Wednesday, June 26, 2013

እርስ በእርስሲያናቁረንዝምብለንከተመለከትን

       እርስ በእርስ ያናቁረን ዝም ብለን ከተመለከትን

         የመሪዎች ሥልጣን በምድር  ከጠመንጃ አፈሙዝ የሚመጣ፣በሰማይ ደግሞ ፈጣሪ ይሁንታ እንዳለበት የምናመን ይመስለኛል፡፡ መሪዎቻችን አሁንም ሥልጣናቸውን የሚያገኙት ከመለኮታዊ ኃይል ንደሆነ አድርገው ይወስዱታል፡፡ ዘመናዊ ለመምሰል የዴሞክራሲ ጭምብል ያጠልቃሉ፤በይዘት ግን ፈላጭ ቆራጭ አምባገነኖች ናቸው፡፡ በዚህ መልክ፣የኢህአዴግ ሥርዓት ቁንጮ ነጥረው ወጥተዋል፡፡ ምድረ-ኢትዮጵያ በሙሉ የእሳቸው ሆናለች፡፡ መሬቱን ከሕዝቡ ነጥቀው ወስደዋል፤መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢህአዴግ ጭሰኛ ሆኗል፡፡ የአፄው ሥርዓት እንኳን ይህን አላደረገም፡፡ ኢህአዴግ የሕዝቡየዓይን ቀለም ስላላማረውሕዝቡን ከመሬቱ ነቅሎ፣የሚያምር የዓይን ቀለም ባላቸው ፈረንጆች ለመተካት እየሞከረ ነው! የሀገሪቱን የወርቅ ማዕድናት ለፈረንጆች ወይምፈረንጅ ለሚመስሉ ሰዎችሰጥቶ የትርፍ ተካፋይ ሆኖአል
           ኢህአዴግ እኛ ኢትዮጵያውያንን በመጣለት ሁሉ እየከፋፈለ እርስ በእርስ ቢያናቁረን ዝም ብለን ከተመለከትን፣መጥፎ ነገር ተገዢ ሆነናል ማለት ነው፡፡ ኢህአዴግ የሰዎች ስብስብ ነው፤እናም ኢህአዴግበስሜ ማሉ፣አምልኩኝ፣ስገዱልኝሲል አሜን ብለን ከተቀበልን፣የፈጣሪ ፀጋ ሁሉ ከእኛ ይርቃል፡፡ ስለዚህ፣ፆምና ፀሎታችንን አጥብቀን እንቀጥላለን፤በንፁሕ ልቦና፡፡ ኃጢያት እየሠሩ ቤተክርስቲያንም ሆነ መስጊድ መሄድ ፈጣሪን እንደ ማታለል ይቆጠራል፡፡ እየሰከሩ፣ጫት እየቃሙ፣ሲጋራና ሀሺሽ እያጨሱ ፍቅር የለም፤ጥላቻና ሞት ነው! የኢትዮጵያ! ወጣቶችን ወደየወሲብ ቁስ አካልነትለማውረድ የሚሞክረውን ኢህአዴግ በፆም በፀሎት ብቻ ሳይሆን፣በሰላማዊ ትግል ስልቶች መፋለም ይገባናል፡፡ ታሪካዊ ዋጋ የተከፈለበትን ታሪካዊ ውርስ የሆነ መሬት ለባዕዳን አንሰጥም ብለን እንጩህ! “ከእናት ሀገራችን ቅድስት ኢትዮጵያ ማህፀን የተገኘውን ወርቅ ኢህአዴግና ባዕዳን እንዲዘርፉት አንፈቅድምእያልን ድምፃችንን እናሰማ! ከኢኮኖሚ ልማት አኳያ፣እንዴት አንድ ሀገር የወርቅ ማዕድኑን ለባዕዳን ይሸጣል
       በሌላ በኩል፣በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵየ ሕዝብ ፀጥ ለጥ ብሎ በኢህአዴግበጊንጥ እየተገረፈ ነው፡፡ እየተራበና ከአፉ እየነጠቀ ለኢህአዴግ መንግሥት ግብር /ቫት/ እየከፈለ ነው፡፡ አፅመ ርስቱን በአዋጅ ሲነጠቅ ዝም ብሎ እየተገዛ ነው፡፡ መከራው የበዛበት ሀገር ጥሎ በአራቱም ማዕዘናት እየተሰደደ ነው፡፡በሀገራችን በኢትዮጵያ ደሞክራሲያዊ ሥርዓት በትግል ሊገነባ ይችላል ብሎ ሕዝቡ የሚያምን አይመስለኝም፤  ከባሕላዊና ጥንታዊ አስተሳሰቡ ገና ሙሉ በሙሉ አልተላቀቀም፡፡ እንዲያውም ኢህአዴግኑ ውጡና አወድሱኝ፣ስገዱልኝ፣አደግድጉልኝእያለ ሲሰራ፣ በነቂስ እየወጣ ኢህአዴግን ያኑርልንእያለ ውዳሴ-ኢህአዴግ ያስተጋባል፡፡ እርግጥ፣በልቡ ሌላ ነገር ይሆናል የሚያስበው፤ፈጣሪ ከዚህ ጭራቅ መንግሥት ገላግለንየሚል ሊሆን ይችላል፤ግን አሁንም እግዚአብሔር ካልፈቀደ በስተቀር በሀገራችን ለውጥ ይመጣል ብሎ የሚያስብ አይመስለኝም፡፡
            ኢህአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲን የሚቃወም በኢትዮጵያ መሬት እንዲኖር አልፍቅድም በማለት ላለፉት ዓመታት በትጋት ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ገዢው ፓርቲ የሃይማኖት ተቋሞችን አብዮታዊ ዴሞክራሲን የሚሰብኩ ካድሬዎች የሚርመሰመሱበት ከማድረግ ጀምሮ የመንግስት ሠራተኛውን፣ መምህሩን፣ ተማሪውን፣ አርሶአደሩን (አርብቶ አደሩን) ነጋዴውን በአጠቃላይ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፀበል በግድ በዘመቻ ሲያጠምቅ የከረመው ኢህአድግ አስርቱን የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ትዕዛዛትን አውጥቶ በማስፈፀም ላይ ይገኛል፡፡


ኢትዮጵያ ክብር ለዘላለም ትኑር!

No comments: