10.   ኡማን ኡጋላ ኡቻንግ
11.     ኡመድ አፒየው አኳይ
አንቀፅ 7 (1 እና 2)

‹የጋምቤላ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ› (ጋዴን) የተባለ ‹የሽብርተኛ ድርጅት› በማቋቋም በሚል ክስ፡

·        የፌ/አ/ህ/መ/ቁ 508/06

1.     ኦኬሎ አኳይ ኡቻላ
2.     ዴቪድ ኡጅሉ ኡባንግ
3.     ኡቻን ኦፒዮ ኡሞድ
4.     ኡማን ኝክየው ኡድሉ
5.     ኡጅሉ ቻሞ ኡኮይ
6.     ኦታካ ኡዋር ኡጋላና
7.     ኡባንግ ኡመድ አቦላ
አንቀፅ 4

የተለያዩ ‹የሽብርተኛ ድርጅቶችን› በማቋቋምበሀገር ውስጥ ‹የሽብርተኝነት ተግባር› ሊፈፅሙ ሲንቀሳቀሱ በሚል ክስ፡

·        በነውብሽት ታ የክስ መዝገብ

1.     ውብሸት ታዬ  (ጋዜጠኛ)
2.     ርዕዮት ዓለሙ (ጋዜጠኛ)
3.     ዘሪሁን ገብረእግዚአብሔር
4.     ሒሩት ክፍሌ
5.     ኤልያስ ክፍሌ  (ጋዜጠኛ)

አንቀፅ 4 እና አንቀፅ 7 (1)



·        /ዓ/ሕ/መ/ቁ 05/07

1.     ሶልያና ሽመልስ ገ/ማርያም (ጦማሪ)
2.     በፍቃዱ ኃይሉ ተጫኔ (ጦማሪ)
3.     ናትናኤል ፈለቀ አበራ (ጦማሪ)
4.     ማህሌት ፋንታሁን ተፈራ (ጦማሪ)
5.     አጥናፉ ብርሃኔ አያሌው (ጦማሪ)
6.     ዘላለም ክብረት በዛ (ጦማሪ)
7.     አቤል ዋበላ ሱጌቦ (ጦማሪ)
8.     አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ ግዛው (ጋዜጠኛ)
9.     ኤዶም ካሳዬ ገላን (ጋዜጠኛ)
10.   ተስፋለም ወ/የስ ኤራጎ (ጋዜጠኛ)

አንቀፅ 3 (2) እና አንቀፅ 4


ማስታዎሻ፡


  •     ዝርዝሩ ሙሉ አይደለም፡፡ ሌሎች ተጨማሪ ሰዎችም በፀረ-ሽብርተኝነትአዋጁ ተከሰው የተፈረደባቸው/በነፃ የተለቀቁ አሉ፡፡
  •    በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱት ግለሰቦች በመደበኛ ችሎትየፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀፆች ተጠቅሶባቸው የተከሰሱ ብቻ ናቸው፡፡ ነገር ግን በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ የሚታሰሩእስረኞች የጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት በሚቀርቡበት ወቅት የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ተጠቅሶባቸው የሃያ ስምንት ቀናት ቀጠሮ ይሰጥባቸውናበመጨረሻ መደበኛ ክስ ሲከፈትባቸው አንቀፁ ከፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ውጭ ሊሆን ይችላል - ለምሳሌ ስለላን ወይም የርስ በርስ ጦርነትንየሚመለከቱ የወንጀል ሕጉ አንቀፆች፡፡
  •     በዝርዝሩ ውስጥ ከተካተቱት ሰዎች መካከል የተፈረደባቸው፣ክሳቸውን ገና እየተከታተሉ ያሉ፣ በነፃ የተለቀቁ እና ክሳቸው የተቋረጠላቸው ግለሰቦች ይገኙበታል፡፡

ፍርድ ቤቱ አቶ ማሙሸት አማረ በነፃ እንዲቀለቀቅ ወሰነ



የአራዳ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ነሃሴ 22/2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም መንግስት ከጠራው ሰልፍ አንድ ቀን ቀድሞ ከለቅሶ ቤት ወደ ቤተ መንግስት የተደረገውን ሰልፍ አደራጅቶ መርቷል እንዲሁም ለዋናው (ለሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም) ሰልፍ አነሳስቷል በሚል ክስ የተመሰረተበት አቶ ማሙሸት አማረ በነፃ እንዲለቀቅ ወስኗል፡፡
አቃቤ ህግ ነሃሴ 20/2007 ዓ.ም አቶ ማሙሸት ገንዘብ ከፍሎ ወጣቶችን ሰልፍ እንዳስወጣቸው፣ ወጣቶችን እንዳደራጀ፣ በሰላማዊ ሰልፉ ወቅትም መንግስትን የሚተቹ መፈክሮችን በመሪነት ሲያሰማ እንደነበርና ለሚያዝያ 14 ሰልፍም ሲያደራጅ እንደነበር ያስረዱልኛል ያላቸውን ሶስት የሰው ምስክሮችን ማሰማቱ ይታወሳል፡፡
ይሁንና ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ምስክሮች የግል ሰራተኛ እንደሆነ በምስክርነት ቃላቸው ቢሰጡም በመስቀለኛ ጥያቄ አንደኛው የመንግስት ሰራተኛ፣ ሁለተኛው የወጣቶች ሊግ ከዚህም አለፍ ሲል የኢህአዴግ አባል፣ ሶስተኛው ደግሞ የጥቃቅንና አነስተኛ ባልደረባ መሆናቸውን በማመናቸው የሰጡት ምስክርነት ትክክል አለመሆኑን ያስረዳል ብሏል፡፡ በተጨማሪም ምስክሮቹ ገዥው ፓርቲን የሚደግፉና የወጣት ሊግ አባል ሆነው ገዥው ፓርቲን የሚቃወም ግለሰብ ላይ የሰጡት ምስክርነት ገለልተኛ ነው ብሎ ለማመን ያስቸግራል ብሏል፡፡
ከዚህም ባሻገር ምስክሮቹ የገዥው ፓርቲ ደጋፊ ሆነው እያለ አቶ ማሙሸት አማረ በተደጋጋሚ ይደውልላቸው እና ይገናኙም እንደነበር የመሰከሩ ሲሆን አቶ ማሙሸት ቀንደኛ የገዥው ፓርቲ ተቃዋሚ ሆኖ እያለ ከመንግስት (ከገዥው ፓርቲ) ቀንደኛ ደጋፊዎች እንዲህ አይነት ግንኙነት ይኖረዋል ብሎ ለማመን እንደማይቻል አስረድቷል፡፡ በሌላ በኩል ከ4 አመት ጀምሮ እስከ 7 አመት አዲስ አበባ ውስጥ የኖሩት ምስክሮች ስለ ሰልፉ ባስረዱበት ወቅት ቤተ መንግስትን ጨምሮ ሰልፉ ያለፈባቸውን ቦታዎች አናውቃቸውም ማለታቸው ራሳቸውን ከመስቀለኛ ጥያቄ ለማዳን ያደረጉት እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ገልጾአል፡፡ በመሆኑም የምስክሮቹ ቃል ታማኒነት ስለሌለው አቶ ማሙሸት አማረ መከላከል ሳያስፈልገው በዛሬው ዕለት በነፃ እንዲለቀቅ ሲል ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡
አቶ ማሙሸት አማረ ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በተካሄደው ሰልፍ ላይ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥሯል በሚል ተከሶ የነበር ቢሆንም በወቅቱ ከምርጫ ቦርድ ጋር በነበረው ክርክር ሰልፉ ላይ አለመገኘቱን የሚያጋግጥ መረጃ በማምጣቱ በነፃ እንዲለቀቅ ተወስኖ ነበር፡፡ ነገር ግን ክሱ ወደማነሳሳት ተቀይሮ እስከዛሬ እስር ቤት እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በእነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ላይ የአቃቤ ህግ ምስክር ተሰማ


የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን አቋርጠው ኤርትራ የሚገኘውን ግንቦት ሰባት የተባለ በተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ የተባለ ድርጅትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ላይ የአቃቤ ህግ ምስክር ተሰማ፡፡

ዛሬ ነሀሴ 22/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት አንደኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ ሁለተኛ ተከሳሽ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ሦስተኛ ተከሳሽ ፍቅረማርያም አስማማው እንዲሁም አራተኛ ተከሳሽ ደሴ ካህሳይ ‹‹አቃቤ ህግ በጻፈውና ለተከሳሽ በደረሰው የክስ ማመልከቻ ላይ አቃቤ ህግ የሰው ማስረጃ (ምስክር) አልጠቀሰም፤ እኛም መቃወሚያ ስናስገባም ሆነ እምነት ክህደት ቃል ስንሰጥ ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት ነው፤ በመሆኑም የአቃቤ ህግ ምስክር ሊሰማብን አይገባም›› በሚል ተቃውሞ ቢያቀርቡም አቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ ባስገባው ክስ ላይ ምስክሩን መጥቀሱን በማስረዳት ምስክሩ እንዲሰሙለት ጠይቋል፡፡

ፍርድ ቤቱ የደረሰው የክስ ማመልከቻ ላይ ምስክር እንደተመዘገበ በማረጋገጥም ብቸኛ ሆነው የቀረቡትን አንድ የአቃቤ ህግ ምስክር ሰምቷል፡፡ ምስክሩም ከ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሰሾች ጋር ሰማያዊ ፓርቲ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ሆነው እንደሚተዋወቁ፣ የካቲት 12/2007 ዓ.ም በ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሽ አማካኝነት ሰላማዊ ትግሉ እንዳላዋጣ በመጥቀስ ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ መጓዝ ማሰባቸውን ገልጸውለት በዚያው ቀን ማታ 3ኛ ተከሳሽን ጨምሮ ወደ ባህር ዳር እንደተጓዙ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡

ባህር ዳር ሲደርሱ ጠዋት ላይ ግን ምስክሩ ሀሳቡን በመቀየር ወደ አዲስ አበባ መመለስ እንደሚፈልግ እንደገለጸላቸው፣ 1ኛ ተከሳሽ በበኩሉ ‹ጎንደር ላይ የምናገኘው ሰው ስላለ ቢያንስ እሱን ካገኘኸው በኋላ መመለስ ትችላለህ› እናዳለው፣ ነገር ግን ምስክሩ በሀሳቡ ባለመስማማት ወደ አዲስ አበባ መመለሱንና ሌሎቹ ሦስቱ ግን ጉዟቸውን መቀጠላቸውን አስረድቷል፡፡ ‹‹ባህር ዳር ላይ ለምን ለመመለስ ወሰንህ›› የሚል መስቀለኛ ጥያቄ ከ1ኛ ተከሳሽ የቀረበለት ምስክሩ፣ ‹‹በወቅቱ ስሜታዊ የሚያደርጉ የግል ጉዳዮች ስለነበሩብኝ በስሜታዊነት የወሰንኩት ውሳኔ በመሆኑ ነው›› ሲል ተናግሯል፡፡

ምስክሩ ‹‹ለምስክርነት ያስገደደህ አካል የለም ወይ›› ተብሎ ሲጠየቅ ‹‹የለም›› የሚል መልስ ሰጥቷል፡፡ ‹‹ግንቦት ሰባት ነጻ አውጭ ድርጅት ነው ወይስ አሸባሪ›› ተብሎ በተከሳሾች መስቀለኛ ጥያቄ ተነስቶ፣ አቃቤ ህግ ተቃውሞውን በማሰማት ‹‹ድርጅቱ በተወካዮች ም/ቤት አሸባሪ ተብሏል፡፡ ይህ የህግ ጉዳይ ነው›› በማለት ጥያቄውን ምስክሩ የመመለስ ግዴታ እንደሌለባቸው አስረድቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም ይህን ተቃውሞ ተቀብሎ ምስክሩ ጥያቄውን እንዲያልፉት ተደርጓል፡፡ ‹‹ማዕከላዊ ታስረህ ነበር፣ ድብደባም እንደደረሰብህ በሚዲያ ሳይቀር ተዘግቧል፡፡ ልክ ነው?›› ተብሎ በመስቀለኛ ጥያቄ ሲጠየቅ ምስክሩ ‹‹ማዕከላዊ ቃል እንድሰጥ ተደርጌያለሁ፤ ግን አልታሰርኩም›› የሚል መልስ ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ የምስክሩን ቃል ከሰማ በኋላ የአቃቤ ህግን አስተያየት የጠየቀ ሲሆን፣ አቃቤ ህግ የምስክሩ ቃልና የሰነድ ማስረጃውን መርምሮ ፍርድ ቤቱ ብይን እንዲሰጥለት ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ብይኑን ለማሰማት ለመስከረም 5/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡