Sunday, July 7, 2013

አቶ ሰውነት ... በ ሼህ አላሙዲ ተዘጋጅቶ የነበራው የአሜሪካ ስፕርት ዝግጅት ላይ በእንግድነት እንዲገኙ ተጠየቁ

አቶ ሰውነት ... በ ሼህ አላሙዲ ተዘጋጅቶ የነበራው የአሜሪካ ስፕርት ዝግጅት ላይ በእንግድነት እንዲገኙ ተጠይቀው.........................

...ሁኔታዎች ከተመቻቹልኝ እዛው አገር መጥቼ ውድድሩን ለማየት እጅግ ፍላጎቱ አለኝ .....እንዳተባለውም ብቃት ያላቸው ልጆችና ወጣቶች ከተገኙ መልምዬ ወደ ኢትዮጵያ አምጥቼ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር እንዳምቀላቅላቸው ቃል እገባለሁ ..... ብለው ነበር ....ከዛ ግን በቦታው አልተገኙም ታዲያ ባለመገኘታቸው ተጠያቂ ያደርጋቸው ይሆን ? እንደምታዩት አጠገባቸው ያለው ጡንቻው እንደ ታይሰን ፈርጠም ያለው ሰውዬ በጣም ያሰፋራል :: ግለሰቡም አሜሪካ ያሉትን የሼክ አላሙዲን ተጨዋቾች እደሜያቸው ከ 17 እስከ 25 የሚሆኑ እና በየት/ቤታቸው የሚጫወቱና ለብሄራዊ ቡድን ለመጫወት እንደሚችሉ ለአቶ ሰውነት ቀደም ብለው አብራርተው ነበር ለዛም ነው አቶ ሰውነት" እንደተባለው " ሲሉ የጀመሩት :-)

በነገራችን ላይ እድሜያቸው በዶላር ነው እንዴ የተቆጠረው ? እንዳየናቸው ከሆነ ወደ እኛ ብር የተቀየሩ ይመሰላሉ :: ሰደት እኮ መከራ ነው ወደኋላ ነው ያሚያስቆጥረው ::

በዝግጅቱ ላይ የጥንቱ አቶ ምሩፅ ይፍጠር እና የብሔራዊ ኳዋስ ተጫዋች ወጣት አዳነ ግርማ ተገኝተው እንደነበራ አረጋግጠናል ::

በመጨረሻም ኣቶ ሰውነት ..... በዚህ አጋጣሚ ለርሶ ትልቅ ክብር እንዳልኝ ለመግለፅ እወዳለሁ :: ሳልጠቅስ ማለፍ የማልፈልገው ..... በዚህ በአሜሪካ የተዘጋጀው አንጋፋው የኢትዮጵያን ስፕርት ፌደሬሽን 30 አመቱን በቁጥር ይህ ነው በማይባሉ ውድ የኢትይጵያን ልጆች በደማቅ ሁኔታ ተክብሮ አልፏል :: ይህ ከላይ የጠቀሰኩት ከዚህ ከአንጋፋው አፈንግጦ የወጣና በሼህ አላሙዲ የሚረዳው ነው ከተወለደ ግና ሁለት አመቱ ነው ::


ምንግዜም ኢትዮጵያዊነት ያሸንፈል !!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!


No comments: