Monday, June 17, 2013

ፊፋ ከ ኢትዮጵያ ሶስት ነጥብ ቀነሰ ሃላፊነቱን ማን ወሰደው ???

ፊፋ ከ ኢትዮጵያ ሶስት ነጥብ ቀነሰ ሃላፊነቱን ማን ወሰደው ???

የሃገራችን እግር ኳስ ፌዴሬስን ኳስን በማያውቁ መመራቱ ጉዳቱ ዛሬ በግልጽ ታየ ። ትላንት ደቡብ አፍሪካን አሸንፈን ወደ ብራዚል ለምናደርገው ጉዞ አመቻቸን ስንል ፊፋ ደስታችንን የሚያቀዘቅዝ ዜና ይዞ ብቅ አለ ። ለነገሩ ፊፋ ምንም ጥፋት የለበትም የራሳችን ችግር ነው ። ግን በጣም የሚያሳዝነው ነገር የወያኔ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ስለ ውጭ ተጨዋቾች ሁለት ቢጫ ማየት እና ለጨዋታ ስላለመሰለፍ ብቻ ሳይሆን የውስጥ ሱሪያቸውን ቀለም ሳይቀር ሲዘግቡ የሚያውቁ ይመስሉ ነበር ። ነገር ግን በዚህ ወሳኝ ግዜ ለደስታችን መቀዝቀዝ ከፍተኛውን አስተዋጽዖ ካደረጉት አካሎች አንዱ ሁነው በመገኘታቸው አሳፋሪ ነገር ነው ። በሚገርም ሁኔታ ስለ ውሸት ቢሆን ቀድመው ተዘጋጅተው በመግባት ራዕይ የሌለውን መሪ " ባለ ራዕይ " ሲሉ ይደመጡ ነበር ።

ሌላው በዚህ ግዙፍ ስተት ውስጥ የ አምበሳው ድርሻ የሚዎስደው ያለሙያቸው ለአምባገነኑ ቡድን በተለያየ መንገድ ቀረቤታ ያላቸው እና የኢትዮጵያ ፉት ቦል ፌዴሬሽን ውስጥ በመስራት ላይ የሚገኙት አመራሮች ፣ የቡድን መሪዎች እና ሌሎችም ግለሰቦች ናቸው ። እነዚህ የቡድን መሪዎች ስለ ሃገራችንን የተጨዋቾ ች መሰለፍ መቻል አለመቻል ምንም ሳያሳስባቸው ከቡድኑ ጋር ሲወጡ ስለሚያገኙት አበል እና ከሚሄዱበት ሃገር የሚሰሩት ቢዝነስ የሚያስጨንቃቸው ግለሰቦች ናቸው ።

በዋናነት ተወቃሽ የሚሆኑት የቡድኑ አሰልጣኝ እና ሁለት ቢጫ እያለው ወደ ሜዳ ገብቶ መጫወት እንደማይችል ግንዛቤ የሌለው የብሄራዊ ቡድን ተጨዋች ምንያህል ተሾመ ነው ። በጥንካሬው በቅርቡ በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት በሌላ ሃገር እናያዋለን ብለን የምንጥብቀው ልጅ በዚህ ስተት ወስጥ መገኘቱ ሳዝናል ። አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውም ቢሆን ከተጠያቂነት የሚያድነው የለም ።

ከዚህ ሁሉ ነገር የኢትዮጵያ አምላክ የሃገራችንን የእግር ኳስ አፍቃሪ ደስታ ሳይቀዘቅዝ ሴንትራል አፍሪካን አሸንፈን ወደሚቀትለው ዙር የምናልፍ ያድርገን ።


No comments: