Tuesday, July 2, 2013

ዶ/ር ብርሃኑ ከኢሳት ጋር በማገናኘት፣ኢሳትና ያገር ቤት ህዝብ ሊቆራረጡ ነው? የኢህአዴግ አዲሱ አዋጅ!!!

ዶ/ር ብርሃኑ ከኢሳት ጋር በማገናኘት፣ኢሳትና ያገር ቤት ህዝብ ሊቆራረጡ ነው? የኢህአዴግ አዲሱ አዋጅ!!!

ዶ/ር ብርሃኑ ከኢሳት ጋር በማገናኘት፣ኢሳትና ያገር ቤት ህዝብ ሊቆራረጡ ነው? የኢህአዴግ አዲሱ አዋጅ!!!
ከኢሳት ጋር ማናቸውም ግንኙነት ያደረገ መረጃ የሰጠ ቃለ መጠይቅ ያደረገ እና ሌሎችንም ለመክሰስ ወያኔ  ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው
በኢትዮጵያ ምድር እንደ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የኢህአዴግን ስነልቦና የተረዳ ሰው የለም ብል ማጋነን አይሆንብኝም፡፡ ከቀድሞ መለስ ዜናዊ ጋር እኩል በእኩል ሊወዳደር፣ እንደውም አንዳንዴ የሚበልጥብኝ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ስለ ዶ/ር ብርሃኑ ሳስብ ብቅ የሚልብኝ እኔ የምታገለው ለልጆቼ ነው፣ልጆቼ በነጻነት የሚኖሩባትን ሀገር ለመፍጠር ነው ያላት ነገር ዛሬ በብዙ አባቶቻችን ልብ ውስጥ አለች፡፡
በርግጥ ዛሬ ዶ/ር ብርሃኑን ለማሞገስ አይደለም ለመጻፍ የተገደድኩት፡፡ ምንም እንኵ ማሞገስ ቢገባውም፡፡ ዋናው ዛሬ ለመጻፍ የተገደድኩበት ምክንያት በኢህአዴግ እጅ በገባ ማስረጃ የዶ/ር ብርሃኑ የተጠለፈ ንግግር ምክንያት ገዢው መንግስት አዲስ አዋጅ አዘጋጅቶ ኢሳት ላይ ቃለ መጠይቅ የሚያደርጉትን ያገር ቤት ፖለቲከኞችና እንግዶችን እንዲሁም በኢሳት ላይ ከዚህ በኋላ የሚናገሩትን በሙሉ ከሽብርተኛው ቡድን ጋር ግንኙነት አላችሁ በማለት ኢሳትን ካገር ቤት ህዝብ ጋር ለማቆራረጥ አስፈላጊውን ማስረጃ እያሰባሰበ መሆናቸውን ስመለከት ካልጻፍኩ ይቆጨኛል ብዬ ነው፡፡
በኢትዮዽያ በጉጉት የሚታየውና እየተደመጠ ያለው ኢሳት ለወያኔ ስጋት ከመሆኑ የተነሳ በተደጋጋሚ ጃም ቢደረግም ፈተናውን አልፎ በሚያጋልጣቸው የወያኔ መሰሪ አካሄድ የተነሳ ከህዝቡ ከፍተኛ ድጋፍ ማግኘቱ ስጋት የሆነበት የወያኔ መንግስት ኢሳትን ከህዝቡ ጋር ለማራራቅ ኢሳት አሸባሪ ከተባለው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር በማዛመድ በፀረ ሽብር ህግ ለማስቀጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየሰሩ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያሳያል፡፡
መንግስት ኢሳትን የግንቦት 7 ንብረት ነው በማለት በርካታ ማስረጃዎችን አሰባስቦ እያጠናቀቀ ይገኛል፡፡ በነገራችን ላይ ባለፈው በአውራምባ ታይምስ የተለቀቀው የድምጽ መረጃ እስከ ክፍል አራት ድረስ ቀስ እየተባለ በመልቀቅ በተለያዩ ወገኖች የሚሰጡትን አስተያየቶችን በመሰብሰብ ለአዋጁ ዝግጅት ለመጠቀም ታስቧል፡፡ ይህንንምና ሌሎችን ማስረጃ በመያዝ ኢሳት የሽብርተኛ ሚዲያ ነው በማለት ከኢሳት ጋር ማናቸውም ግንኙነት ያደረገ/መረጃ የሰጠ/ቃለ መጠይቅ ያደረገ እና ሌሎችንም በማካተት እስከ 2007 ዓ.ም ምርጫ ድረስ ሚዲያውን ከህዝብ ለመነጠል እየተዶለተ ይገኛል፡፡ ስለዚህም ኢሳትና ማኔጅመንቱ አስፈላጊውን ዝግጅትና ሌሎች እርምጃዎችን እንዲወሰዱ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ በመቀጠልም ዶ/ር ብርሃኑ ገንዘቡን የተቀበለው ከኤርትራ ነው በማለት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ኤርትራ በአለም አቀፍ መንግስት ማዕቅብና ሌሎች መገለሎች የደረሰባት በመሆኑ የዶ/ር ብርሃኑን እንቅስቃሴ ለመግታት ያተቀደ ተግባር ነው፡፡
ኢሳትን እንወደዋለንና!!!!!!

No comments: