Saturday, August 31, 2013

በነገው እለት


                     በነገው እለት 

ክርስትና እምነት ተከታዮች ላይም ይሁን ቤተክርስቲያን ላይ አደጋ ቢደርስ፤ 


ሙስሊሞችም ላይ ይሁን መስጊድ ላይ አደጋ ቢደርስ፤

ለአደጋው ብቸኛ ተዋናይና ተጠያቂ ህወሃትና ህሊናቢስ አጅ እባሽ ቀላዋጮቹ 


ናቸው፡አክራሪ አስልምና ተከታዮች አረጉት፤ ወይም አክራሪ የክርስትና እምነት 

ተከታዮች አደረጉት ብሎ እንደተለመደው ሊቀባጥር ይችላል፡ 


ምንም አለ ምን የኢትዮጵያ ህዝብ ከ22 አመት ተሞክሮው በትክክል ህወሀትን 


የተረዳው በመሆኑ። የረጅም ጊዜውን ትተን በትናንትናው እለት ሰማያዊ ፓርቲ 

አባላትና ቢሮ ላይ የፈጸመው አሳፋሪ ተግባር ማንነቱን ፍንትው አድርጎ ያሳየበት 

ጸያፍ ተግባር ነው።

ስለዚህ ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ሁሉ ተጠያቂው ህወሃትና 

አጨብጫቢዎቹ ብቻ መሆናቸው እስማሙም ሆነ ክርስቲያኑ ምዕመን ልብ 

ሊለው ይገባል። ህዝቡ አያውቀውም ለማለት ሳይሆን ለማስታወስ ብቻ ነው።


እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ



ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ~

ውድቀት ለዘረኞችና አምባገነኖች!!!

No comments: