Tuesday, June 25, 2013

በቁርሾና በቂም አንገቱን ለደፋ ህዝብ ስለልማት ማውራት ከፈረሱ ጋሪ እንደ ማስቀደም ነው

በቁርሾና በቂም አንገቱን ለደፋ ህዝብ ስለልማት ማውራት ከፈረሱ ጋሪ እንደ ማስቀደም ነው
በመሠረቱ የሰው ልጆችና ልማት ተደጋጋፊዎችና ተመጋጋቢዎች ናቸው፤ ቢባልም ልማት ከውጥን እስከተግባር የሚከናወነው በፍቅር በመተማመንና በመከባበር በታነጸና በተገነባ የቤተሰባዊነት መንፈስ በዳበረ ጤናማና ሠላማዊ ሕብረተሰብ እንጂ በቁርሾና በቂም አንገቱን ለደፋውና ዝምታን ለመረጠው ሕዝብ ልማት ከፈረሱ ጋሪውን እንደማስቀደም ያህል ነው
     ስለሆነም በሀገራችን የዜጎቻችን መሠረታዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በትክክል መተግበር፣ የሰብአዊ መብቶችና የግል የህሊና ነፃነት፣ የፕሬስ የመናገርና የመፃፍ፣ የመሰብሰብና የሠላማዊ ሠልፍ ሕገ-መንግስታዊ መብት መረጋገጥ ጉዳይ ከእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ጋር ቢያንስ ጎን ለጎን ማስኬድ በተገባ ነበር በሀገራችን ታሪክ በምርጫ ካርድ ሳይሆን በትጥቅ ትግልና በጠመንጃ የመንግስት ሥልጣን ቅብብሎሽ የተነሳ በየሥርዓቶቹ አራማጆችና ደጋፊዎቻቸው እንዲሁም በአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍሎችና ቡድኖች መካከል በተለያዩ ወቅቶቹና ምክንያቶች የተፀነሰው የፍትህ እጦት፣ ፖለቲካዊ ቁርሾና ቂም በቀልሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ፀሎትእንዳይሆንብን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለወሳኙብሔራዊ መግባባት ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያመቻቹ የመወያያና የመነጋገሪያ መድረኮች መከፈት እንዳለባቸው ይህም ለአብሮነታችንና ለአስተማማኝ ሰላማችን ለእድገታችንና ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለጥንካሬአችንና ለክብራችን ብቸኛ መንገድ ተብሎ በብዙዎቻችን ዘንድ የታመነበት በመሆኑ ኢህአዴግን ጨምሮ በተቃዋሚ (ተፎካካሪ) የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ቅንነትንና ግልፅነትን የተላበሰ ከዘረኝነት፤ ከፀበኛነትና ባላንጣነት መንፈስ የፀዳ የመልካም ግንኙነትም ምዕራፍ እንዲከፈት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጭፍን ጥላቻ ፖለቲካ ማራመድ እንደማይፈልግ ቂም በቀልና ቁርሾን ማየት እንደሌለበት ሕይወት አግኝቶና ነፍስ ዘርቶ ሥራ ላይ እንዲውል እንዲደረግ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ አገር ምን ኢትዮጵያውያን ዜጎች በሙሉ በፖለቲካ መስመሮቻቸ በኃይማኖታቸውና በእምነቶቻቸ በዘር፣ በጎሳና በክልላዊነት፣ በጾታና በቋንቋ ወዘተ መከፋፈልን አጥብበው ለብሄራዊ ጥቅማችንና ለኢትዮጵያዊነታችን ልዕልና ሲባል ሠላማዊ፣ ነገር ግን ወሳኝ የተባበረ ጫና በመንግስትና በፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ እንዲያሳርፉ፡፡ ማንኛውም ሠላም ወዳድ ዴሞክራትና ቅን አሳቢ ዜጋ፣ ታዋቂ ግለሰቦች የኃይማኖት አባቶች (መሪዎች) የሀገሪቱ ምሁራን፣ የግል ባለሀብቶችና የንግድ ተቋማት፣ የመንግስትና የግል ድርጅቶች ሠራተኞች፣ መምህራንና ተማሪዎች የግልና የመንግስት የሚዲያ ተቋማት፣ የሙያና የሲቪክ ማህበራት፣ አርሶ አደሩ፣ አርብቶ አደሩና . . . ወዘተ ሁሉም ያለልዩነት ለብሔራዊ መግባባት መሳካት ሁለንተናዊ የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ፣ ሌሎች ተራማጅና ዲሞክራት የውጭ ሀገር መንግስታት፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የግጭት አስወጋጅ ድርጅቶ እና ሌሎችም የሚሰጡን የትብብር መስኮች ቢኖሩ ሕጋዊ መስመሮች ተዘርግተው ልምዳቸውን የሚያካፍሉን ሁኔታዎች እንዲመቻቹ፣ ላለሁ።
         በአንድ ሀገር ህዝብ እንደ ህዝብ በብልሹ የአስተዳደር ሥርዓቱ ላይ የሚያቀርባቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሞራላዊ የፍትህና የዴሞክራሲ፣ የመብትና የነፃነት ጥያቄዎችና የሚወስዳቸው እርምጃዎች ሁል ጊዜ ሰላማዊ ይሆናሉ ወይንም እንዲሆኑ ይገደዳሉ ኃይልን መጠቀም ወይም በኃይልና በጡንቻ መመካትና መተማመን አርቆ አስተዋነትና ጤናማ መፍትሄ ነን ለማለት አያስደፍርም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በወርቃማ ምሳሌነቱ ሲጠቀስና ሲሞገስ የሚኖርበትን ሁኔታ መፍጠር ይቻል ዘንድ የቤታችንና የጓዳችንን ሁሉ አቀፍ ችግሮች ራሳችን በራሳችን በጠረጴዛ ዙሪያ በግልፅነትና በቅንነት በመነጋገር፣ በመወያየትና ብሔራዊ መግባባትን በማዳበር ብሎም በፈርሃ እግዚአብሔርና በሠለጠነ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የመደማመጥ መርሆቻችን ላይ ተመሰርተን መሠረታዊ ችግሮቻችንን በሰላማዊ የጋራ መድረክ በውይይት የምንፈታበትን ጊዜ እናመቻች ስል መልዕክቴን እዚህ ላይ ላብቃ ።


ኢትዮጵያ ክብር ለዘላለም ትኑር!

No comments: