Friday, August 9, 2013

ይህቺ በጣም አጭር VIDEO በትናንትናዉ እለት ስቴዲየም አካባቢ ካለዉ ድብደባ ተርፈዉ ወደቤታቸዉ በመመለስ ላይ እያሉና ቤታቻዉ ሊገቡ ትቂት ሲቀራቸዉ አሰቃቂ ድብደባ የተደረገባቸዉን ሙስሊሞችን በከፊል ታሳያለች ፡፡ ቦታዉ ጦርሀይሎች አካባቢ ነዉ ከስቴዲየም በግምት 10 – 12 . ርቀት ላይ ይሆናል ፡፡ በዚህ እርቀት ላይ እንኳን በመሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ የዚህ አይነት ድብደባ ተካሂዷል ፡፡ መጀመሪያ በሰላም እየመጡ የነበሩ ሙስሊሞችን አንድላይ ካሰባሰቡ ቡሃላ አሰቃቂ ድብደባቸዉን ሲት ህፃናት ሳይለዮ ጀመሩ በዚህ ግዜ የተወሰኑ ሴቶችና ህፃናት ሸሽተዉ ምስሉላይ በሚታየዉ ደረጃ ላይ ወተዉ ያመልጣሉ ትንሽ ሲረጋጋ ተመልሰዉ ለመሄድ ሲሞክሩ ነዉ ከታች ሲጠባበቁ በነበሩ ጨካኝ ፖሊሶች የሚታየዉ አይነት ድብደባ የተፈፀመባቸዉ ፡፡ VIDEO ዉን አንዲት እህታችን መኪና ዉስጥ ሆና ነዉ የቀረፀችዉ ፡፡ ተመሳሳይ ድብደባዎች በአራቱም የከተማይቱ አቅጣጫዎች በሰላማዊዉ ሙስሊም ላይ ተፈፅመዋል ፡፡
ይህንን ድርጊት ትናንት የቀብር ስነ - ስረአቱ በህዝበሙስሊሙ የተፈፀመዉና የህገወጡ የፌድራል መጂሊስ ፕረስደንት አቶ .ኪያር በእርኩስ መንፈሳቸዉ ETV ዜና ላይ ቀርበዉ በአጭሩ እንዲህ ሲሉ ገልፀዉታል
መንግስት የወሰደዉ እርምጃ ተገቢና ትክክለኛ ነዉ ፡፡
እዉነት ግን እነዚህ የመጂሊስ አመራሮች ከሞት ቡሃላ መቀስቀስ መኖሩን ያምኑ ይሆን

No comments: