Tuesday, June 18, 2013

የጠፋዉ ወረቀት…..Fifa vs E.F.F.

                   
                       የጠፋዉ ወረቀት…..Fifa vs E.F.F.
ይህ አመት በስፖርቱ ለምክትሎች አልሆነም..የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት በሙስና ሽቤ ገቡ..የእግር ኩዋሱ ብሂራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ ከዋልያዎቹ ተለዩ..አሁን ደሞ የእግር ኩዋሱ ምክትል ችግር ዉስጥ ገብተዋልብርሀኑ ከበደን ለማወቅ ደቂቃዎች ብቻ ይበቃሉ..ትሁት ነገሮችን ለማስረዳት ብዙ የሚጥር አይነት ሰዉ ነዉ፤የሚሰራዉ ከዉጭ ሀገር ዜጎች ጋር ነዉ፤ብዙ ጊዜም ስራ ይበዛበታል..ለዚህም ነዉ በብዙ ጊዜ አንዳንዴ ብቻ ስልኩ የሚከፈተዉ..የማወራችሁ ስለ እግር ኩዋስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት እናም የዋልያ ቡድን መሪ..የዛሬ ቀን ሁነኛ ተወቃሽ ነዉ
እኔ እንኩዋን ፈርመህ ወረቀት ወስደሀል ተብዮ አይደለም..ሁለት ሰዎች ወስደሀል ካሉኝ እንኩዋን እቀበላለሁ፤የምንያህልን መቀጣት የሚገልጻዉ የፊፋ ኮሚኒኬ ከብዙ ወረቀቶች ጋር የት እንደገባ አላስታዉስምመቀጣቱንም አላየሁም..እመኑኝግን አጥፍቺያለሁ
ለብርሀኑ ከበደ ወረቀቱ ከአቶ አሽናፊ የጠሰጣቸዉ ከቦትሰዋናዉ ጨዋታ 74ቀናት በፊት ነዉ፤ምንያህል መሰለፍ የለበትም የጠባለዉ ከተቀጣበት ጨዋታ 74ቀናት በፊት ነበር..እናም ወረቀቱ ጠፋ..ብርሀኑም ረሳ..አሽናፊም ስራዮ ወረቀቱን ለቡድን መሪና አሰልጣኝ መስጠት እንጂ የተቀጣዉን ማየት አይደለም አለ..እናም ኢትዮጲያ ፊፋ ከመሰረተባት ክስ እንደማታመልጥ አረጋገጠች…3 ነጥብ ለቦትስዋን ሆኑዋልአስቂኙ ነገር በደረጃ የተቀመጡት የተጠያቂዎች ጉዳይ ነዉ፤ እንደ ሙስናዉ ዜና አልያም እንደ 81 ጄኔራሎች ስም አንብቡት!!
1
ብርሀኑ ከበደ --ቡድን መሪ
2
--ሰዉነት ቢሻዉ
3
-ስዩም ከበደ
አፈወርቅ አየለ--የቀድሞዉ ቡድን መሪ
4
ተኛ- ምንያህል ተሾመ
5
ተኛ-ጥፋተኝነቱን በግድ በጉልበት ፕሬዝዳንቱ ያሽከሙት የፅህፈት ቤት ሀላፊ አሽናፊ እጅጉ!!
ፊፋ እስከ አርብ ድረስ መከራከሪያ አቅርቡ ብሎ ደብዳቤዉን የላከዉ ከደቡብ አፍሪካ ጨዋታ 4ቀናት በፊት እሮብ ነበር፤4 የኢመርጀንሲ ኮሚቴ ሰዎች ተሰበሰብንና በሚስጥር እንያዘዉ ተባባልን አሉ፤እናም የደቡብ አፍሪካን ጨዋታ ኢትዮጲያ ብታሽንፍም እንደማታልፍ ያቁ ነበርበመግለጫዉ መሀል ብርሀኑ ከበደ ይህን ነገር ትላንት ስሰማ በጣም ነዉ የደነገጥኩት አለ..ነገሩ ትንሽ ያምታታል..እሱ የኢመርጀንሲ ኮሚቴ አባል ነዉ ግን ትላንት ነዉ የሰማሁት አለ… አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ በርግጥም ተደናግጥዋል--ጥፋቱ የቡድን እንጂ የግል አይደለም..አለ...ለአፍሪካ ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ የሄደዉ ቡድን ከቡድን መሪነት እና ተያያዠ ነገሮች ጋር በጣም ብዙ ክፍተት ነበረበት፤በዘልማድ መሰራቱ..ከቡድኑ ይለቅ ለግለ መታሰቡ አግባብ አደለም..ለንደን ኦሎምፒክ ላይ ክትፎ ቤቶችን እነዳጣበቡት ቡድን መሪ ማለቴ ነዉ!!
ኢትዮጲያ አሁን 10 ነጥብ ደቡብ አፍሪካ 8 ቦትስዋና 7 ነጥብ ይዘዉ ..መስከረም 6የሚደረገዉን የሞት ሞት ጨዋታ ያደርጋሉ፤ከማንም በላይ ለብርሀኑ ከበደና ለምንያህል ወሳኝ ጨዋታዎች ናቸዉበጣም የሚገርመዉ ግን የብሂራዊ ቡድኑ ደካማ የደቡብ አፍሪካ ጨዋታ አቁዋም በግርግር መታለፉ ነዉ..ስሜት እንጂ እዉቀት ያልታየበት ቡድን 3 ነጥብ በላይ ስለ ድክመቱ ማዉራቱ ይጠቅመዋልና!!ለጊዜዉ ግን የጠፋዉ ወረቀት አስረስቶታል!!!



No comments: