አምባገነኖች ጫንቃችን ላይ ፊጥ ብለው መሰረታዊ መብቶቻችንን እየነጠቁ እንዲኖሩ አንፈቅድም!!!
በደርግ ድክመት
ወደ በትረ ስልጣን የወጣው
ኢህአዴግ መራሹ መንግስትም ላለፉት
21 ዓመታት ራሱን ከደርግ ጋር እያነፃፀረ ‹‹የተሻልኩ
ነኝ››
ከማለት
ውጭ መሰረታዊ መብቶችን በመንፈግ
ከደርጉ
የሚለይበትን
ነጥብ ፈልገን ለማግኘት ይቸግረናል፡፡
ላለፉት
21 ዓመታት ያልተመለሱ ጥያቄዎች እንዲመለሱ
አላደረገም፡፡
ዋና ዋና መሰረታዊ መብቶችን
በህገ-መንግስት ላይና በሌሎች ህጎች
ብቻ በማካተት ለውጥ
ማምጣት
ሳይችል
ቀጥሏል፡፡
የኢህአዴግ ሊቀመንበርና
የፌደራላዊ
ስርዓቱ
ርዕሰ መስተዳድር የሆኑት
አቶ መለስ ዜናዊም በዚሁ
ቅኝት ዘልቀው ለማናችንም
የማይቀረውን
ሞት በድንገት ሞተዋል፡፡
እጅግ በጣም
በሚያሳቅቅና
በሚያሳዝን
ሁኔታ ስርዓቱ ለባለፉት 21 ዓመታት የኢትጵያ ህዝብ ሲጠይቅ የነበረውን መሰረታዊ መብቶች ጥያቄ ለመፍታት ያቀደ
አይመስልም፡፡ እንደውም ብሶበታል፡፡ በአቶ መለስ የአገዛዝ
ዘመን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ
መብትና
ነፃው ፕሬስ ጥርስ የተነከሰበት ቢሆንም ከእሳቸው ህልፈት በኋላ ተባብሶ በመቀጠል በሃገሪቱ ላይ ያሉ ነፃ-ፕሬሶች ተጠርቅመው ተዘግተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ
መሰረታዊ
የነፃነት
ጥያቄዎች አልተመለሱም፤ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት አልተመሰረተም ብሎ አምባገነኖች በስልጣን
መተካካት ሰበብ
ጫንቃችን
ላይ ፊጥ ብለው መሰረታዊ መብቶቻችንን እየነጠቁ እንዲኖሩ የምንፈቅድበት አቅም የለንም፡፡
ዘመኑም
አይፈቅድም፡፡
ስለዚህ ለመሰረታዊ
የሰው ልጅ መብቶችና ሃሳብን
በነፃነት የመግለፅ መብት የምናደርገው ትግል
አጠናክሮ
በመቀጠል ለባለፉት 21 ዓመታት
ያልተመለሱት
ጥያቄዎች
በተግባር
እስከሚረጋገጡ
ድረስና
ዴሚክራሲያዊት
ኢትዮጵያ
እስከምትፈጠር
ድረስ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ አምባገነኖች ልሳናችንን እንዲዘጉ አንፈቅድም፡፡ የመናገር መብታችን
በመዝጋትም
ትግላችንን
መጠምዘዝ
አይችሉም፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
No comments:
Post a Comment