Friday, July 5, 2013

የአፍሪካ መንግስታት ፈሪዎች ናቸው



የአፍሪካ መንግስታት ፈሪዎች ናቸው። አንድ ሃገር ዉስጥ ዓምባ ገነን መንግስት በተባበረ የህዝብ ድምጽ ተደመሰሰ ሲባል ፈጥነዉ የዚያችን ሃገር ጀግና ህዝብ ያወግዛሉ። ከዚያም አዲስ አበባ ላይ ይሰበሰቡና ያችን ሃገር ከአባልነት ያግዳሉ ምክንያት አፍሪካ ዉስጥ ካሉ ሃገራት መካከል በጣት ከሚቆጠሩት ዉጭ ሁሉም ፈላጭ ቆራጭ ናቸዉና
የአፍሪካ ህብረት ተብየዉ ሰሞኑን ተሰባስቦ ሞርሲ ከሄዱ ግብጽ አባላችን አትሆንም ሊሉ ነው አሉ። የአፍሪካ ህብረት የተባበሩት አምባ ገነኖች ህብረት። 
አሁን ነገሩ ግልጽ እየሆነ ነው፡ አንድ ሃገር ዓባል የሚሆነዉ ፈላጭ ቆራጭ የሆነ መንግስትን በኣመጽ እስካልጣለ ድረስ ነው ማለት ነው። ፈላጭ ቆራጭ መንግስትን በተባበረ ድምጽ አዉርዶ ሲያንኮታኩት ግን ሃጢያት እንደሰራ ይታያል። 
መቸ ነው ለአፍሪካዉያን ጥቅምና ነጻነት የሚሰራ መሪ አፍሪካ ላይ የሚወለደው?

No comments: