Sunday, June 9, 2013

የትግል እንቅፋቶች ስብስብ የሆነው መድረክ ራሱን ይመርምር

የትግል እንቅፋቶች ስብስብ የሆነው መድረክ ራሱን ይመርምር :: ሰማይዊ ፓርቲ ራስህን አጥራ ::ራእይ ለወጣቶች የተባለውም ማህበር ደግመን እንናገራለን ራስህን ሰልል:: አዛውንቶች ከፖለቲካው መስክ በክብር ቢሰናበቱ የተመረጠ ነው::የእሁዱም የሰማያዊ ርቲ ሰልፍ “የኢህአዴግ ድራማ ሊሆን ይችላል” / በየነ ጴጥሮስመጠላለፍ ይላሉ ይህ ነው!!! ቅናት ነው ምቀኝነት ??? ምን ይባላል??

ላለፉት 22 አመታት ከወይኔ ጎን ለጎን ሆነው አንዴ ባለስልጣን አንዴ ተቃዋሚ አንዴ ምናምን እየሆኑ ያገለገሉት በየነ ጴጥሮስ የሰማያዊ ፓርቲን ሌላኛው ኢዴፓ እንደማለት አድርገው የተቹ ሲሆን ሰልፉም ወያኔ ያቀነባበርው ድራም እንደሚሆን ተናግረዋል:: በቆዩባቸው የፖለቲካ አመታቶች ዉጤት ያላመጡት እና ባንድ ዛቢያ ሲሽከረከሩ ያረጁት / በየነ ይህንን ሰልፍ በምን አይነት ሞራል ሊተቹ እንደቻሉ አጠያያቂ ሆኗል:: አሁንም የትግል እንቅፋቶች ስብስብ የሆነው መድረክ ራሱን ይመርምር :: ሰማይዊ ፓርቲ ራስህን አጥራ ::ራእይ ለወጣቶች የተባለውም ማህበር ደግመን እንናገራለን ራስህን ሰልል::አዛውንቶች ከፖለቲካው መስክ በክብር ቢሰናበቱ የተመረጠ ነው::


ባለፈው እሁድ በሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ፣ 97 ምርጫ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ መሆኑን የሚናገሩት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ ላለፉት ስምንት ዓመታት እንኳን ሰልፍ ስብሰባም ማካሄድ እንዳልቻሉ በመግለጽ፤ የእሁዱም ሰልፍየኢህአዴግ ድራማ ሊሆን ይችላልበማለት እንደሚጠራጠሩ ገለፁ ፡፡ የመድረክ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ / በየነ ጴጥሮስ፤ እስከአሁን ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ይቅርና አዳራሽ ለመከራየት እንኳን ሆቴሎች የመስተዳድሩን ፈቃድ አምጡ እያሉ ሲያስቸግሯቸው እንደነበር ገልፀው፤ የሰሞኑ የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍም ምናልባትም ከአፍሪካ ህብረት ጋር በተያያዘ ኢህአዴግ ያደረገው ጨዋታ ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡

ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት እኛም ዕቅድ ይዘን እየተነጋገርን ነውየሚሉት / በየነ፤ ኢቴቪ ሰልፉን መዘገቡን ብቻ በማየት መሻሻሉን ለማወቅ እንደማይቻል ገልፀዋል፡፡ኢቴቪም ቢሆን ድራማውን እየሰራ ይሆናልበማለት ዘገባውን የሰራው አንዳንድ የሚያስወነጅሉ ጉዳዩች ላይ በማተኮር ነው ብለዋል፡፡አላማቸውና መሻሻላቸው የሚታወቀው ወደፊት መቀጠሉ ሲታይ ነውብለዋል - ፕሮፌሰሩ፡፡ የመድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ / መረራ ጉዲና በበኩላቸው፤ ሰላማዊ ሰልፉ መካሄዱ ችግሮችን ካልፈታ ልክ በአረብ አገራት ላይ እንደታየው አይነት ችግሮች ሊከሰት እንደሚችል ይናገራሉ፡፡የህዝብ ችግር እስካልተፈታ ድረስ ህዝብ አንድ ቀን በቃኝ ሊል ይችላል - መብቱ ካልተከበረለትና የሚበላው ካጣ ችሎ የሚቀመጥበት መንገድ የለም፡፡ ይሄ ህዝብ መብቱ እንዲከበርለት፣ ነፃነት እንዲያገኝ፣ በልቶ እንዲያድር ይፈልጋል፡፡ ኢህአዴግ ይህንን ችግር መፍታት ካልቻለ፣ ህዝቡ አሁንምመሪውን ይበላልየሚባለውን ሊተገብር ይችላል፡፡የሚሉት / መራራ፤ እኛን አዳራሽ እየከለከሉ ለሌላው ሰላማዊ ሰልፍ የሚፈቅዱት የህዝብ ሙቀት ለመፍጠር በማሰብ ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡

ምናልባትም የኢህአዴግ አዲስ አሰራር ከሆነ ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ፣ በነካ እጁ ለመድረክና ለሌሎች ፓርቲዎችም እንዲፈቅድ ጥያቄያችን ነውብለዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲዎች የሰላማዊ ሰልፍ ትርጉሙ አልገባቸውም:: አቶ በረከት ስምኦን ...ይህንን ያሉት ከወያኔ አመራሮች ጋር በጋር በተደረገ አጭር ስብሰባ ላይ ሲሆን ሚስታቸው ላይ እንደለመዱት በወቅቱ በቁጣ እና በጩሀት ይናገሩ እንደነበር ምንጮች ጠቁመዋል:: አቶ በረከት ካድረዎቻችን ገበናችንን እየሸጡ ያዋርዱናል:በማለት ለመጪው ጊዜ ያላቸውን ስጋት ጭምር ገልጸዋል::

No comments: