Friday, August 23, 2013

ዜና ከባሌ ሮቤ


ዜና ከባሌ ሮቤ
==============
ሀሙስ ነሃሴ 16 ቀን 2005 ዓ.ም የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች ከሮቤ ከተማ ከንቲባ፣ ምክትል ከንቲባ፣ የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊና ከከተማው ካቢኔዎች ጋር 3 ሰዓት የፈጀ ውይይት አድርገዋል፡፡ ባለስልጣናቱ “አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን ማድረግ አይችልም፤ እኛ ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ስጋት አለብን፡፡ የቀድሞው ጠ/ሚር መለስ በፓርላማ እንደተናገሩት በአካባቢያችን የአልቃይዳ ክንፍ አለ” ብለዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች በበኩላቸው “በባሌ አካባቢ ያለውን የፀጥታ ችግር የምታውቁት እናንተ ናችሁ፤ አልቃይዳ ባሌ ውስጥ አለ ካላችሁ፣ ይሄንኑ የሚያረጋግጥ ይፋዊ ደብዳቤ ስጡን፤ይህ ካልሆነ ግን ሰላማዊ ሰልፉን እንቀጥላለን፡፡” የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡ ዛሬ ወደ ከንቲባው ጽ/ቤት የተጠሩት የአንድነት ተወካዮች “እሁድ በባሌ ሮቤ የገበያ ቀን ስለሆነ ሰልፍ ማድረግ አትችሉም፡፡” የሚል ምላሽ አግኝተዋል፡፡ ተወካዮቹም አንድነት ፓርቲ እሁድ ሰላማዊ ሰልፉን ከማድረግ የሚከለክለው ህጋዊ ምግንያት እንደሌለ አስረግጠው አስረድተው ወጥተዋል፡፡ #Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ

No comments: