Wednesday, August 28, 2013

መንግስት በግዳጅ እየጠራ ያለው ሰልፍ ላይ ሰልፈኞች ሁሉ ሃይማኖታዊ አለባበስ እንዲከተሉ አዘዘ!

መንግስት በግዳጅ እየጠራ ያለው ሰልፍ ላይ ሰልፈኞች ሁሉ ሃይማኖታዊ አለባበስ እንዲከተሉ አዘዘ!


‹‹ሰልፉን የጠራው መንግስት ነው አትበሉ፡፡ የሃይማኖቶች ጉባኤ ነው የጠራው በሉ›› የመንግስት ኃላፊዎች አንዳንድ የእምነት አባቶች ሰልፉን በተመለከ ቅሬታ አቅርበዋል!

የፊታችን እሁድ ነሀሴ 26 መንግስት በጠራው ሰላፍ ላይ ተሳታፊዎች ሃይማኖታዊ አለባበስ እንዲለብሱ ትእዛዝ ተላለፈ፡፡ ይህ የተላለፈው ትላንት ሰኞ በየክፍለ ከተማ አስተዳደሮች ሰብሳቢነት አማካኝነት ከየወረዳ መጅሊስ አባላትና ከሌሎች ሀይማኖቶች ጉባኤ ተጠሪዎች ጋር በተደረገ ስብሰባ ሲሆን ስብሰባውን የመሩት የመንግስት ኃላፊዎች ‹‹እንዲገኙ የምታደርጓቸው ሰልፈኞች ሀይማኖታዊ አለባበስ እንዲለብሱ አስገድዷቸው›› የሚል ትእዛዝ አቅርበውላቸዋል፡፡ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ ስብሰባው ከእስልምና ውጭ ከሆኑ ሀይማኖቶች ጉባኤ አባላት ጋር የተደረገ ሲሆን፤ ከቀኑ አስር ሰዐት ላይ ደግሞ ሕዝብ ካወረዳቸው የመጅሊስ ሹመኛ አባላት ጋር ባለስልጣናቱ የተናጥል ውይይት እንዳደረጉ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የየክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰብሳቢዎቹ ትላንት በቅድሚያ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ሲሆን በየክፍለ ከተማው ኢሕአዴግ /ቤቶች ውስጥ የኦርቶዶክስ /ክርስቲያን፣ የቃለ ህይወት፣ የሰቨን አድቬንቲስት፣ የካቶሊክና የወንጌላዊት መካነ እየሱስ ተጠሪዎችን ሰብስበው እስከዛሬ ስለተካሄደው ቅስቀሳ ሪፖርት የተቀበሉ ሲሆን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተወካዮች በተለይ ‹‹ጥሪ ስናደርግ ጥቂት የማይባሉ ምእመናን ቤተክርስቲያናችን በሰው ሃይማኖት እንድትገባ ለማድረግ የምትሞክሩት ለምንድነው? ከቻልን ፀሎት ማድረግ ካልቻልን ዝምታን መምረጥ ነው ያለብን፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ የፖለቲካ መጠቀሚያ ለምን ትሆናለች?›› የሚል ቅሬታ ቀርቦብናል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም ‹‹እኛ ግን መንግስት ያዘዘው ስለሆነ ሰልፉ ላይ መካፈል አለባችሁ እያልን ነው›› የሚል ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ የተቀሩት ሀይማኖቶች ተወካዮችም ተመሳሳይ ይዘት ያለው አስተያየት ቢገጥመንም የተለያዩ ምክንያቶችን እያቀረብን በሰልፉ ሕዝቡ መገኘቱ ግድ እንደሆነ አስረግጠን ተናግረናል ብለዋል፡፡ ከሪፖርቱ በመነሳት ምላሽ የሰጡት የክፍለ ከተማዎቹ አመራሮች በበኩላቸው ‹‹እዚህ ላይ መሳት የሌለባችሁ ነጥብ ቢኖር ሰልፉን ስትጠሩ መንግስት ጠራው ብላችሁ ሳይሆን የሀይማኖቶች ጉባኤ ነው ማለት ያለባችሁ፤ አለበለዚያ እሺ ብለው ሰልፉ ላይ አይገኙላችሁም›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋቸዋል ፡፡ አመራሮቹ በመቀጠል ‹‹ቤተክርስቲያን በሰው ሃይማኖት መግባት የለባትም፣ የፖለቲካ መጠቀሚያ ለምን ትሆናላችሁ የሚሏችሁ አንዳንድ ኪራይ ሰብሳቢ የኢሕአዴግ ተቃዋሚዎች ስለሆኑ አትስሟቸው›› የሚል ትእዛዝ ያስተላለፉ ሲሆን ተሰብቢዎቹም በቀጣዮቹ ቀናት የተጠቀሱትን ችግሮች በማስተካከል ሰልፉን መጥራት እንዲቀጥሉ አዘዋል፡፡

ሰልፈኞች ሲመጡ የግድ ቤተክርስቲያናዊ አለባበስ እንዲለብሱ መደረግ አለበት ያሉት የመንግስት ሀላፊ ለዚህም ‹‹ይህ ካልሆነ ሰልፉ ሳይጠናቀቅ መንገደኛ እየመሰሉ ሾልከው ይጠፉባችኋል›› ሲሉ ምክንያታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ መንግስት የሃይማኖት ተቋማትን በዚህ መልኩ በመሰብሰብ የየእለት መመሪያዎችን ትእዛዝ እያስተላለፈ ያለበት ሁኔታ እጅግ ብዙዎችን እያስገረመ የሚገኝ ሲሆን በሕገ መንግስት የተቀመጠው የሃይማኖትና መለያየት ትርጉም አልባ እየሆነ መምጣቱን አመላካች ነው፡፡ ከስብሰባው በኋላም አንዳንድ ተሰብሳቢዎች ‹‹በክፍለ ከተማችን ኢሕአዴግ ፅህፈት ውስጥ ቤት መንግስት እየሰበሰበን እንዴት ነው ሰልፉን የጠራው መንግስት አይደለም ብለን የምንዋሸው?›› ሲሉ ማማረራቸው ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡
አላሁ አክበር!

ድምፃችን ይሰማ 

No comments: