“ከማያውቁት መላዕክ የሚያውቁት ሰይጣን”
በቅርቡ ጠ/ሚኒስትሩ ከነጋዴዎች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ስለስደተኞች ጉዳይ ሲናገሩ፣ ቀደም ሲል የአረብ አገራትን የቤት ሰራተኞች ፍላጎት የሚሞሉት እንደ እነፊሊፒንስ ያሉ አገራት እንደነበሩ ጠቅሰው፣ አሁን ግን እነሱ ስላደጉና ዜጎቻቸውን በየአገራቸው ለመቅጠር ስለቻሉ ተረኞቹ የእኛ አገር ዜጎች ሆነዋል” በማለት ካስረዱ በኋላ “መፍትሄው እንደ እነ ፊሊፒንስ ማደግ ብቻ ነው”
ብለዋል (ይሄ ነው ከፕሮፓጋንዳ የፀዳ መልስ ማለት!) እስከዛ ግን የኢቴቪ ጋዜጠኛዋ እንዳደረገችው ቢያንስ በህገወጥ ደላሎች አማካኝነት የሚደረገውን ጉዞ ለመግታት ብዙ ውይይቶች፣ ብዙ ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች በማድረግ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት መቀነስ ይቻላል፡፡ ይሄኔ ፕሮፓጋንዳ ከእነአካቴው
አያስፈልግም፡፡ መርሳት የሌለብን ምን መሰላችሁ በአገሩ የሥራና የእድገት እድል እያለ ደቡብ አፍሪካም ሆነ አረብ አገር ለመጓዝ የሚመርጥ ማንም የለም (“ከማያውቁት መላዕክ የሚያውቁት ሰይጣን” ይባል የለ!)
በነገራችሁ ላይ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችም እኮ እየተሰደዱ ነው፡፡ እነሱ ግን በህገወጥ ደላላ ተታለው
አይደለም፡፡ የስደት ምክንያታቸውም እንደሌሎች ዜጎች ኢኮኖሚያዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ ነው፡፡ እኔ ግን
በተቃዋሚዎች ስደት የአንዳንድ ኢህአዴግ arm twister ወይም “እጅ ጠምዛዥ” የሚላቸውን ማለቴ ነው) እጅ አለበት፡፡ ተቃዋሚዎች ግን ለአመራሮችም ሆነ ለአባላቶቻቸው ስደት ተጠያቂው ማነው ሲባሉ ጣታቸውን የሚሰነዝሩት ኢህአዴግ ላይ ነው፡፡ እንዴት ሲባሉም ገዢው ፓርቲ እያደረሰብን ነው የሚሉትን በደል ዘርዝረው ያስረዳሉ፡፡ ከተለመዱት እስርና ወከባ በተጨማሪ የመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብታችንን ተነፍገናል የሚሉት ተቃዋሚዎች፤ በአገራቸው ጉዳይ ባይተዋር መደረጋቸውንም ይናገራሉ (“በህዳሴው ግድብ ዙሪያ አላማከረንም” የሚል ቅሬታቸውን ልብ ይሏል) “ኢህአዴግ ከህዝብ ጋር ከተገናኘን አሲረን ሥልጣን የምንቀማው ስለሚመስለው መፈናፈኛ አሳጥቶናል” የሚሉት ተቃዋሚዎች፤ ለዚህ ነው አመራሮችም ሆኑ አባላት የሚሰደዱት ባይ ናቸው፡፡ “ዲሞክራሲ ለኢህአዴግ የምርጫ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው”
የሚለው ኢህአዴግ ግን የተቃዋሚዎች ስደት ዲሞክራሲው ያመጣው ነው ይላል፡፡ (እድገቱ ያመጣው ነው እንደሚለው መሆኑ ነው!)እኔ ግን የስደት ነገር በጣም የሚያሳስበኝ መቼ መሰላችሁ? ቱባ ቱባ የኢህአዴግ ባለስልጣናት መሰደድ የጀመሩ ዕለት ነው (ምን አጥተው
እንዳትሉኝ ብቻ!) ለነገሩማ የተቃዋሚዎችን ያህል አይሆኑም እንጂ ስንቶቹ ለኮንፍረንስና ለህክምና እያሉ ተሰደው የለ፡፡ (የኢህአዴግ አባላትም ሲሰደዱ ተቃዋሚ ይሆናሉ አይደል?) ወዳጆቼ መሪዎች ስደት ከጀመሩ እኮ ሃይለኛ ቀውስ ነው የሚፈጠረው፡፡ (ተሰደው ካላየን አናምን እንዳትሉኝ!)
ከአንድናት ኢትዮጵያ ብሎግ
ኢትዮጵያ
በክብር ለዘላለም ትኑር!
No comments:
Post a Comment