Saturday, August 24, 2013

የአምባገነኖች ቅዠታዊ እድገት ተዋርዶ ከመቀበር አያድናቸውም!!

የአምባገነኖች ቅዠታዊ እድገት ተዋርዶ ከመቀበር 

አያድናቸውም!!

የአምባገነኑ ኢህአዴግ ሚዲያዎች 24 ሰአት የሚለፈልፉት ቅዠታዊ የኢኮኖሚ 

እድገት ተራ ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ ብዙሃኑ ይረዳዋል። አደገች የምትባለው አገር ወደ 

ኋላ መንሸራተቷን የቀጠለች ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ በርካታ አካባቢዎች 

መብራት ከተቋረጠ ቀናትን እያስቆጠረ ነው። በዛሬው እለት በደረሰኝ መረጃ በወሎ 

ሰፈር አካባቢ 6 ቀናት፣ በልደታ እና አብነት 3 ቀናት፣ በ22 እና አካባቢው 2 ቀናት 

እንዲሁም ኮልፌ አካባቢ 4 ቀናት ከመብራት ውጪ ሆነው ህዝቡ በሻማ 

እየተጠቀመ፣ ሌቦችም በመበራከታቸው የደህንነት ስጋቶች በሰፊው እየተስተዋሉ 

ይገኛሉ። (እረየመብራትያለህ DarkAddis)

No comments: