Sunday, July 7, 2013

መሪ የማይወጣለት ተመሪ

  መሪ የማይወጣለት ተመሪ


     በአገራችን የሺህ ዓመታት ታሪክ ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ቅንና መልካም መሪን ለማግኘት አልታደለም፡፡ አንዱ ህዝቡን በባርነት ሲገዛ ሌላው ደም ሲያፋስስ፣ አንዱ የአገርን የግዛት ወሰን በሀይል ሲያሰፋ ሌላኛው እየቆራረሰ ሲያጠብ ዘመናት አለፉ፡፡ ከዝክረ ታሪክ እየጨለፍን ዛሬ ላይ የምናወድሳቸው የዘመነ መሳፍንት ነገስታትም ቢሆኑ ለሚመሩት ህዝብ ቅንና ምቹ ስለነበሩ አይደለም፤ ከዛሬዎቹ 21ኛው /ዘመን መሪዎች ማንነትና በተለይም ከአገር አንድነትና ሉዓላዊነት አንፃር እያነፃፀርን ስንፈትሻቸው የተሻሉ መስለው ስለሚታዩን እንጂ፡፡ ይሄ ደግሞ ትልቅ የታሪክ ዝቅጠት ነው፡፡ ከትናንቱ የዛሬው መሻል ሲኖርበት የኋላውን በቁጭት መመኘትና ማወደስ የትውልዱን እርቃንነት የሚያጋልጥ ነው፡፡
    የኢትዮጵያ ህዝብ ከየትኛውም ዓለም ህዝብ ይልቅ ለምሪት የሚመች ነው፡፡ ያለ መሪ ለዓመታትና ለወራት የዘለቁ ጊዜያትና ተፈቃቅሮና ተከባብሮ አሳልፏል፡፡ ለዚህም የምኒልክ የህመምና የሞት ምስጢር፣ ኃይለ ሥላሴ ከስልጣን ሲወገዱ የነበረው ክፍተት፣ ኢህአዴግ መላ አገሪቱን እስኪቆጣጠር የህዝቡ ጨዋነት፣ አሁን እንኳን አቶ መለስ ሞታቸው እስከተነገረበት ቀን ድረስ ለሁለት ወራት ስልጣናቸው ክፍት ሆኖ ሳለ ህዝቡ በራሱ ጊዜ በሰላም ወጥቶ ይገባ ነበር፡፡
ከአንድናት ኢትዮጵያ ብሎግ

ኢትዮጵያ ክብር ለዘላለም ትኑር!

No comments: