Wednesday, July 3, 2013

በጎንደር ህገ ወጡ እስር ቀጥሏል

በጎንደር ህገ ወጡ እስር ቀጥሏል 
-ወገራ ወረዳ ላይ የግድያ ሙከራ ተደርጓል 

/ሰኔ 26,2005.

-----------------------------------------------------------------------
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት››በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ንቅናቄ ይፋ ማድረጉና የንቅናቄው የመጀመሪያ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ሰኔ 30 ቀን 2005 . ለማድረግ በህገ መንግስቱ መሰረት ለሚመለከተው አካል የማሳወቂያ ደብዳቤ በማስገባት የቅስቀሳ ስራውን በጎንደርና አካባቢው መስራት ቢጀምርም መንግስት ህገወጥ እስር እያካሄደ ይገኛል፡፡

ለቅስቀሳ ስራ ወደ ምዕራብ አርማጭሆ ተንቀሳቅሰው የነበሩ አራት የፓርቲው አባላት ህገ ወጥ ወረቀት በትናችኋል ተብለው ባሳለፍነው ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2005 . በቁጥጥር ስር ውለው ማክሰኞ ሰኔ 24 ቀን 2005 . ፍርድ ቤት ቀርበው የአራት ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡

እስሩ ህገ መንግስታዊ መብትን ለመጠቀም በተወሰደ እንቅስቃሴ በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የተደረገ አፈና መሆኑን በመግለጽ አንድነት ታሳሪዎቹ እንዲለቀቁና ይህንን ባደረጉ የጸጥታ ሃላፊዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ የዞኑን አመራሮች ቢጠይቅም በአፈናው በመቀጠል ዛሬ ረፋድ ላይ በጎንደር ከተማ ቅስቀሳ ላይ የነበረ አንድ አባላችንን አስረውታል፡፡ 

በተያያዘ ዜና በትላንትናው እለት በጎንደር ከተማ ለሰላማዊ ሰልፉ የተዘጋጀውን በራሪ ወረቀት ሲያሰራጩ የነበሩት አቶ አምደ ማርያም እዝራ እና አቶ ስማቸው ግንቤ በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡ በዛሬው እለት አቶ ማሩ አሻግር የተባሉ የዞኑ የአንድነት አመራር ትላንት የታሰሩ አባላትን ለመጠየቅ ወደ 3 ፖሊስ ጣቢያ በሚሄድበት ወቅት እሱንም በህገ ወጥ መንገድ ማሰራቸውን ታውቋል፡፡ በተጨማሪም በላይ አርማጨሆ ትክል ድንጋይ ከተማ አቶ እርሻው አደራጀው የተባለ የአንድነት አባል የሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳውን የሚመለከት በራሪ ወረቀት በማሰራጨቱ በታሰሩንና በሰሜ ጎንደር ወገራ ወረዳ ተመሳሳይ በራሪ ወረቀት ሲበትኑ ከነበሩ አባላት መካከል አቶ ጄጃው ቡላዴ የተባሉ የአንድነት አባል በህገወጥ መንገድ ሲታሰሩ አቶ ጋሻው ዘውዱ የተባሉ አባል ላይ በጥይት የግድያ ሙከራ ተደገርጎባቸው ማምለጣቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት አስታውቀዋል፡፡
የአንድነት ፓርቲ የህዝባዊ ንቅናቄ ግብረሀይል በፓርቲው አባላት ላይ እየተወሰደ ያለውን ህገወጥ እስርና የግያ ሙከራ አውግዞ፤የትኛውም የመንግስት ህገወጥ እርምጃ ከንቅናቄው እንደማይገታው ለፍኖተ ነፃነት አስታውቋል፡፡ 

No comments: