Friday, August 30, 2013

ሰላማዊ ትግልን የሚገድብ ህገወጥ መመሪያ ተግባራዊ ሆነ

ሰላማዊ ትግልን የሚገድብ ህገወጥ መመሪያ ተግባራዊ ሆነ



የአዲስ አበባ መስተዳድር ካቢኔ አዲስ የሰላማዊ ሰልፍና የሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ 

መመሪያ በማዘጋጀት በህገወጥ መንገድ ተግባራዊ ማስደረጉ ታወቀ፡፡

ነሃሴ 10 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ካቢኔ የፀደቀውናለ Addis Ababa 


Police ኮሚሽn የተላከው መመሪያ ከሕዝብ ፊርማ ለማሰባሰብ፣በራሪ ወረቀት 

ለመበተን፣ በማይክራፎን ለመቀስቀስና ፖስተር ለመለጠፍ ውስብስብና የተለያዩ 

አካላትን ፍቃድ ማግኘትን የግድ የሚል ነው፡፡

የመመሪያው አወጣጥ ህገወጥነት እንደተጠበቀ ሆኖ መመሪያው በነጋሪት ጋዜጣ 


ታትሞ ሳይወጣና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ሳይሰራጭ፤ የአዲስ አበባ 

ፓሊስ ኮሚሽን ህገወጡን መመሪያ እንዲያስፈፅም ከአዲስ አበባ መስተዳድር ከንቲባ 

ጽ/ቤት ትእዛዝ መተላለፉ በኢትዮጵያ የህግ የበላይነት እንዳበቃለት የሚያሳይ ነው፡፡

የመመሪያው ህገወጥነት አሳሳቢ በመሆኑ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንንበር ዶ/ር ነጋሶ 


ጊዳዳ እና የፓርቲው ዋና ፀሀፊ አቶ አስራት ጣሴ ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን 

ኮሚሽነር ግርማ ካሳና ከኮሚሽኑ 3 ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት 

ህገወጡን መመሪያ ፖሊስ ኮሚሽኑ እንዲያስፈፅም መታዘዙን አረጋግጠዋል፡፡

“መመሪያው በ1983 ዓ.ም ከወጣው (አዋጅ ቁጥር 3/1983 ዓ.ም ስለ ሰላማዊ 


ሰልፍና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ሥርዓት የወጣ አዋጅ ገጽ 12) አዋጅ ጋር 

የሚጣረስ ነው፣ በአዋጁ የአዲስ አበባ መስተዳድር የራሱን መመሪያ ማውጣት 

እንደሚችልም የሚገልፅ ነጥብ የለም.

No comments: