Friday, August 23, 2013

ዜና ከአዲስ አበባ ፤ ፍኖተ ነጻነት

ዜና ከአዲስ አበባ ፤ ፍኖተ ነጻነት

በመጪው እሁድ ነሃሴ 19 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚገኘው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መ.ኢ.አ.ድ/ ዋና ጽ/ቤት 33ቱ ፓርቲዎች ለጠሩት ህዝባዊ ውይይት የመኪና ላይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ የፓርቲዎቹ አባላት በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡ አቶ ደመላሽ፣ አቶ አብርሃም ፣ አቶ አታላይ በለው፣ አቶ እዮብዘርና አቶ መላኩ መሰለ የተባሉት አባላት የቅስቀሳ መከናውን ከያዘው ሹፌርና ረዳት ጋር ታስረዋል፡፡ የፓርቲዎቹ አመራሮች አባሎቻቸው ወደታሰሩበት 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ አቅንተው እስሩ ህጋዊ አለመሆኑን አዋጅ በመጥቀስ ቢያስረዱም በስፍራው የነበሩት የፖሊስ አዛዥም
“እኔ በአዋጅ ሳይሆን በትዕዛዝ ነው የምመራው፤ እሰር የሚል ትዕዛዝ ደርሶኝ አስሬያቸዋለሁ”
934939_487240494685925_524628143_nየሚል ምላሽ ሸሰጥተዋቸዋል፡፡ #Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ

No comments: