Saturday, August 31, 2013

ድምፃችን ይሰማ ግልፅ መልዕክት ለሰልፉ ተሳታፊ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች!


ድምፃችን ይሰማ




#ForcedGovtDemonstration #Nehase26Demonstration


ግልፅ መልዕክት ለሰልፉ ተሳታፊ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች!


ቅዳሜ ነሐሴ 25/2005

አገራችን ኢትዮጵያ ካለባት ውስብስብ የፖለቲካ ችግሮች በተቃራኒ ህዝቦቿ ተቻችለው ለዘመናት 


ዘልቀዋል፡፡ አብዛኛው 

ገዢዎቻችን በአገዛዝ ዘመናቸው ይህን ውስብስብ የፖለቲካ ሰንኮፍ ለህዝብ በሚጠቅም መልኩ መንቀል ሲሳናቸው የህዝብ 

ጥያቂ አቅጣጫ ለማሳት ያልተጠቀሙት እጅግ አደገኛና አገር ያበጣብጣል የተባለ ዘዴ አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡ የማታማታ 

ህዝብ እንደ ህዝብ ለዘመናት አቆይቶ በጠበቀው መስተጋብር ራሱን ከገዢዎች ሴራ ሲጠብቅ ቆይቷል፡፡ የገዢዎቹ ሴራ ጥንካሬ 

ቢኖረውም ማህበረሰባችን ታንፆ የሚያድገው በሚከተለው የሃይማኖት ቀኖና በመሆኑና ለተንኮለኞች ሴራ የሚሰጠው ምላሽ 

ግብታዊ ሳይሆን በመንፈሳዊ ስብዕናው ታግሶ በመሆኑ የቀደሙ አገዛዞች ተንኮታኩተው ሲወድቁ ህዝቦች ማንነታቸውን 

ጠብቀው ዛሬም ድረስ ቆይተዋል፡፡ ይህን ታሪክና ማንነት ጠብቀን ልናቆይ የምንችለውና የተንኮል እቅዶችን ማምከን 

የሚቻለውም ህዝቦች ባለን የሃይማኖት ስብእና በመታገዝ እንጂ በርካሽ ፖለቲካ ተጠልፈን በመውደቅ አይደለም፡፡ 

የሃይማኖቶች ጉባኤ ጠርቶታል የተባለው የነገው ሰልፍም ይህ መርህ በተንኮለኞች ሴራ ሳይጠለፉ መስተጋብራችንን ጠብቀን 

ለመቆየታችን ቋሚ ማሳያ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ሊሆንም ይገባል፡፡


ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳቸውን ሰላማዊ የመብት ጥያቄዎች በዴሞክራሲያዊ አግባብ ከመመለስ ይልቅ መንግስት ይከተላቸው 


የነበሩ የስም ማጥፋት አካሄዶች ባለፉት ሁለት አመታት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲያቀርብ ነበር፡፡ ውንጀላዎቹ ከሙስሊሙ 

ጥያቄ ጋር ምንም ዝምድና ስለሌላቸው ተቀባይ ሊያገኙም አልቻሉም፡፡ እንደውም ከሙስሊሙ እኩል የሌሎች እምነት 

ተከታዮች የህዝብ ጥያቄ እንዲመለስ ሲሉ በየስብሰባው የሚያምኑበትን እየገለፁ ነው፡፡ ይህም ህዝባዊ ማንነታችንን ጠብቀን 

የማቆየታችን ትልቅ ማሳያ ነው፡፡ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠርቶታል በተባለው በነገው ሰልፍ ህዝበ ሙስሊሙ ሁለት 

አላማን በማንገብ ሰልፉን ይቀላቀላል፡፡

የመጀመሪያው ኢትዮጵያ ሃገራችን በሰላም እና ህዝቦች በተግባቡበት የጋራ ህገ-መንግስት እንድትተዳደር የፖለቲካን ጨምሮ 


ማንኛውም አይነት አክራሪነትን ለማውገዝ ሲሆን ሁለተኛው አላማ ደግሞ ከተቀሩት የሃገር ወንድምና እህቶቻችን ጋር የቆየውን 

መስተጋብራችንን በመከባበርና በመተባበር መንፈስ ለማስጠበቅ ነው፡፡ ዛሬ መንግስት በሙስሊሙ ላይ እያደረገ ያለው ብሄራዊ 

ጭቆና መፍትሄ ሳያገኝ ለሁለት አመት እንዲዘልቅ ያደረገው እንዲሁ በዘፈቀደ ምንም አያመጡም በሚለው ሳይሆን ለተንኮል 

በር ያልከፈተው የህዝብ አንድነት ስላሰጋው ነው፡፡ ይህን የህዝቦች አንድነት ለመናድ ባለ በሌለ ሃይሉ ሙስሊሙን ወደ አመጽ 

ለመምራት እጅግ አስከፊ በደሎችን ሲፈጽም ታዝበናል፡፡ እስካሁን በህዝብ ታጋሽነትና በሰላማዊ አካሄድ ለማምከን የተቻለ 

ቢሆንም፡፡


የነገው ሰልፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠራው ቢባልም የሁላችንንም ቤት እያስጨነቁ ያሉ ካድሬዎች ሃይማኖታቸው 


ፖለቲካ የሆኑ ቅጥረኞች አሊያም የእንጀራ ጉዳይ ያስገደዳቸው የመንግስት ሰራተኞች ናቸው፡፡ ይህ እንግዲህ ሌላኛው ምእራፍ 

መሆኑ ነው፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ በሰልፉ ላይ የሚሳተፍበት ሁለተኛው አላማም በቦታው አለመገኘት ማለት መንግስት 

የጀመረውን በህዝብ መሃል የጥላቻ እሳት የማቀጣጠሉን ሂደት መፍቀድና ክፉ ሴራው ነፍስ ዘርቶ ለሃገራችን አደጋ 

የሚሆንበትን በር ለመዝጋት ነው፡፡ በቦታው መገኘት መንግስት እየሰራ ያለውን ታረካዊ ስህተት የማረም አገራዊ ሃላፊነት፤ 

ምንም በግፍ ብንጨቆንም አገሪቷን እንደአገር ቆማ እንድትሄድ ያደረጋትን ሃይማኖታዊ መስተጋብራችንን የምንከፍለውን ዋጋ 

ከፍለን የምናስጠብቅበት ብቸኛ አማራጭ በመሆኑ ነው፡፡ በሚዲያዎች እና በስብሰባዎች የውስጥ አርበኞችን በመጠቀም 

ሃይማኖተኞችን እምነታቸው ከሚያዛቸው አብሮነት ይልቅ ለፖለቲካ ግዳጅ ሲሉ መከፋፈልን እንዲመርጡ እንዳደረገ 

የተሰማው አካል ካለ መላው የአዲስ አበባ ነዋሪ ይህ ሊሆን እንደማይችል ነገ በይፋ ያሳያል፡፡


እኛ ሙስሊሞች የነሐሴ 26ቱ ‹‹አክራሪነትን የማወገዝ ሰልፍ›› ላይ የምንገኝበት አብይ ምክንያት አክራሪነትን በማውገዝ ደረጃ 


ከእምነታችን የተቀዳ የጠነከረ መርህ ተከታዮች በመሆናችን ነው፡፡ እምነታችን የአክራሪነትን ጉዳት በግልፅ ያስተምራል፡፡ 

አጀንዳው አገራዊ ብቻ ሳይሆን ግዙፍም ነው፡፡ ይህን መርህ በመከተል በርካታ ወራትን ያስቆጠረው ሠላማዊ የተቃውሞ ሂደት 

አክራሪነትን ለማውገዝ የሞራልና የህግ ግዴታ አለበት፡፡ የዕለቱን ውሎ ሠላማዊነት አስመልክቶ ያካበትነው ልምድ እጅጉን 

እንደሚጠቅመን ጠንካራ መተማመን አለን፡፡ ሂደቱ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ ተጀምሮ ያልቅ ዘንድ የምናበረክተው የተሰባጠረ 

ሁለንተናዊ አስተዋፅኦ የዕለቱን መልዕክት በሚገባ አድርሰን ለመምጣት እጅጉን ይጠቅመናል፡፡ የሌሎች እምነት ተከታይ ወገኖች 

የተለመደ ሰላማዊ ገፅታችንን በአካል እንዲመሰክሩ እና በቀጣይ ለጥያቄዎቻችን መመለስ እንደቀዳሚው ጊዜ ሁሉ ድጋፋቸውን 

እየለገሱ እንዲቆዩም የሚያደርግ ነው፡፡

አላሁ አክበር!

No comments: