Monday, June 24, 2013

ወያኔ ከ11 ቁጥር ጋር ያለው ጥብቅ ቁርኝት

       ወያኔ 11 ቁጥር ጋር ያለው ጥብቅ ቁርኝት


           ወያኔ በያመቱ ግንቦት 20 የሠፈር ሴቶችን በቀበሌ ሹመኞቹ እያሰለፈ አብዮት አደባባይ (መስቀል አደባባይ) መፈክር አሸክሞ ከማስጮህ ተቆጥቦ አያውቅም፡፡ ኢህአፓ ባንድ ወቅት አፍለኛ ፋኖ በነበረበት ወቅት አሮጊቶችን ሰብስቦየኡ ኡታ ኮሚቴአቋቁሞ ነበር፡፡ ዓላማው አንድ የኢህአፓ ነፍሰ ገዳይ የደርግን ደጋፊዎች ሲገል እንዳይያዝ በየሰፈሩ ያሉ የኡኡታ ኮሚቴዎች የተገደለው ልክ የነሱ ወገን አስመስለው እየተቀባባሉ ኡኡታን በማቅለጥ አደናግረው ገዳዩን እንዲያመልጥ ለማድረግ ነበር፡፡ ውጤቱ ግን አገሪቱን ዛሬም ድረስ የኡኡታ፣ የዋይታ፣ የሰቆቃ አገር ሆና ቀረች፡፡ ዋይታ ቀጥሏል፣ ኡኡታ ነግሷል . . .
          ኢህአዴግ ዘንድሮ ግንቦት 20 ድፍን 22 ዓመቱን በደመቀ ሁኔታ ባይባልም ዳቦ ያጡ ምስኪን ሴቶችን ከየቀበሌው አሰብስቦ አክብሮ ውሏል፡፡ ደርግም እንዲሁአኢሴማ፣ አኢወማ፣ መኢገማ . . .” እያለ አብዮቱን ወይንም መሥከረም ሁለትን ለማድመቅ ሞክሮ አልተሳካለትም፡፡ ኢህአዴግም ግንቦት 20 ለማክበር ምንም የማያውቁ ዳቦ ያረረባቸውን ሴቶች እየሰበሰበ ማስጮሁ በዚህ ዓመት የተጀመረ አይደለም፡፡ 22 ዓመታት አስቆጥሯል፡፡ ጠብ ያለ ነገር ግን የለም፡፡ እስቲ አሁን ደግሞ 11 ቁጥር ጋር ያለውን ቁርኝት እንመልከት፡፡
ህወሓት ገና ከጥንስሱ ወይንም ሲመሠረት 11 ታጋዮች እንደነበሩ እነሱ ራሳቸው ለጉራም ይሁን ለቁም ነገር የሚተርኩልን ነው፡፡ እየመረረንም ቢሆን ማዳመጣችን አልቀረም፡፡ ህወሓት ግንቦት 20/1983 . አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ አስተዳደሩን ያዋቀረው በዘጠኝ ክልሎችና በሁለት ልዩ አስተዳደሮች ነው፡፡ (አዲስ አበባና ድሬደዋ ከተሞች) ሲደመሩ 11 ቁጥሮች ይሆናሉ፡፡ ኢህአዴግ የሚገዛትን አገር የኢኮኖሚ እድገት ሲያበስር የሕዝብን አንጀት ግን በርሃብ ሲያስር11 በመቶ ተመንድገናል፡፡ ወይንም አስደናቂ እድገት አስመዝግበናል፤ አይ ኤም.ኤፍ (ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም) መስክሮልናልይለናል፡፡ የሚገርመው ግን ነዳጅ የሚያመርቱ አረብ አገራት እንኳን 11% እድገት አስመዝግበው አያውቁም፡፡ እኛ ግን በየአመቱ 11 ቁጥር የተጣባን ይመስል አስራ አንድ በመቶ አድገናል እየተባልን እስካሁን 22 ጊዜ ተዋሽተናል፡፡ በዚህ ቢበቃን ጥሩ ነበር፡፡ ግን የመከራችን ጽዋ ገና ሞልቶ አልፈሰሰም፤ ምን ያህል አሥራ አንዶች እንደሚቀሩን አናውቅም? ሌላው 11 ቁጥር ጋር የሚቆራኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር የተባለው ሲሆን ከግጥሙ ርእስ ጀምሮ ያሉትን ስንኞች ብንቆጥራቸው አሥራ አንድ ናቸው፡፡ ምን ዓይነት ንግርት ነው? ተማሪዎች ብሔራዊ መዝሙሩን እየዘመሩ ባንዲራ ሲሰቅሉና ሲያወርዱ በጥንቃቄ የሚያጤኑ ከሆኑ ካረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ አርማችን (ዓላማችን) መሀከል ያለውን በሰማያዊ መደብ ላይ ወርቃማ ቀለም የተቀባውን ቢጫ ኮከብ ወይንም ባለ አምስት ጨረር ደማምረን ስንቆጥራቸው አሥራ አንድ ይሆናሉ፡፡ ገዥው ፓርቲ ዲግ ሌሎችም የሚታወቅባቸው 11 ቁጥሮች እንዳሉትም ለማወቅ ችያለሁ፡፡ ወደፊትም በርካታ 11 ቁጥሮችን ከእድገታችን ጋር እንደሚያስመዘግበን አንጠራጠርም፡፡

ኢትዮጵያ ክብር ለዘላለም ትኑር!

No comments: