Friday, August 9, 2013

ምራቁን ዋጥ ያረገ መንግስት ቢኖር ኖሮ-ዛሬ ከጫፍ እስከጫፍ የተዳረሰውን 

የሙስሊሞች ጥያቄ ከአወሊያ ግቢ ሳይወጣ መፍታት በተቻለ ነበር።ይሁንና 

መንግስት ሆኖ የተቀመጠው የመንደሩ ጎረምሳ ኢህአዴግ ነውና በእልህ ተሞልቶና 

ነገሩን ሁሉ ገፍቶ ገፍቶ እዚህ ደረጃ ላይ አደረሰው።ይህ የጎረምሳው የእልኸኝነት 

ባህርይ ሁሌም ያሳዝነኛል። ከመገረም በላይ የሚያስቀኝ ባህሪው ግን ሁሌም ራሱ 

የቆሰቆሰው፣ያነደደውና ያቀጣጠለው እሳት አስደንጋጭ ደረጃ ላይ በደረሰ ቁጥር 

የሚያሰማው ክስ ነው፦”… ይህን እያረጉ ያሉት እነ ሻዕቢያ ናቸው፣..የሻዕቢያ 

ተላላኪዎችና ነጭ ለባሾች፣……ግንቦት 7..ሰማያዊ ፓርቲ፣ አንድነት ከአክራሪዎቹ 

ጀርባ ሆነው…..ቅብጥርሴ…” የሚለው ዓይነት ክስ ማለቴ ነው። የሙስሊሞች 

የመብት ይከበር አንቅስቃሴ ያስደነገጣቸውአንድ የመንግስት ባለስልጣን ከሳምንት 

በፊት ፦”ግንቦት 7፣ ሰማያዊ ፓርቲ እና አክራሪዎቹ ያልተለመደ አይነት ጋብቻ 

ፈጽመዋል’ብለው አሳቁን።ዛሬ በቪኦኤ የቀረቡት የህወሀቱ ሊቀ መንበር አቶ አበይ 

ወልዱ ደግሞ ለውጥረቱ እንደተለመደው ሻዕቢያን ከሰዋል።


“ባልመረጥነው መጂሊስ አንመራም!የራሳችንን የሀይማኖት መሪዎች ራሳችን 

እንምረጥ! የአህባሽን አስተምህሮ እንድንቀበል መንግስት ተጽዕኖ አይፍጠርብን” 

የሚሉ ቀላል ጥያቄዎችን መመለስ ያቃተው ጎረምሳ መንግስት፤በነዚሁ ጥያቄዎች 

አለመመለስ ሳቢያ ችግሮች እየሰፉ ሲመጡ፦ <<ከጀርባ ሆነው አመጹን የሚመሩት 

እነ እገሌ ናቸው>>ማለቱ በእርግጥ ያስቃል፣ያሳቅቃልም።

“የሞኝ(የአምባገነን) ዘፈን ሁሌ አበባዬሆሽ”

No comments: