Thursday, June 6, 2013

የአዲስ አበባ ተማሪዎች በፌዴራል እየተደበደቡ ነው

የአዲስ አበባ ተማሪዎች በፌዴራል እየተደበደቡ ነው!

EMF: ዛሬ ተማሪዎች ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱበት የመጨረሻ ቀን ነው። በዚህ የመጨረሻ ቀናቸው ተማሪዎች ስለፈተናው ማውራት፣ በቡድን በቡድን እየሆኑ መሄድ የተለመደ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም ካለፈው የግንቦት 25 ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በኋላ ገዢው ፓርቲ ውስጥ ውስጡን በንዴት ሲጦፍ ከርሞ አሁን እነዚህን ተማሪዎች፤ “ለምን በቡድን በቡድን ሆናቹህ ትሄዳላቹህ?” በማለት፤ ፌዴራል ፖሊሶች በአሰቃቂ ሁኔታ በማባረር እየደበደቧቸው መሆኑን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ አመልክቷል።

ከፈተና በኋላ ተማሪዎች ላይ የማሳደድ ድብደባ በፌዴራል ፖሊስ ደርሶባቸዋል።
ይህ በተለይ እየሆነ ያለው ከስድስት ኪሎ ንስካየ ህዙናን ተማሪዎች ጀምሮ የየካቲት 12 ተማሪዎችም እየተደበደቡ ናቸው። ጥቂት ተማሪዎችም በፖሊስ ተይዘው ተወስደዋል። ከላይ እንደገለጽነው፤ በፌዴራል ፖሊስ በኩል የበቀል እርምጃ እየተወሰደ ያለ ይመስላል። ተጨማሪ ዘገባዎች ካሉ በዚህ ጉዳይ እንመለስበታለን።

No comments: