Wednesday, July 3, 2013

አዋጅን ሽፋን አድርጎ በአደባባይ ሰውን መግደል የሚፈቅደው አዋጅ ጸደቀ::


በአደባባይ ሰውን መግደል በይፋ ተፈቀደ:: 
አዋጅን ሽፋን አድርጎ በአደባባይ ሰውን መግደል የሚፈቅደው አዋጅ ጸደቀ::
የደኅንነት ሠራተኞች ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ለሚወስዱት ዕርም በሕግ አይጠየቁም!!!
በሃገር ደህንነት ሽፋን ከፍተኛ የሆኑ ሙስናዎች ይፈጸማሉ::
በምስጢር ጥበቃ ስም ሙስናዎች ቢፈጸሙም የፌዴራሉ ኦዲተር መስሪያቤት የደህንነትን የሂሳብ መዝገቦች የመመርመር ስልጣኑ ባዳ ሆኗል:;

በእስራኤል አገር በታል አራድ ኔጊቭ ማሰልጠኛ ጣቢያ ያሰለጠናቸው 987 የደህንነት ሰራተኞች ወደ አገር ቤት መግባታቸውን እና ሌሎች አዳዲስ የደህንነት ሰራተኞችም በስልጠና ላይ መሆናቸውን ተከትሎ የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት /ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ከአንድ ሳምንት ዕይታ በኋላ ለፓርላማው ቀርቦ እምብዛም ውይይት ሳይደረግበት መጽደቁ ታውቋል፡፡
አንድ የደህንነት ሰራተኛ አስቸጋሪ ሁኔታ ካልገጠመው በስተቀር የሚለውን ጠቅሰውአስቸጋሪ ሁኔታየሚለው ሀረግ እና ሌሎች ለትርጉም አሻሚ የሆኑ አሻሚ ድንጋጌዎች ተካተውበታል ሲሉ የምክርቤቱ የተቃዋሚ ተወካይ ተቃውመውታል::በአዋጁ ውስጥ ብሄራዊ የደህንነት መስሪያ ቤት ተቃዋሚዎችን እንዳይሰልል፣ ወይም በተቃዋሚዎች ላይ እንግልት እንዳይፈጽም የሚያስገድድ ድንጋጌ አልተካተተበትም::
በአዲስ መልክ ለሙስናው በር አመቻችተዋል ማንኛውንም የመረጃና ደህንነት ማቴሪያሎች ከጉምሩክ እይታ ውጪ ማስገባት ይቻላል:: ወደ ዉጪም እንዲሁ መላክ ይቻላል ::በሃገር ደህንነት ሽፋን ከፍተኛ የሆኑ ሙስናዎች ይፈጸማሉ:: እንዲሁም በደህንነት መስሪያ ቤቱ ስም እና በውስጡ የሚፈጸሙ ዘረፋዎችን በተመለከተ የፌዴራሉ ኦዲተር ሊመረመር የማይችልበት ምስጢር ነው በማለት የሚደፍኑበት አዋጅ ነው::የሒሳብ መዛግብትና ሌሎች የሥራ መረጃዎችን እጅግ ብርቱ ሚስጥር ብሎ በመሰየም ለሌሎች አካላት (የፈዴራል ኦዲተርንም ቢሆን) ሊከለክል እንደሚችል አውጁ ላይ ተካቷል፡፡ እንዲሁም ክልሎች በዚህ በዚህ መስሪያ ቤት ውስጥ መሳተፍ እንደማይችሉ እና ይህን መስለ ተቋምም እንዳይመሰርቱ ያዛል:

No comments: