Saturday, August 24, 2013

ባለ ራእዩ መሪ እና "The paradox society"


ባለ ራእዩ መሪ እና "The paradox society" 

ስለ ሟች ጠሚ ዜናዊ በ21 አመት የስልጣን ዘመኑ ካየሁት ያነበብኩት እና የሰማሁት በላይ ዘንድሮ ከሞተ ጊዜ ጀምሮ ላለፈዉ አመት ሙሉ በጣም ብዙ ተብሏል እየተባለም ነዉ

አሁን አሁን የሙት አመት ሲደርስ እና ሲከበር ከበፊቱ በገነነ መልኩ ለሰሚ እስከሚቀፍ እየተወራ ያለበት ሁኔታ ላይ ነዉ ያለነዉ,.... በእርግጥ መለስ እንደማንኛዉም መሪ የራሱ ደጋፊዎች ወዳጆች እንዲሁም ተቃዋሚዎች አሉት በአሁን ሰዓት በደጋፊዎቹ በኩል የሚዘገበዉ ከእዉነት የራቀ ከፕሮፖጋንዳ ያለፈ ፍጥጥ ያለ የሚቀፍ የሌለ ታሪክ እና ነጭ ዉሸት ነዉ
ላለፈዉ አመት ሙሉ እንደ ጉንዳን በአንድ መንገድ ተጓዙ እያሉን 85 ሚሊዮን ጭንቅላት በአንድ ሟች ራእይ ሲመሩን መቆየታቸዉ ሳይበቃ ለተደረገዉ ሁሉ ራእያቸዉ ነዉ አያሉ ልክ በ17 18 እና 19ኛዉ ክፍለ ዘመናት እንደ ነበሩ የ'Middle age Era ነገስታት በህዝብ እያሳለቁ እና እያሾፉ ነዉ

ከመንግስት ፓርቲ አባላት በላይ ትንሽ የሚገርመኝ ራእዩ ከሰማይ ቤት የወረደ የሂወት መመሪያ ራእይ ነዉ የሚሉ የህብረተሰቡ አካላት ናቸዉ,..... በአንድ አፋቸዉ ሲያሙ ቆይተዉ በሌላ የሚያሞግሱ አቋማቸዉ ግልፅ ያልሆነ እርስ በርሱ የሚጣረር አመለካከት ያላቸ ህዝቦች {the paradox society} ማለት እነዚህን ነዉ

ለነገሩ እንደዚህ አይነት አመለካከት በኢትዮጵያ አዲስ አይደለም

1. ጃንሆይ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን ጨፍልቆ ህዝብን በድሎ የከበርቴ እና ጭሰኛ የፊዉዳሊዝም ስርአት አንግቦ ህዝብ እየበደሉ ሲገዙ ህብረተሰቡ እሳቸዉን እንደ ፃድቅ/ነብይ ቆጥሮ ስዩመ እግዚአብሄር እያሉ ሲያመልካቸዉ ነበር ....ለፍትህ ለሰብአዊ መብት እና ነፃነት የታገሏቸዉ እነ መንግስቱ ንዋይ, ሻለቃ ሀይሌ, ጄኔራል ታደሰ ብሩ, በላይ ዘለቀ አና ሌሎች ስማቸዉ እራሱ በወግ አይነሳም

2. የሶሻሊስትዋ ኢትዮጵያ መሪ የኮሚኒስት ስርዓት ኣራማጅ አብዮታዊዉ ኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማሪያም (lack of wisdom in leadership) እዳሉት ሁሉንም በጡንቻ ህዝብን ሲጨፈጭፍ በ70 እና በ90 ብር ደሞዝ ለሀገር ህይወታቸዉን መስዉአት የከፈሉ አያሌ ወታደሮች በተለያዩ ሰንካላ ምክኒያቶች አብዮት ልጆችዋን ትበላለች እየተባለ ስንቱ አለ አግባብ እየተረሸነ ከንቱ ቀረ በዛ ላይ ስንቱ ለሀገር ብዙ ያረጋሉ እየተባለ የሚፈለጉ አንደነ ጄኔራል ፋንታ በላይ ኣምሀ ደስታ ሀይሌ ፊዳ ኩማ እና ብዙ ተጠርተዉ የማያልቁ ዜጎችን አጠፋ ይህም ሁሉ ሆኖ ብዙ የሚባሉ ወዳጆቹ የህብረተሰባችን አካላት እሱን ሀገር ወዳድ ቆራጥ ጀግና እያሉ እስከዛሬ ያሞካሹታል

3. በአሁን ሰዓት ደግሞ ስለመለስ ዜናዊ የምሰማዉ እና የማየዉ ከቀደምቶቹ አይለይም ወዳጆቹ እና ደጋፊዎቹ ሁሌ ከሚያመሰግኑበት ነገሮች አንዱ የልማት አባት ይሉታል ምንም እንኳን የ'Communism side effect በኑሮ ዉድነት ናላችን ቢዞርም በራእዩ ትልቅ እድገት አይተናል ይላሉ በእርግጥ ህንፃዎች መገንባታቸዉን ኮንደሚየም መሰራቱን በተለያዩ አርዳታዎች መንገድ አና የሀይል ማመንጫዎች ግድቦች መሰራታቸዉ ኣልክድም ሚሌነር ኣርሶ ኣደር እያሉ ቢያወሩም መራሩ እዉነት አሁንም 80% ያላነሰዉ በሞፈር እና በገሶ ነዉ የሚያርሰዉ ምንም ይሁን ምን በሌላ በኩል ይህ ድንቅ ራእይ በሰብአዊ መብት ዙሪያ ያለዉን አቋም ብናይ በጣም አሳፋሪ እና ለመስማት አስጸያፊ ነዉ ስልጣን ላይ ጉብ ካለ ጀምሮ ስንት የኦሮሞ ኣርቲስት ተማሪ እና ፖለቲከኛ ኦነግ አየተባለ ተገደሉ ታሰሩ ስንት የኦጋዴን ተወላጅ ONLF ትደግፋለህ እየተባለ ተገደለ ታሰረ ተደፈረ ተፈናቀለ ሟች አልነበረም 194 ንፁሀን ዜጎችን በኣዲስ ኣበባ 1997 በጠ/ሚ ቀጥታ ትዛዝ በኣጋዚ ጦር የተደፋት ??

ልማት ልማት ይላሉ እስቲ ይሁን እና ግን እንደ እኔ እንደ እኔ (development without freedom and basic human rights respected is to live like any organic decaying matter),.. ያ ባይሆን እማ የደቡብ ኣፍሪካ የነፃነት አባት ኔልሰን ማንዴላ የብሪታኒያ ወይም የነጮች ኣገዛዝን ባልተቃወመ መቼም ደቡብ አፍሪካ ላላት እድገት እና ልማት በኣፍሪካ ወደር የለሽ መሆኑን ማንም አይክድም ለዚህ ያደረሱት ደግሞ ኣፓርታይዱ የታላቋ ብሪታኒያ ገዢዎች መሆኑ የኣደባባይ ሚስጥር ነዉ ይህም ሁኖ ማንዴላ ልማት ስለሌለ ኣልነበርም የታገለዉ ፍትህ እኩልነት ነፃነት ፍለጋ ነበር ባጠቃላይ የልማት ጥያቄ ሳይሆን የሰብአዊ መብት ጥያቄ ነበር

ወደ ዉሃላ አስሬ ማየት ዉሃላ ያስቀራል ስለ ሟች ማንሳትም ኣልፈለኩም ነበር ግን ኡህን ፁሁፍ ቢጤ እንድ ፅፍ የገፋፋኝ ስሙን ታግ ማድረግ ያልፈለኩት አንድ አቀርቅሮ አዳሪ ስለ ሟች በትዊተር ገፁ ላይ አንዲህ ብሎ ፅፎ አምልኮቱን ሲገልፅ አይቼ ነዉ "በ3000 አመት የኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ ከሟች በስተቀር ጀግና የለም" አለ በሚገርም ሁኔታ THE ONLY የምትለዉን ካፕ ሎክ ነበር ያረጋት

ይህን ሁሉ ሳይ Simon Bolivar ያለዉ ትዝ አለኝ,... {{ስልጣን በአንድ ሰዉ እጅ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ እንደማድረግ ያለ ፍፁም አደገኛ ነገር የለም ። ሕዝቦችም ለእሱ መታዘዝን ባህል ያረጉታል እሱም እነሱን ማዘዝን ተገቢ አድርጎ ይወስደዋል ይህም የፍፁም ፈላጭ ቆራጭነት ምንጭ ነዉ}}
,... አስከ ሌላ ፈላጭ ቆራጭ Keep calm and follow the dead guy vision አለ ያ ካድሬ

No comments: