Friday, June 28, 2013


Ethiopian Muslims are holding protest rallies in Adama, Woldya and other cities in Ethiopia today

Ethiopian Muslims are holding protest rallies in Adama, Woldya and other cities in Ethiopia today.

በክልል ከተሞች ዛሬ ተቃውሞዎች ተደረገዋል፤ የአንዳንዶቹም በመደረግ ላይ ናቸው፡፡ አዳማ በአቡበክር መስጂድ የተከሄደዉን ታላቅ ተቃውሞ አንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በካድሬዎች ጥቆማ ተይዟል፡፡ 

የተካሀየደዉ ተቃዉሞ በሠላም ተጠናቆል በወልደያም ህዝብ አህባሾችንን አርበድብዷል:: በአሣሣ ከተማ ክራም መስጂድ ከጁምዓ ሶላት በኋላ ከባድ የሆነ ተክቢራ ተደረገ፡፡ 

በመስጂዱ የሚገኙ ምእመናን በሙሉ በአንድ ድምፅ ከፍተኛ ተክቢራ በማሰማት ሰላማዊዉን ተቃዉሞ በሰላም አጠናቀዋል፡፡ በከተማዋ ፌዴራል ፖሊሶች ሲዘዋወሩ የዋሉ ሲሆን፤ ምንም አይነት የጸጥታ ችግር እንዳልተፈጠረ ለማወቅ ተችሏል፡፡


Image
Jun 28, 2013 1:41pm
አዳማ በ አቡበክር መስጂድ የተከሄደዉን ታላቅ ተቃውሞ ከፊል ገጽታ፡፡ 

No comments: