በናዝሬት አዳማ ከተማ ላይ የህዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ ተቃውሞ በሃይል ለማስቆም በተጠራው ስብሰባ ላይ ከተካፈሉት አቃቤ ህጎች እና ዳኞች መካከል 15ቱ በመኪና አደጋ ሂወታቸው አለፈ
በናዝሬት አዳማ ከተማ ላይ የህዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ ተቃውሞ በሃይል ለማስቆም በተጠራው ስብሰባ ላይ ከተካፈሉት አቃቤ ህጎች እና ዳኞች መካከል 15ቱ በመኪና አደጋ ሂወታቸው ማለፉ ተሰማ::
ለ 15 ቀናት ያክል በቆየው እና ትላንት በተጠናቀቀው በናዝሬት አዳማ ከተማ ሲካሄድ በነበረው በኢትዬጲያ እየተጠናከረ የመጣውን የህዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ ተቃውሞ በሃይል ለመስቆም በሚቻልበት መንገድ ላይ የሚመክር ስብሰባ ተካፍለው ከነበሩት አቃቤ ህጎች እና ዳኞች መካከል 15ቱ ሞጆ ከተማ ላይ በገጠማቸው የመኪና አደጋ ሂወታቸው ማለፉን እየተነገረ ነው፡፡፡
ትናንት ሌሊት በሞጆ ከተማ በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ሹፌሩን ጨምሮ 16 ሰዎች መሞታቸው የተነገረ ሲሆን ሌሎች አምስት ተካፋዬችም ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
አደጋው የደረሰው ኮድ 3 አዲስ አበባ የሰሌዳ ቁጥሩ 27 8 55 የሆነው የሚኒባስ ተሽከርካሪ ከተፈቀደው የጭነት ልክ በላይ ዘጠኝ ትርፍ ሰዎችን ጭኖ በመጓዝ ላይ በነበረበት ወቅት ነው ተብሏል።
ተሽከርካሪው ከመጠን በላይ በሆነ ፍጥነት ሲጓዝ በሞጆ ከተማ በብልሽት ከቆመ ማርቼዲስ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ አደጋው መድረሱን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ በአደጋው የሞቱት 16 ሰዎች አስከሬን በአዳማ ሆስፒታል ለጊዜው የገባ መሆኑንን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
No comments:
Post a Comment