Wednesday, June 19, 2013

አደብና ወደብ ያሳጣን መንግሥት ሲኩራራ ይገርመኛል

       አደብና ወደብ ያሳጣን መንግሥት ሲኩራራ ይገርመኛል

           በተለያዩ ዘርፎች የተለያዩ አመለካከቶች ይኖሩናል፡፡ ለፃድቃን ያለንን አመለካከት ለማንም ተራ ሰው መያዝ አንችልም፡፡ አሊያም ለቤተ ክርስቲያን ያለንን ክብር ለመንግሥት ላይኖረን ይችላል፡፡ እንዴትስ ሊኖረን ይችላል? መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን የተለያየ አለማትን ለማዉረስ የሚሰሩ ናቸዉ፡፡ መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን የተለያየ አለማትን ለማየት የሚፈልጉ ተቋማት ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ያላትን ይዛ የምትቆይ ዋጋዋም፣ ድርሻዋም የማይለዋወጥ ናት፡፡ ለመንግሥት ይህ ይሆናል ብዬ አላስብም፡፡ ለምሳሌ የአሁኑ መንግሥት ከቀድሞው የመሻል ተፈጥሯዊ ግዴታ አለበት፡፡ -መደበኛ በሆነ አኳኋን ምንም ቢሆን የምንሄደው ወደ ፊት ነው ይባላል፡፡ በመሆኑም ኢህአዴግ ተነስቶበትራንስፖርቱ ዘርፍ በአፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት ከነበረው 1000% አሻሽዬዋለሁቢል ቁጥሩ ጉዳይ ሆኖ መነሳት የለበትም፡፡ መነሳት ያለበትበዘመኑ ትራንስፖርት መች ነበር?” የሚል ጥያቄ ነው፡፡ ይህን ጥያቄ ያልጠየቀ ሰው በቀጥታ የኢህአዴግ ወጥመድ ውስጥ መውደቁ አይቀሬ ነው፡፡ ምክንያቱም የኢህአዴግ ትልቁ ችሎታየቁጥር መረጃ መጋገርነውና፡፡በርግጥየኢህአዴግን ቁጥር ያመነ ጉም የዘገነአንድ ናቸው ማለት እችል ነበር፡፡ ነገር ግን ይህኛው ፍሬ ነገሩን ‹‹አለመጨበጥ›› ብቻ አድርጎ ያስቀረዋል፡፡ እናላችሁ 11.2 በመቶ እያደጉ መኖር ከዚህ የተለየ ትርጉም የለውም፡፡ ደግሞ አደግን እንበል፣ ኑሮ ተወዶም፣ ህይወት ተወድዳም፡፡ ግን እኮ የምናድገው አንዲት የአሜሪካ የዞን ከተማ ከምታድገው ኢኮኖሚ 11% እና ከዚያ በታች በሚያንስ ድምር ነው፡፡ መቼም የህይወታችንን መሻሻል አለመሻሻል ለመገንዘብ የግድ ኢኮኖምክስ መማር አለባቸው የሚል እምነት የያዘዉ የአቶ መለስ መንግሥትኑሮ የተወደደው፤ የዋጋ ንረቱ የጦዘው በምናስመዘግበው ተምዘግዛጊ የኢኮኖሚ እድገት ነውይሉናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይ የነኩት ሁሉ ወርቅ እንደሚሆን ሁሉ አሉታዊ የተባሉ ነገሮች በገጠሙ ቁጥር ዕድል አድርገው ያቀርቡታል፡፡ ባለፉት 21 ዓመታት ሁለት ተመሳሳይ ነገሮችን አስተውዬባቸዋለሁ፡፡ አንድኛ ሁሉንም ነገር ወርቅ አድርጎ ማቅረቡ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሁሌም የሚገኙበት የጠቅላይነት መንበራቸው ነው፡፡
            የኑሮ ውድነት ከተነሳ ዘንዳ አንድ ነገር ልመርቅ፡፡ አንዲት ባለ ግሮሰሪ በአስር ብር ለገዛችው ሳር እንኳን ለቤቷ፣ ለጀበናዋ ረከቦትም የማትሆን ነበረች፡፡ ታዲያ ይህን ያየ እንድ ተጠቃሚወገን ይሄ ደግሞ ምን ቢሆን ነው ዋጋዉ እንዲህ የተሰቀለው? የተመረተው በኛው ሀገር ነው ግን?” ሲል ጠይቋል፡፡
             አቶ መለስ መንግሥት በትልቁ የሚከሰስበት አንዱ ጉዳይ ብሔራዊ/ሀገራዊ አንድነትንና የብሔር ብሔረሰቦችን መብት ማመጣጠን ያለመቻሉ ነው፡፡ የአቶ መለስ ቡድን በአመፂ አብዮተኝነት ስልጣን የጨበጠ በመሆኑ ነገሮችን ከባዶ መጀመር መፈለጉ ያስማማል፡፡ ነገር ግን እጅግ በበዛ መልኩ የቀድሞውን የብሔራዊ አንድነት መንፈስ በብሔር ብሔረሰቦች መብት ለመገዳደር ስል ሌላኛውን ጫፍ ያዘ፡፡ ይህን ባነሳሁ መጠን 1960ዎቹ እጅግ ተወዳጅ የነበረውን ጨቋኝ ተጨቋኝ /Dependency theory/ ማውራት ይቀናኛል፡፡ አብዮተኞቹ የዚህን ፅንሰ ሀሳብ አንድ አቅጣጫ በመውሰድ ኤርትራ እንድትገነጠል፣ ሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎችም የመገንጠያ የህግ ድጋፍ የሚሆን ህገ መንግሥት በመስራት ደመደሙ፡፡ የሰሞኑ የደቡብ ክልል አሉታዊ ብሔርተኝነትም ከዚህ መች ይዘላል፡፡ የአንድ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሆኑትን አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤን ‹‹አማሮች ወደ ሀገራችሁ›› ያሰኛቸዉ ምን ሆኖ ነዉ፡፡
         ዛሬም ድረስ የአሰብ ጉዳይ እንደ አዲስ ያሳስበኛል፡፡ በርግጥ የመለስ ዜናዊ መንግሥት ‹‹የአሰብ ናፋቂ›› ሊለኛ ይችላል፡፡ ሆኖም ዛሬም አሰብ ሄጄ መዝናናት ያምረኛል፡፡ ሞምባሳ፣ አሊያም ሲሸልስ አሊያም ሲንጋፖር ለምን እንደማይናፍቁኝ አላውቅም፡፡ አዎን የመለስ መንግሥት በብሉይ ትንተና ቢፈረጀኝና ቢከሰኝም አሰብን ከነ የአሰብ ራስ ገዝ መሬቷ እናፍቃታለሁ፡፡ ይህ ለጅቡቲ በቀን 300 ሚሊዮን ዶላር በላይ በመክፈላችንም አይደለም፡፡ አሰብ ከነ ግዛቷ የኢትዮጵያ መሆኗን ከልቡናዬ በተጨማሪ / ያዕቆብ /ማርያምን አንብቤ አሰብን ያሳጣን ህወሓት እንጂ ህግ ያለመሆኑን፣ ተፈጥሮ ያለመሆኗን በማረጋገጤ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሚያውቋቸው ሸቀጦች በቀን 300 ሚለዮን የሚያስወጣው ወደብ ብቻ ነው፡፡ ወደብ ከመግቢያ መውጪያነቱ በተጨማሪ የያዘውን የደህንነት ጥቅም መዘርዘር አያስፈልገኝም፡፡
            አቶ ስብሃት ነጋ የኤርትራ /አሰብ ጉዳይ ከተነሳ ደግሞ ደደቢት እንደሚገኙ አቋም መያዛቸው ይነገራል፡፡ በአጠቃላይ ህወሓት ውስጥ የመለስ ቡድን የሚባለውኤርትራዊነትንበማበረታታትና በማቀንቀን ይታወቃል፡፡ በአጠቃላይ ‹‹በመቀነስ›› የሚኩራራ መንግሥት አለን፡፡ አቶ መለስ ደመሩ ከተባለ ‹‹ዜሮ ሰም ጌም›› ከማለት አይዘሉም፡፡ መቀነስ ቢያቆሙ ከዜሮ የሚበልጥ ነገር አይደምሩም፡፡ በተቃራኒዉ አጤ ምኒልክ በማስፋታቸዉ/በመደመራቸዉ ሠይጣን ተደርገው ይሳላሉ፡፡
           አመራር እንደሚወስን መረዳት ይቻላል፡፡ ‹‹አመራር እዉቀቱ ብቻ ሳይሆን መንፈሱም ይፈለጋል›› ይላሉ የዘረፉ ባለሙያዎች፡፡ መሪዎቻችን ለማህበራዊና ስነ ልቡናዊ ብልፅግና ለምን እንደማይጨነቁ ለማሰብ እሞክራለሁ፡፡ ዋናው ነገር በዚህ ዘርፍ ብዙም ያልተሳካላቸው በመሆናቸው ለኛም ጭንቅ የለባቸውም፡፡ ዴሞክራሲ፣ መልካም ስነ ምግባር፣ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት አልተሳኩም፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ በዚህ በኩል ወድቋል፡፡ በመሆኑም ተቃራኒው ተሳክቷል፡፡ስለ መፃህፍትየተባለ ፕሮግራም ሰሞኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ ቀርቦ ነበር፡፡ አንዱ ታዳሚ ‹‹ለተማሪዎቻችን ምን የንባብ ባህል ሰጠንና መልካም አንባቢ እንጠብቃለንሲል ለጠየቀው ጥያቄ / ፈቃደ አዘዘ የራሳቸውን አስተያየት ሲሰጡ “9 ክፍል ስማር ከተሰጡኝ 13 መፃህፍት አንዱ ዌብስተርስ ዲክሽነሪ ነበር፤ የክፍል ውስጡን በአንድ በኩል የመፃህፍቱን በሌላ ትይዩ እያፃፍኩ ነው የማመሳክረው፤ በመሆኑም አጠሬራ ይዤ ለፈተና ክፍል አልገባም ነበርብለዋል፡፡ / ፈቃደ በተቃራኒው ቸልታችን ትክክለኛውን ፍሬ ማፍራቱን ተናግረው ነበር፡፡

           በዲሽ ባመጣነው ነገርማንቼ አርሴንአፈራን፡፡ ሀይላቸንን ስራፈት በማድረግ በጫትና በተለያዩ ሱሶች የናወዘ ትውልድ በበቂ ሁኔታ ማፍራታችን ይታወቃል፡፡ ጫት የተስፋ ማጣት፣ በተፈጥሯዊው በራስ ያለመተማመን፣ እንዲሁም የውሸት ሽግግ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እንጠጣለን፣ አንዳንድ ሰዎች ወጣቱ የጫት ትዉልድ ሆኗል ይላሉ፡፡ በኤድስ እንሞታለን እንዘርፋለን፡፡ ቅብዝብዝ ሆነን ምን አደብ አለን፤ አደብ የሚገዛዉ የተረጋጋ ትዉልድ ነዉ፡፡ በአጠቃላይ አደብም አሰብም ያሳጣን መንግሥት ግን ይኩራራል፡፡

No comments: