Saturday, July 27, 2013

በሙስና የተጠረጠሩ ዋና ሃላፊዎች እየተፈለጉ ነው


በሙስና የተጠረጠሩ ዋና ሃላፊዎች እየተፈለጉ ነው


በማሽኖች ግዢና ኪራይ ከፍተኛ ሙስና ፈጽመዋል ተብለው ከሚፈለጉ 25 የኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ባለስልጣናት መካከል 13ቱ የተያዙ ሲሆን፤ የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅና ምክትላቸውን ጨምሮ ዋና ዋና ሃላፊዎች እስካሁን አልተያዙም፡፡ ዘንድሮ አንድ ሺህ የሚጠጉ ጥቆማዎች እንደቀረቡ የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን የኮሙኒኬሽንና የትምህርት ክፍል ሃላፊ አቶ ጠይብ አባፎጊ፤ ጥቅሞች መነሻነት ከ250 በላይ የምርመራ መዝገቦች ተከፍተዋል፤ የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ሃላፊዎች ላይ የተከፈተው የምርመራ መዝገቡም ከእነዚህ አንዱ ነው ብለዋል፡፡
የድርጅቱ ቦርድ ዋና ፀሐፊ፣ ዋና ስራአስኪያጅና ምክትላቸው፣ እንዲሁም የፋይናንስና የማሽነሪ ግዢ ሃላፊዎች በፖሊስ እየተፈለጉ ሲሆን፤ መጀመሪያ ላይ የተያዙትን ጨምሮ እስካሁን 13 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተገልጿል፡፡ ተጨማሪ ተጠርጣሪዎች ይኖሩ እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ጠይብ፣ ጉዳዩ ከእቃ ግዢና ኪራይ ጋር በተያያዘ ስለሆነ አንዳንድ ባለሀብቶችንም ሊመለከት ይችላል ካሉ በኋላ፣ እስካሁን ግን እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ የኦሮሚያ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዘንድሮ ከከፈታቸው 250 መዝገቦች መካከል፣ 150 ያክሉ ላይ ውሳኔ እንደተሰጠባቸው አቶ ጠይብ ጠቅሰው፣ ተከሳሾች ከ4 ወር እስከ 18 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣቶችና ተጨማሪ የገንዘብ መቀጮ ተፈርዶባቸዋል ብለዋል፡፡ ኮሚሽኑ በፍ/ቤት ውሳኔ አማካኝነት ከለአራት አመታት ባደረገው ግምገማና በደረሰው ጥቆማበኦሮሚያ ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ወደ መንግስት ካዝና እንዲገባ መደረጉን የገለፁት አቶ ጠይብ በሌሎች የክልሉ መስሪያ ቤቶች ላይ ምርመራው እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

No comments: