Friday, June 7, 2013

ኢራን የኢትዮጵያ ግድብ ግብጽን ይጎዳታል ስትል አሳወቀች

ኢራን የኢትዮጵያ ግድብ ግብጽን ይጎዳታል ስትል አሳወቀች

የኅዳሴ ግድብ ንድፍ
ኢራን ዛሬ በነጋታው በለቀቀችው የኢራን መንግስት የዜና አውታር በሆነው Press Tv ኢትዮጵያ የምትገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግብጽን የሚጎዳ ነው ብላለች።
ዜናውን ስታሰራጭ የትንተና ባለሞያው ተናገሩ ብላ ነው የዘገበችው። ሆኖም ይህ ዘገባ የግብጽ ሱዳን እና የኢትዮጵያ ሁለት ሁለት እና ዓለም ዓቀፍ አራት ባለሞያዎች የተሳተፉበት አጥኚ ቡድን ግድቡ ጉዳት እንደሌለው እና ጥቅሙ አመዛኝ መሆኑን በይፋ ለሶስቱም ሃገራት መንግስታት መግለጫ ልከው አቋማቸውን ማሳወቃቸው እየታወቀ እና ግድቡን በተመለከተ ግብጽን ጨምሮ ወካይ የላኩ ሃገራት የተማመኑባቸውን ባለሞያዎች በማጣጣል ተንታኝ ብላ ያለችውን ግለሰብ የግል ቁንጽል አስተሳሰብ አሰራጭታለች።
የዘገባው አቅራቢ መረጃ ላይ ተንተርሶ መናገር ሲገባው ለግብጽ የሚሞግት ዘመን ያለፈበት እና ያረጀ አስተሳሰቦችን ሲለፍፍ ተደምጧል።
ኢራን በኒውክሌር ግንባታ ፍላጎቷ ዓለም ዓቀፍ ተቃውሞ የገጠማት ሃገር እንደመሆኗ ከማንም በላይ ባለድርሻ አካላት ላልወደዱት ነገር የአንድን ሃገር ፍላጎት ሊጫኑት እንደሚችሉ ከማንም በላይ ተገነዘባለች። ሆኖም ይህን እያስተዋለች ይህንን ዘገባ በብሄራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ ማሰራጨቷ የሚያስገምታት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያዝንባት ምክንያት የሆነ ነው።
ኢትዮጵያ ግድቡን ለመስራት የተነሳሳችው ለልማታዊ ተግባር የኤልክትሪክ ሃይል ለማመንጨት እንደሆነ እና ለትብብር በሯ ክፍት እንደሆነ ከመጀመሪያው ማሳወቋ፡ ይህን ተከትሎ የተቋቋመ የሶስትዮሽ የባለሞ ያዎች ቡድን ባደረገው ጥናት ግድቡ ዓለም ዓቀፍ ስታንዳርዶች እንደሚያሟላ እና ጥቅም እንጂ ጉዳት እንደሌለው እያሳወቀ ያንን ችላ በማለት ባለሞያ የተባሉት እኚህ ግለሰብ ”ግብጽ የራሷን ፍላጎጎት የማስጠበቅ መብት አላት። ሌሎች ሰዎችም የራሳቸውን ፍላጎቶች የመጠቀም መብት ሊኖራቸው ይችላል። ሆኖም ግድቡ ግብጽን መጉዳት የለበትም። አለዚያ ሁሉም አማራጭ ክፍት ነው” ብለዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት የተጠየቁ የኢራን እና ፐርዥያ ጥናት ባለሞያ ይሄ የኢራን ህዝብ የሚደግፈው ከሆነ እጅግ አሳፋሪ ነው። ሆኖም ኢራናውያን በእንዲህ ዓይነት የከሰረ ንግድ አይሳተፉም ብሏል። ይህ የፖለቲከኞች ስካር ከመባል የማያልፍ ለግብጽም ምንም የማይፈይድላት ራስን ማስገመት ልንለው የምንችለው ተግባር ነው ሲሉ ባለሞያው አክለዋል።
ባለሞያው ኢራን ይህን ዜና ልታሰራጭ የሚኖራት ብቸኛ ምክንያት ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ካላት ወዳጅነት እና ኢራን በኒውክሌር ግንባታዋ ምክንያት ከአሜሪካ ጋር ጸበኛ በመሆኗ ነው። ይህን ጸብ ተከትሎ የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ማዕቀብ የጣለባት ሲሆን የአውሮፓ ህብረት ምንም ነዳጅ ከኢራን መግዛት አቋርጧል።
ስለዚህ የተቀጥያ ትንኮሳ መሆኑ ነው ያሉት እኚሁ ባለሞያ ናቸው።
posted by Dawit Gessese

No comments: