Thursday, August 29, 2013

ወንድሞችና እህቶች ልብ በሉ!

ወንድሞችና እህቶች ልብ በሉ! 

ብዙ የሚያግባቡን አጀንዳዎች፣ ብዙም በጋራ ልንተገብራቸው የምንችላቸው የሥራ 


መስኮች አሉ።

እስቲ ቆም ብለን እናስተውል!!!

ሀገራችንና ህዝባችን ብዙ ይጠብቅብናልና መጀመሪያ ለችግሮቻችን መፍትሄ እናብጅ።

ያሉብን አደራዎች ብርቱና ብዙ ናቸው። ለልዩነቶቻችን ቦታ አንስጥ። ምክንያቱም፤ 

ልዩነቶቻችን በጋራ ተደምረው ከምንስማማባቸው ጉዳይ ውስጥ የአንዱን ሚዛን 

መድፋትአይችሉም። የነዚያም ድንቅ ትውልዶች ባህሪ ለልዩነቶቻቸው 

ቦታ አለመስጠት ነበር። እንነሳ እናስተውል በቁርጠኝነት እነዚያን ህዝቦች 

ተከትለን ለአንድነት ቅድሚያ እንስጥ። እንደ ሙሀጂሮችና አንሷሮች 

የእውነት እንዋደድ፣ ለእውነት እንቁም። ያኔ ትክክለኛ ቁርኣናዊ ትውልድ 

መሆን እንችላለን!

No comments: