Wednesday, June 26, 2013

“ብሦት” የወለደው” ኢሕአዴግ ሚሊዮን ብሶተኞችን በየቀኑ እያመረተ

ብሦትየወለደውኢሕአዴግ ሚሊዮን ብሶተኞችን በየቀኑ እያመረተ
         በኢህአዴግና በደርግ መካከል የአፈፃፀም እንጂ የመርህ ልዩነት አለ ብሎ ለመናገር ያስቸግራል፤በተለይ በፀረ-ሽብር ሕጉ በብልጠትና በማናለብኝነት የሚፈጸም ልዩነት ብቻ ነው ያለው፤በደርግ ጊዜ አሸባሪ ካላቸው ቡድኖች/ ግለሰቦች ጋር የተገናኘ፣የተሰበሰበ፣ጽሑፋቸውን የበተነ፣ያስበተነ፣በጽሑፍ ደረጃ ሕግ ሆኖ ባይወጣም ቀይ ሽብር ይፋፋምበታል፡፡ በኢህአዴግም ቢሆን ሽብርተኛ ብሎ ከወነጀላቸው ጋር ስልክ የተደዋወለ፣አብሮ የተቀመጠ፣ ጽሑፎቻቸውን ያነበበ፣ሊያነብ ያሰበ፣ያስነበበ . . . የፀረ-ሽብር አዋጁ ተጠቅሶበት ወደ ቃልቲ ይወረወራል፡፡ በዚህም የደርግና የኢህአዴግ የፀረ-ሽብር የቀለም ካልሆነ የሌላ ልዩነት እንደሌለው ያሳያል፡፡
        በአሁኑ ወቅት 40 የሚበልጡ ፓርቲዎችቢኖሩም እንኳን ከጥቂቶቹ በቀር ከገዢው ፓርቲ ጋር ያላቸው የአመለካከት ልዩነት ይሄ ነው የሚባል አይደለም፡፡ ሁሉም የተቃዋሚ ሥራ አመራሮች ሰጥቶ የመቀበል ልምድ ሳይሆን የመቀበል አባዜ ብቻ ስለተጠናወታቸው ነው፡፡ እነርሱ ካሉበት ድረስ ሌላው እንዲመጣላቸው እንጂ አንድ ስንዝር እንኳ ወደዚያኛው የመሄድ ፍላጎት የላቸውም፡፡ ከሁለቱም ወገን መጥራት እንጂ መሄድ አይታወቅም፡፡ በአንድ አስገዳጅ ሁኔታ ለመቀራረብ ሲሞክሩ እንኳን አንዳቸው መሄድ እስካለፈለጉ ድረስ መገናኘቱ ፈፅሞ አይታሰብም፡፡ ሁሉምእኔ አውቅልሃለሁኝ፡፡ያውቁበታል፡፡ በዚህ ዓይነት ይህ ሕዝብ እንዴት ታቅፎ ከተቀመጠው ጥያቄ ይገላገላል? በዚህ ወቅት የተሻለ የሚያስብ፣ ሰጥቶ መቀበል የሚችል ሰው ነው ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት፡፡ ይህ እስካልሆነ ድረስ የኢህአዴግን ጡንቻ ከማፈርጠም ያለፈ አንዲት ስንዝር መራመድ አይችልም፡፡ በተቃዋሚውም ዘንድ ጎልቶ ይታያል፡፡ የተቃዋሚ መሪዎች ይሁኑ ደጋፊዎች አንድን ሰው ብቻ ጎልቶ እንዲታይ በማድረግ ህብረተሰቡ ያለዚያ ሰው የተቃውሞው ትግል መላ ቢስ እንዲሆን አድርጎ አዲስ የትግል ሥልት ይዘው ሊመጡ የሚችሉ ሰዎች ከትግል ስልቶቻቸውና ከሙሉ አቅማቸው ጋር እንዳይወጡና አዲሱን የትግል ሥልት ይፋ እንዳያደርጉ ይታፈናሉ፡፡ የዚያ ፖለቲካ ድርጅት ደጋፊዎችም ቢሆኑ የዚህን ዓይነቱ ባህል ያጠቃቸዋል፡፡ በዚህም ሕብረተሰቡ አንድ ሰው ላይ ጥገኛ እንዲሆን የተለያየ ፊት እንዳያይ በተደረገው ሂደት ተጠያቂው የፖለቲካ ድርጅቱ ነው፡፡በዚህ ሁኔታ የሁለቱንም ጎራ ተጠያቂነት የሚያመጣ ነገር ሊከሰት እንደሚችል መገንዘቡ አይከብድም፡፡ ምክንያቱም ይህ ሕዝብ ጥያቄውን ታቅፎ ከአፄው ጀምሮ እስከ አሁን አለ፡፡ ጥያቄዎቹ እየተጨመሩ ሞልተው ከማፍሰስ ውጭ አንዳቸውም መልስ አላገኙም፡፡ በራሳችን መሬት ጭሰኞች እስከምንሆን ድረስ ሄደናል፡፡ ጉልበተኛ ሁሉ የሕዝቡን ጥያቄ ወንበር አድርጎ እንዳይቀመጥበት በሁለቱም በኩል ተገቢ የሚባል ሥራ ሊሰራ ይገባል፡፡ ሕዝብ የታቀፈው ጥያቄ አብጦ መፈንዳቱ አይቀርም፡፡ ሲፈነዳ ደግሞ አካባቢውን ሊያበላሸው ወይም ሊያሳምረው ይችላል፡፡ በዚህ መልኩ ከተቃዋሚዎች አንፃር የሕዝብን ጥያቄ ሊመልሱ የሚችሉና ሊያስመልሱ የሚችሉ ጠንካራ ታጋዮች ማፍራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከገዢው ፓርቲ ወገንም ቢሆን ሕዝቡ ጥያቄ የለውም፤ተስማምቶታል ከሚሉ ካድሬዎች ባለፈ ወረድ ብሎ እውነተኛውን የሕዝብ ጥያቄ መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢህአዴግ ስርዓት እንዲወድቅ የሚፈልገው የተበደለው ሕዝብና ከሕዝብ ጎን የቆመው የፖለቲካ ፓርቲዎች ብቻ ጭምር መሆናቸውን መገንዘብ ጥሩ ነው፡፡ በእኛ ሀገር የተለመደው አገዛዝ የባለቤትነት ነው፡፡
      ደርግም የሕዝብን ሥልጣን ለሕዝብ እንዲሆን እታገላለሁ ብሎ ቃል ገብቶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ሥልጣኑን ለማደላደል ሲታገል በሥልጣን ፈላጊዎች ባፍጢሙ ተደፋ፡፡ በዚህ ሂደት ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር እንደ ተቆለለ አለ፡፡ብሦትየወለደውኢሕአዴግ ሚሊዮን ብሶተኞችን በየቀኑ እያመረተ የራሱን የከፋና የተዋረደ ውድቀት እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡ ላለመውደቅ ግን መጠነ ሰፊ ጥፋት እያጠፋ ነው፡፡ አሳሳቢው ጉዳይ ግን ይኸ ነው፡፡ ሥልጣን የሕዝብ እንጂ የግል አለመሆኑን 4ኪሎ ከገቡ በኋላ መቀበል ሲያቅታቸው ይታያል፡፡ በዚህም አመለካከታቸው ከእነርሱ ሌላ ይህችን ሀገር ሌላ ሰው ችሎ የሚያስተዳድር አይመስላቸውም፡፡ በዚህም የሥልጣን ጥማት ችግር በሁለቱም አቅጣጫ ስላለ መዋቅር ዘርግተው ሀገር በመመሪያና በደንብ ሳይሆን በእነርሱ መልካም ፍቃድ እንድትተዳደር በማድረጋቸው በሰለጠነው ዓለም መሪዎች በየዓመቱ ከነቤተሰቦቻቸው ሲያርፉ የእኛዎቹ 22 ይሁን 100 ዓመትያለዕረፍትይሰራሉ፡፡ ይህም ሕዝብን ወደው ሳይሆን ሥልጣናቸውን ላለመነጠቅ ነው፡፡


ኢትዮጵያ ክብር ለዘላለም ትኑር!

No comments: