Friday, August 30, 2013

የኢሕአዴግ ወታደራዊ ትጥቅ ማምረቻ ፋብሪካ ተቃጠለ |

የኢሕአዴግ ወታደራዊ ትጥቅ ማምረቻ ፋብሪካ ተቃጠለ | 
(ይህን የሚሊተሪ ልብስ የሚያመርተው ፋብሪካ ነው የተቃጠለው)
(ይህን የሚሊተሪ ልብስ የሚያመርተው ፋብሪካ ነው የተቃጠለው)












በመከላከያ ሚኒስትር የትጥቅና ወታደራዊ ልብስ ስፌት ፋብሪካ ህንጻ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ማስታወቃቸውን ኢሳት ራድዮ ዛሬ ዘገበ። የእሳት አደጋ ቃጠሎ በሕንፃው ላይ ጉዳት እንዳደረሰና እንዳወደመ የዘገበው ኢሳት ራድዮ የአደጋውን ምንጭ እያጣራሁ ነው ብሏል።
ከአዳማ ከተማ ወደ ወንጂ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው ወታደራዊ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ በፋብሪካው ላይ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት መድረሱን የዘገበው ራድዮው በ18 ሚሊዮን ብር ወጪ በቅርቡ የተገነባው ፋብሪካው የተለያዩ ወታደራዊ ዩኒፎርሞችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ሲሆን የደረሰው አደጋ መንስኤ ሊታወቅ አልቻለም ብሏል።
እንደ ራድዮው ዘገባ ከሆነ በፋብሪካው ላይ የደረሰውን ቃጠሎ ለማጥፋት ከአዳማ ከተማ የእሳት ማጥፊያ ባለመኖሩ ደብረ ዘይት ከሚገኘው አየር ሀይል እሳት ማጥፊያ እስከሚደርስ ድረስ የተነሳውን እሳት ማጥፋት አለመቻሉን የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ ለአንድ ሰዓት ያህል በቆየው የእሳት አደጋ ግምታቸው ከፍተኛ የሆነ ማሽኖች ላይ ጉዳት እንደደረሰ የታወቀ ሲሆን ከአራት ቀናት በፊት መንግስት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የገዛቸው ማሽኖች በፋብሪካው ገብተው እንደነበረ ታውቋል ሲል ኢሳት ራድዮ ዘገባውን አጠናቋል።
ከአደጋው በስተጀርባ ሊደበቅ የተፈለገ የሙስና ወንጀል ይኖር ይሆን?

No comments: