Friday, August 23, 2013


ቁጥራቸው እንዳሸን የፈላው የተቃዋሚ ፓርቲነኝ ባዮች አስተዋሽ ሲያጡ ተጣመርን 


ተቀናጀን ተዋሃድን ግምባርፈጠርን ይሉናል። ጥቅም ሲያጣላቸው ደግሞ ተለያየን 

እያሉ ለ22 ዓመት በዲሞክራሲ ስም ወያኔን በማጀብ ይሄን ያህል ጊዜ ሲቀመጡ 

ወምበር ከማሞቅና ከወያኔጋ ተባብሮ አገር ስትጠፋ አሰብ ወደባችን ሲዘጋ ድሆች 

ከመሬት ከንብረታቸው እየተፈናቀሉ የኢትዮጵያ መሬት ለውጭ ባዕዳን ባለሃብቶች 

ሲሸጥ ዜጎች በዘራቸው ከኖሩበት ቅየ ሲፈናቀሉ የኢትዮጵያመሬት ለጎረቤት አገር 

ተቆርሶ ሲሰጥ...ዝም ብሎ ከማየት በቀር ምን የሰሩት መልካም ስራ አለና ነው 

እንዲህ ዛሬ የሚያቅራሩ? የሰማያዊ ፓርቲን ያህል ሊሰሩ ቀርቶ አስበውት የማያውቁ 

ምድረ ወጣት አፍዝዝ አዚማም ቦዘኔ ሁላ ከነሱ የስም ቁልል ፓርቲ ሰማያዊ ፓርቲን 

አስወጡት አላስወጡት ምንም የሚቀንሱበት አለናነው?ለምን ተበለጥነ ነው?አዚማም 

ሁላ ስሩ! ሳምሶናይት ይዞ ወዲያና ወዲህ በመዞር መግለጫ በማውጣት ቢሮውስጥ 

በተሽከርካሪ ወንበር ቁጭ ብሎ የቆጥ የባጡን (የሰፈር ወሬ)ሲያወሩ በመዋል ለውጥ 

አይመጣም።የናንተ እንቶ ፈንቶ ወሬ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈይድለት ነገር 

የለም።የማዝነው ግን መኢአድም የተሻለ የተባለው ፓርቲ ከነዚህ ቦዘኔወችጋ 

መተባበሩ ነው። ሰማያዊ ፓርቲግን ከነሱ በመለየቱ በጀመረው ትግሉ ተጠናክሮ 

ቢቀጥል ባሁኑወቅት የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው የሚሰራለትን እንጂ 

የሚያወራለትን ስላልሆነ ተከታዩ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሚሆን 

አልጠራጠርም።

አይዞን ሰማያዊ ፓርቲ!


ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

Admas Keadmas

No comments: